Get Mystery Box with random crypto!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የቴሌግራም ቻናል አርማ ahmedin99 — Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል
የሰርጥ አድራሻ: @ahmedin99
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 59.96K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2024-01-12 11:29:19
በነቢዩ ሙሀመድ [ﷺ] ላይ ሰለዋት ሲያደርጉ ሀጥያት እንደሚራገፍልዎ ያውቃሉ?

የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ) እንዲህ ብለዋል:–

"በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። አስር ኃጥያቶችንም ያራግፍለታል።"

"Namni anarrattii salawaata tokko buuse Rabbiin isarratti salawaata kudhan buusa. Badii kudhan isaaf dhiisa."

Nabi Muhammad(saw)
14.5K views08:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-11 10:54:54
ውሸትን ተጠንቀቁ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦
﴿يا مَعشرَ التُّجّارِ ! إياكُم والكذبَ﴾

“እናንተ ነጋዴዎች ሆይ! ውሸትን ተጠንቀቁ!”

Telegram፦ https://t.me/ahmedin99
13.3K views07:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-09 20:24:20
ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من هجر أخاه سنةً، فهو كسفْكِ دَمِه﴾

“ወንድሙን አንድ አመት ያኮረፈ ደሙን እንዳፈሰሰው ነው።”

ሶሂህ አልጃሚዕ: 6581

Telegram፡‐ https://t.me/ahmedin99
12.8K views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-09 15:49:05
ተጠርጣሪው አልተያዘም!

ፖሊስ ተጠርጣሪ መሐመድ ሽኩር አለመያዙን አሰታወቀ


የአዲስ አበባ ፖሊስ ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው ሙሐመድ ሽኩር አለመያዙን ዛሬ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃን አያይዘናል።

"ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሐመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል። አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጣሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ።
***
ተጠርጣሪውን ለመያዝ ክትትሉ ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ እንደተያዘ ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ አዲስ አበባ ፖሊስ እየገለጸ መሐመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማነኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።
14.6K views12:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-07 12:10:10 ኪታባቸውን ተንተርሰው ወደቁ


በሳኡዲ የሸህ ኡሰይሚን ደረሳ የነበሩ፤ሱደይስን ተጅሪድ ያቀሩ ታላቁ ዓሊም ሀገር ውስጥ ከገቡ በኋላ በርካቶችን እያስተማሩ ነበር። አሁን አስኮ በድር መስጅድ ኸጢብ ከመሆናቸው በፊት አፍንጮ በር የሚገኘው አቅሷ መስጅድ ያቀሩ እንደነበር የሚታወቁት በነሲሀ ቲቪም ሲያስተምሩ ይታወቃሉ።

ትናንት ምሽት ኪታባቸውን ተንተርሰው ለልጃቸው የገዙትን ዳቦ በትነው የወደቁበት ቦታ ላይ የዳቦው ፌስታል በደም ጨቅይቶ አየነው። ከጀርባቸው ሲመቱ አይነ በሲሩን አረቡን ቤቱ እየሸኙት ነበር።

ወደ አረቡ ቤት አቅንተን የሆነው ሁሉ ሲቃ እየተናነቀው አጫወተን። አረቡ እንደነገረን ከመግሪብ እስከ ኢሻ ተፍሲር ሲያቀሩ አመሹ። ለዚያውም ሱረቱል ዙመርን ሲያብራሩ አመሹ።

ሁሌም እንደሚያደርጉት መስጅድ በር ላይ ሲዋክ የሚሸጠውን አይነ በሲሩን አረቡን ለመሸት ጠበቁት። አረቡ ሁሌ እንደሚያደርገው «ኡስታዝ አይጠብቁኝ ይሂዱ» ይላቸዋል። እሳቸው እሽ አይሉም። ከኢሻ በኋላ ለአረቡ ምርኩዝ ናቸው። እንጀራ አይበላም ለሚሉት ለልጃቸው ዳቦ ገዝተው አረቡን ቤቱ እየመሩ አስገብተው ነው ወደቤታቸው የሚገቡት።

ትናንትም አይነ በሲሩን አረቡን እየመሩ ወደቤታቸው ሲሄዱ መታጠፊያ አሳቻ ቦታ ላይ ከቅርብ ርቀት በተተኮሰ ሽጉጥ ከጀርባቸው በኩል ተመተው የወደቁ ሲሆን በወቅቱ አረቡም ራሱን ስቶ አብሮ ወድቆ ነበር። በተመቱበት ሰዓት በአካባቢው መብራት ጠፍቶ እንደነበርና ከወደቁ ከጥቂት ደቂቃዎች በኋላ መብራት መምጣቱን የአካባቢው ሰዎች ነግረውናል።

እዳ ያስጭንቃቸው እንደነበር እና በሽማግሌዎችም የተሰጣቸው ጊዜ አጭር በመሆኑ ያሳስባቸው እንደነበር የተወሰነውን ተበድረው ከፍለው ቀሪውን ለመክፈል ቤታቸውን ለመሸጥ እንዳሰቡ ነገር ግን የበድር መስጅድ ጀመዓዎች ቤቱ ከመሸጡ በፊት ትላንት ፈጅር ላይ ለመስጅድ ጀመአ ዛሬ እሁድ ገቢ ለማሰባሰብ እቅድ ተይዞ እንደነበር ነገሩን።

እናንተ የአላህ ባሮች ኢማማችንን ሸኻችንን ከየቲም ልጆቻቸው ጋር እና ከእዳቸው ጋር ለኛ ትተው ተገድለዋል።

ከቀብራቸው በፊት እዳ ለመክፈል እየተንቀሳቀሱ ያሉ ኮሚቴዎች አካውንት የከፈቱና የገለጹ ስለሆነ ፖሊስ ገዳዩን አጣርቶ ለህዝብ ይፋ እስኪያደርግ የመስጅድ ኢማም እንደመሆናቸው መጠን መጅሊስ በቅርብ ርቀት ዜናው ከተሰማበት አንስቶ ከሚመለከተው አካል ጋር ሲከታተል እንደነበረው ሁሉ ማህበረሰቡም ደግሞ እዳውን እንዲከፍል ጥሪ ቀርቧል።

የኢማማችን ባለቤት በቅርብ ጊዜ ወደ አኸራ የተሻገሩ በመሆኑ የቤቱ አስተዳዳሪ አባት ሸይኽ አላህ ይዘንላቸው ያለውን ክፍተት እንሙላ።

አስተባባሪ ኮሚቴ ስም የተከፈለ የሂሳብ አካውንት


የአካውንት ስም:- ጀሚል ሁሴን ፣ ሲሩ ሀሰን እና አብዱ ዑስማን
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ:- 1000592716309
14.6K views09:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-07 09:06:22 ሸይኽ አብዱ ያሲን ጀናዛቸው በዛሬው እለት በአስኮ በድር መስጂድ ተሰግዶበት ከዙሁር ሀኋላ በኮልፌ መካነ መቃብር የሚቀበሩ ይሆናል!
--------------
ሌሊቱን ለምርመራ ጳውሎስ የቆየው ጀናዛቸው ዛሬ እሁድ ጠዋት ወጥቶ አወሊያ ላይ እየተከፈነ ይገኛል!!

በአላህ ፈቃድ በአስኮ አዲስ ሰፈር በድር መስጂድ ዙሁር ላይ ተሰግዶበት የቀብር ስነስርአቱ ደግሞ ከዙሁር በኋላ በኮልፌ መካነ መቃብር እንደሚሆን የአካባቢው ሰዎች ገልፀዋል!!

የቻላችሁ ሰዎች ቦታው በመገኘት እንድትሸኙ እናሳስባለን!!

ረሂመሁላሁ ረህመተን ዋሲዓ

Huda multimedia
14.1K views06:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-07 00:48:44
ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን
እኛ የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን!


በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በአስኮ አዲስ ሰፈር የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ከዒሻ ሰላት በኃላ ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ወደ አኼራ ሄደዋል::

መንግስትና ባለድርሻ አካላትም አስቸኳይ የማጣራት ተግባር በማድረግ የኢማሙን ገዳይ ለሕግ እንዲያቀርቡ እንዲሁም ህብረተሰቡ የጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ምርመራ አጋዥ ሊሆን የሚችል መረጃ በማቀበል የኢማሙ ገዳዮች እንዲታወቁ ለህግ እንዲቀርቡ የበከሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።


አሳዛኝ እና አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ኢማም ሼይኽ አብዱ ያሲን አላህ እንዲምራቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ እንዲያደርግላቸው፣ የሸሂድነትን ማዕረግም እንዲያጎናፅፋቸው እንዲሁም ለቤተሰባቸውና ለመላው ሙስሊም ማህበረስሰብ መፅናናትን እንዲሰጥ አላህን እንለምነዋለን።
13.9K views21:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-05 13:32:29
በነቢዩ ሙሀመድ [ﷺ] ላይ ሰለዋት ሲያደርጉ ሀጥያት እንደሚራገፍልዎ ያውቃሉ?

የአላህ መልዕክተኛ(ሰዓወ) እንዲህ ብለዋል:–

"በኔ ላይ አንዴ ሰለዋትን ላወረደ አላህ በሱ ላይ አስር ሰለዋትን ያወርድበታል። አስር ኃጥያቶችንም ያራግፍለታል።"

"Namni anarrattii salawaata tokko buuse Rabbiin isarratti salawaata kudhan buusa. Badii kudhan isaaf dhiisa."

Nabi Muhammad(saw)
16.4K views10:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-04 20:52:31
“ነገር አዋሳጅ ጀነት አይገባም።” ረሱል (ﷺ)

ሙስሊም ዘግበውታል: 105

ቴሌግራም:- T.me/ahmedin99
14.3K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2024-01-02 21:40:17
በማይመለከትህ ጉዳይ አትግባ!

ረሱል (ﷺ) እንዲህ ብለዋል፦

﴿من حُسنِ إسلامِ المرءِ تركُه ما لا يَعْنيه.﴾

“የአንድ ሰው ከእስልምናው ማማር የማይመለከተውን ነገር መተዉ ነው።”

ቲርሚዚ ሀሰን ብለውታል: 2317

ቴሌግራም፦ https://t.me/ahmedin99
15.9K views18:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ