Get Mystery Box with random crypto!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የሰርጥ አድራሻ: @ahmedin99
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 60.13K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2024-04-20 22:06:44 “ሌሊት መስገድን አስቦ ወደ ፍራሹ የሄደ ከዚያም እስከ ንጋት ዓይኑ ያሸነፈችው ያሰበውን አላህ ይፅፍለታል፤ እንቅልፉም ከጌታው ዘንድ ሶደቃ ይሆንለታል”

ረሱል ﷺ

(ነሳኢ 1787ና ኢብኑ ማጀህ 1344)
13.6K views19:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-20 18:22:15 በድንገት ከሁሉም ለየት ያለ ሰው ወታደራዊ ልብሱን እንደለበሰ መትረየሱን ደግኖ ወደ ሰልፉ ጠጋ አለ። የአስተባባሪዎቹ ዓይን በቅጽበት በርሱ ላይ ዐረፈ።የባሕር ኃይል ምክትል ኃላፊ የነበረው ኮማንደር ዘካርያ ይባላል። ሙስሊም ነው። የእምነት ጭቆና አንገሽግሾታል። ብዙ በደሎች ደርሰውበታል። ሌላ ምንም ጥፋት አላጠፋም፤ወንጀሉ ሙስሊም መሆኑ ብቻ ነበር! ጠጋ ብሎ ወደ ሰልፉ ተቀላቀለ። መትረየሱን ደግኖ የመጣው ‹‹ከመንግሥት ኃይል ጥቃት ይፈጸምብናል›› በሚል ሥጋት ነበር። ዶ/ር አሕመድ ቀሎ ጠጋ ብሎ ‹‹ይህ ምንድን ነው?›› ሲል ጠየቀው። ‹‹ዛሬ ቀናችን ነው! ብናልቅም ጨርሰን ነው የምንሞተው!›› ሲል መለሰ። በርግጥ ሰልፉ የተጠራው ያለፈቃድ ነው። ሆኖም መንግሥት ሳይወድ በግድ ሰልፉ እየተካሄደ ነው። ዶ/ር አሕመድ ቀሎ አግባብተው ሰይፉን ብቻ ታጥቆ ከነወታደራዊ ልብሱ በሰልፉ እንዲሳተፍ አደረጉት።

ሙስሊሙ ለመብቱ ሲል እንዲያ ሲሆን ለጥቅም ብለው ከመንግሥት ጋር የወገኑ ሙስሊሞችም አልጠፉም። ከሙስሊሙ መብት መከበር ይልቅ ለነሱ የበለጠባቸው ዓለማዊ ጥቅም (ከመንግሥት የሚገኝ ጥቅም) ነበርና። የሙስሊሙ ስሜትና ብሶቱን የሚያሰማበት አኳኋን አስደንጋጭ ነበር። ማንም ‹‹እንደዚህ ያለ ሰልፍ ይደረጋል›› ብሎ አልጠበቀም ነበር። ‹‹ሙስሊሙ እንዲህ ይበዛል›› ብሎ የገመተም አልነበረም። ሰልፉን ለማክሸፍ ሲራወጡ የነበሩት የደህንነት አባላትም ጥረታቸው ከሽፎ ከፖሊስ ጋር ፀጥታ ለማስከበር ጥግ ጥጉን ይዘዋል።
ሰልፉ ተጀመረ። እየዘመረ፣ መፈክር እያሰማና ተክቢራም እያለ ከአንዋር መስጂድ ተንቀሳቀሰ። ሐብተ ጊዮርጊስ ድልድይን ተሻገረ። ፒያሳን አቋርጦ ራስ መኮንን ድልድይን አለፈ። አራት ኪሎ አካባቢ ሲደርስ ትንሽ ግርግር የሚጀመር መስሎ ነበር። ግና ወዲያው ተረጋጋ። ጉዞውንም በሰላም ቀጠለ። በየመንገድ ዳር የቆሙና በየፎቅ በረንዳ ላይ በመስኮት በኩል በሚመለከቱት ጭብጨባ ደመቀ።መፈክሮች ተስተጋቡ፡-

‹‹ሀገር የጋራ ነው! ሃይማኖት የግል ነው! እስላማዊ በዓላት ብሔራዊ በዓላት ይሁኑ! ‹ኢትዮጵያዉያን እስላሞች› ተብለን እንጠራ! የሃይማኖት ልዩነት በየትም ቦታና መሥሪያ ቤት ይቅር! የእስልምና ሃይማኖት የመንግስት ድጋፍ ይኑረው! ኢትዮጵያ በሃይማኖት መከፋፈል የለባትም! ኢትዮጵያዉያን እስላሞችና ክርስቲያኖች ወንድማማቾች ናቸው! በኢትዮጵያዉያን መካከል አንድነት ለዘለዓለም ይኑር! ኢትዮጵያ በልጆቿ አማካይነት ወደፊት ትራመድ! አንድነት ኃይል ነው! ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዉያን ደሴት ናት! ነቀፌታ የማይቀበል መንግሥት ዘለቄታ የለውም! (የኢትዮጵያ የጥናትና ምርምር ተቋም፣ ማኑስክሪፕት ክፍል፣ ማኅደር ቁጥር 2396/02/5)

ይቀጥላል....
14.2K views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-14 14:51:40 “ሰዎች ቢያዩብህ የምትጠላውን ነገር ብቻህን ስትሆን አትስራው።”

ነቢዩ (ﷺ)
18.0K viewsedited  11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-13 20:52:51 “ከፆም፣ ከሰላት፣ ከሰደቃ በላጭና ደረጃው ከፍ ያለውን ተግባር አልነግራችሁምን? እንዴታ! ይንገሩን አሉ ሶሃቦች፦ ‘በሰዎች መካካል ማስታረቅ’ ነው አሉ።”

ረሱል (ﷺ)
14.3K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 23:00:04 ለወንድምህ ዱዐ አድርግለት

“ወንድም ለወንድሙ በሌለበት የሚያደርገው ዱዓ አይመለስም። (ተቀባይነት አለው)።”

ረሱል (ﷺ)
17.4K viewsedited  20:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-12 21:01:04 ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ!


በትንሹ ለ100 ሺህ ዓመታት ቀብርህ ውስጥ ምን ትሰራለህ? ከደጋጎቹ አንዱ ለዚህ ጥያቄ መልስ ይሰጣሉ። "በርግጥ ለደጋጎች ካልሆነ በቀር ቀብር አስፈሪ ነው። ዱንያንና ውስጧን እጅግ የምጠላ ስሆን አሁን እድሜዬ 54 ነው። በትንሹ ቀብሬ ውስጥ ለ100 ሺ ዓመታት ምንድን ነው የምሰራው? ስል አሰብኩ።

እናም እንደሚከተለው መስራት ጀመርኩ ። እኔ እንደሆነ እሞታለሁ፣ የሚጠብቀኝም ሙሉ በሙሉ ጨለማና ባዶ የሆነ ቀብር ነው። እናም ይህ ቀብር ጌጣጌጥ ይሻል፣ የማደርጋትን እያንዳንዷን ኢስቲግፋርና አዝካር ብቸኝነቴን ያጫውተኝ ዘንድ ወደ ቀብሬ ቀድሞ እንዲጠብቀኝ እየላኩት ነው ብዬ ማሰብ ጀመርኩ። እውነቴን ነው አልቀለድኩም፣ የቀብሬን ለሕድ በሺዎች በሚቆጠሩ ተስቢሖች ማጌጡን ተያያዝኩት።

እዚህ ሳለሁ በትንሹ 300 ጊዜ ቁርአንን ቀርቼ አኸትመዋለሁ፣ እያንዳንዷን የሰላት ረከዐ ለቀብር ሒሳብ አካውንት ላይ ጥሪት አድርጌ አስባታለሁ፣ ሁሉም ጥሎኝ ወደ ቤቱ ይመለሳል፣ ምናልባት ብቻዬን ሚሊዮን ዓመታትን እዛ ነኝ። ቀብሬ የግድ ጨፌ፣ ብርሃናማ እና የምርም ጀነት መሆን ይኖርበታል።

እናም ከእያንዳንዷ መልካም ተግባር፣ ከዚክርና ቁርአኔ፣ ከሰደቃና ተሸሁዴ በነርሱ ተከብቤ አብረን ስንስቅና ስንጫወት በእዝነ ህሊናዬ አስባለሁ። በዚህ ጨዋታ መሃል በረሱሉ (ሰዐወ) የተደረገ ሶለዋት ጨዋታውን ሲካፈል አስባለሁ። ከሕይወት በኋላ ሌላ ሕይወት....

ምድር ላይ ሳለሁ ከሃሜትና ነገር ማዋሰድ፣ ለአላህ ተብሎ ካልተሰራ ስራዬ ውጤት ማለትም ከጭንቀት፣ ከቅጣትና ከጨለማና ቅጣት አይሻለኝም?!

ከዛሬ ጀምሮ ለናንተ ያለኝ ምክር ይላሉ ይህ ደግ ሰው

ቀብራችሁን ባንክ አድርጉትና ሁሌም ከመልካም ስራዎች ጣል እያደረጋችሁበት ሙሉት። በዒባዳዎች ላይ ጠንክሩ። ወላሂ ቀብር ውስጥ ሆነህ ታመሰግነኛለህ፣ ከዱንያ ይልቅ ለወዲያኛው ዓለም ተጠበብ።

አሁንማ ቤተሰብ መሃል ሆነህ ያሻህን ትለብሳለህ፣ ትመገባለህ እንዲሁም ደስ ብሎህ እንቅልፍህንም ትተኛለህ። ሁሉም ፍላጎቶቻችን ተሟልተው እንኳ ተጨባጫችንን እናማርራለን። ይህ ምቾት ማጣት እስቲ ከምድር ሆድ ውስጥ ቢሆን ብለህ አስበው?!

ስለዚህ እያንዳንዷን ተስቢሕ በትኩረት አድርግ፣ መልካም አጫዋችና አቀማማጬ ትሆኝልኝ ዘንድ ቀብር ቀድመሽ ጠብቂኝ በላት።"

[ሐሳቡ (አላህ ይዘንላቸውና)የዶክተር ሙስጠፋ ማሕሙድ ነው።]

ኡስታዝ በድሩ ሁሴን
13.0K viewsedited  18:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 19:25:06
ሴኩላር የሚሆነው ተማሪው ነው ወይስ የትምህርት ስርዓቱ?

T.me/ahmedin99
14.0K viewsedited  16:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 14:59:32
‘ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በሀይማኖታቸው ምክንያት እየተበጠሩ ወደ ዳር እየተደረጉ ነው።”

T.me/ahmedin99
13.6K viewsedited  11:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 12:43:28
አመተ ምህረት ምንድነው?

@ahmedin99
14.4K views09:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-04-11 10:50:36 “አላህ የታመፀባቸውን ሁሉንም ወንጀሎች ምህረት ያደርጋል። በሱ ላይ አጋርቶ የሞተ ሲቀር።”

ረሱል (ﷺ)
13.0K views07:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ