Get Mystery Box with random crypto!

ተጠርጣሪው አልተያዘም! ፖሊስ ተጠርጣሪ መሐመድ ሽኩር አለመያዙን አሰታወቀ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ተጠርጣሪው አልተያዘም!

ፖሊስ ተጠርጣሪ መሐመድ ሽኩር አለመያዙን አሰታወቀ


የአዲስ አበባ ፖሊስ ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው ሙሐመድ ሽኩር አለመያዙን ዛሬ ባወጣው ዘገባ አስታውቋል። የአዲስ አበባ ፖሊስ መረጃን አያይዘናል።

"ሼህ አብዱ ያሲንን በመግደል የሚጠረጠረው መሐመድ ሽኩር አበባው በቁጥጥር ስር ለማዋል ፖሊስ ክትትሉን አጠናክሮ ቀጥሏል። አንዳንድ ማህበራዊ ሚዲያዎች ተጠርጣሪው እንደተያዘ በማስመሰል የሚያሰራጩት መረጃ ሀሰተኛ መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል ።
***
ተጠርጣሪውን ለመያዝ ክትትሉ ቀጥሏል፡፡ ነገር ግን ግለሰቡ እንደተያዘ ተደርጎ የተሰራጨው መረጃ ሀሰት መሆኑን አዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ተጠርጣሪው ሳይያዝ እንደተያዘ አድርጎ መረጃ ማሰራጨት ተገቢ እንዳልሆነ አዲስ አበባ ፖሊስ እየገለጸ መሐመድ ሽኩር አበባው ያለበትን የሚያውቅም ሆነ ማነኛውም መረጃ ያለው በስልክ ቁጥር 011-1-11-01-11 ወይም በነፃ ስልክ ቁጥር 991 መረጃ በመስጠት ትብብር እንዲደረግ ጥሪ አቅርቧል።