Get Mystery Box with random crypto!

Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

የሰርጥ አድራሻ: @ahmedin99
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 60.07K
የሰርጥ መግለጫ

ይህ ይፋዊ የአሕመዲን ጀበል የቴሌግራም ገፅ ነው!

Ratings & Reviews

2.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

0

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-12-28 20:23:56

15.9K views17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-27 21:04:01
ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ): - ሚሊዮነሩ ነብይ!

ነገ ሀሙስ ምሽት በ2:00 ላይ በአሕመዲን ጀበል የቱቲቱብ ቻናል ላይ ይከታተሉ። የቻናሉን አድራሻ ከሥር ያገኙታል።



16.9K viewsedited  18:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-26 10:36:12
15.4K views07:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-25 21:07:17

14.1K views18:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-23 08:34:51 “በረመዳን ብቻ ሳይሆን በዘውትር ቀናቶችም በተለይ ወጣቱ መስጂዶችን ሞልቶ የጀምዓ ሰላት እንደሚሰግድ ታዝቢያለው። " ሸይኽ ተውፊቅ ሳይግ


ባሳለፍነው ሳምንት የሀበሻን ምድር የጎበኙት እና በፍልውሃ ተውፊቅ መስጂድ ተገኝተው በሚደንቅ የንግግር ስልታቸው ስለ ሀበሻ የጁምዓ ኹጥባ ያቀረቡልን ሼይኽ ቶውፊቅ ሳይግ ወደሚኖሩበት ሀገር ተመልሰው በዛሬው ጁምዓም የሀበሻን ታላቅነት በሚንበራቸው ላይ ሆነው በኹጥባቸው አወድሰዋል:: በጉብኝታቸው ወቅት ከመጅሊሱ የተሰጣቸውን አማናም ለህዝባቸው አድርሰዋል::

በትናንትናው የጁምዓ ኹጥባቸው ከመካ ቀጥሎ ኢስላምን በመቀበል ቀዳሚ ስለሆነችው የሀበሻ ምድር የገለፁ ሲሆን ስደተኞችን ተቀብሎ ጥበቃ በማድረግ ቀዳሚ መሆን ስለቻሉት ስለ ንጉስ ነጃሺ ፍትሀዊነት በሰፊው በኹጥባቸው አቅርበዋል:: ስለ ሀበሻዊው ቢላልም ለምዕመናኑ አስታውሰዋል::

ኢትዮጵያዊያን ሙስሊሞች በአፄ ሐይለስላሴ ዘመን ይደርስባቸው የነበሩ ጭቆናዎችን በወፍ በረር በማንሳት ሙስሊሙ ለነፃነቱ አደባባይ በመውጣት የአፄው ስርዓት ፍፃሜ እንዲሆን እና ሀይማኖታዊ መብታቸው እንዲከበር ትግል ሲያደርጉ እንደነበር በኹጥባቸው አቅርበዋል::

ከአፄ ሀይለስላሴ ቡኃላም የሙስሊሙን ሁኔታ በማውሳት በተለይም የኢህአዴግ መንግስት በመጅሊሱ ውስጥ ጣልቃ በመግባት የፈፀመውን የመከፋፈል፣ ሙስሊሞችን እና ኡስታዞችን የማሰር ዘመቻውን አንስተዋል::

አሁም ያለው በዶ/ር አብይ አሕመድ የሚመራው መንግስት ወደ ስልጣን ከመጣ ወዲህ መጅሊሱ ከተራ የእርዳታ ድርጅት ፈቃድ ወጥቶ በአዋጅ እንዲቋቋም ማድረጉን፣ በፊት ላይ መጅሊሱ ከየትኛውም የውጪ አካል ጋር በቀጥታ መገናኘት የማይፈቀድለት መሆኑን እንደምሳሌ በማንሳት አሁን ግን ተቋሙ በተጎናፀፈው ህጋዊ ሰውነት ምክንያት ከተለያዩ ኢስላማዊ ሀገራት እና ተቋማት ጋር ግንኙነት ማድረግ መጀመሩን ገልፀዋል:: ይህን ተከትሎም የአለም ሙስሊሞች ሊግም የፍትሃዊ ንጉሱን ነጃሺ ስም የሚያስታውስ ታላቅ መስጂድ እና መርከዝ ሊገነባ መሆኑን ተናግረዋል::

በትናንቱ ኹጥባቸው ባሳለፉት ሳምንት የሀበሻን ምድር በአካል ሄደው መጎብኘታቸውን እና የሙስሊሞች ሀገር ከሚባሉት በላይ ኢስላማዊ ገፅታዎችን መመልከታቸውን ገልፀዋል:: የመሳጂዶች ብዛት ፣ በረመዳን ብቻ ሳይሆን በዘውትር ቀናቶችም በተለይ ወጣቱ መስጂዶችን ሞልቶ የጀምዓ ሰላት እንደሚሰግድ የታዘቡትን አካፍለዋል::

በጁምዓ ኹጥባቸው ላይ ከላይ የዘረዘሩትን ሃሳብ በዛሬው ኹጥባቸው ላይ ያነሱበትን ምክንያት የዘረዘሩ ሲሆን ከነዚህም መካከል:-

የመጀመሪያው ምክንያት መላው ሙስሊም በሀበሻ ላይ ባለዕዳ መሆኑን፣ ይህም ዕዳ የአላህ መልዕክተኛን(ሰዓወ) አደራ በመጠበቅ የሳቸውን ቤተሰቦች እና ሰሀቦች ያስጠለለች ሀገር በመሆኗ፣ የመልዕክተኛው(ሰዓወ) የመሰከሩላት የፍትሃዊው ንጉስ ሀገር በመሆኗ መሆኑን በመግለፅ ሀበሾች በእኛ ላይ ሀቅ አላቸው ብለዋል

በሁለተኛነት ጌታችን አላህ(ሱወ) ይህ ኡማ አንድ ህዝብ ነው ባለው መሰረት ፣በሀዲስም የአንዱ ሙስሊም ጭንቀት፣ ችግር እና ሀሳብ ያላስጨነቀው ከእኛ አይደለም በተባለው መሰረት ስለሀበሾች ሁኔታ መስማት መከታተል ስለሚያስፈግ መሆኑም

በሶስተኝነት ትውልዱ የሙሽሪኮችን ሀገር ይበልጥ እያወቀ የራሱን ሀገር ለትውልድ ማስተማሩን በመዘንጋቱ ይበልጥ ስለሀበሻ ማሳወቅ አስፈላጊ በመሆኑ እና

በአራተኛነትም የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ለመላው የአረቡ አለም ሙስሊሞች እንዲያደርሱላቸው የጣሉባቸው አማና ስላለም መሆኑን ጠቅሰዋል::

ይህም የአደራ መልዕክት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች መሳጂዶችን ፣መድረሳዎችን፣ ትምህርት ቤቶችን የሚገነቡላቸው ፣ የዲን መፅሀፍቶችን፣ ቁርኣኖችን እና ሰብዓዊ ድጋፎችን ይበልጥ በብዛት የሚልክላቸው አካል እንደሚያስፈልጋቸው በመግለፅ ሙስሊሙ በሙሉ ጫንቃው ላይ ያለውን የሀበሻ ዕዳ ለመክፈል የሚፈልጉትን በሟሟላት እና ከጎናቸው መቆም እንዳለበት ጥሪ በማቅረብ ኹጥባቸውን በዱዓ ቋጭተዋል::

ሙሉውን የሼይኹን ኹጥባ መልዕክት በሚከተለው ሊንክ ያገኙታል



16.7K views05:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-20 21:15:56 ሂጅራ ባንክ ስንት አተረፈ?





16.4K views18:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-18 09:38:08
"አንድ አማኝ ለሌላው አማኝ እንደ ግንብ ክፍሎች ነው። አንዱ ሌላውን ይጠግናል(ያጠነክራል)"

የአላህ መልዕክተኛ [ﷺ]
16.6K views06:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-17 20:31:29

16.6K views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-13 19:10:06
ዛውያ 2020 የናንተን ሀሳብ ይፈልጋል


ዛውያ ቲቪ ለስርጭት ከበቃ 6 ዓመታትን አስቆጥሯል፡፡ ባሳለፍናቸው 6 ዓመታት በሙስሊሙ የደስታም ይሁን የሀዘን ጊዜያት ግንባር ቀደም ተሰላፊ በመሆን የተቋቋመለትን አላማ ለማሳካት በብዙ ወጣ ውረዶች ውስጥ አልፏል፡፡ እነሆ 6ኛ አመታችን ላይ ቆመን ወደ ፊት አሻግረን በመመልከት ላይ እንገኛለን፡፡ የቀጣይ 5 ዓመታት ራእያችንንም ዛውያ2020 ስንል ሰይመነዋል፡፡ እናንተም ውድ የክብር አባሎቻችን እና ተከታታዮቻችን ለዚህ ራእይ ስንቅ ይሆነን ዘንድ ከዛውያ ጋር ያሳለፋችሁትን 6 ዓመታት ዞር ብላችሁ በመመልከት ሀሳባችሁን እንድታካፍሉን፣ ከፊታችን ያሉትን 5 ዓመታት ደግሞ በሰውኛ አይን አይታችሁ ስለ ዛውያ ያላችሁን ራእይ እንድታጋሩን ስንል በአላህ ስም ጠየቅናችሁ፡፡
የጎግል ፎርም ሊንኩን በመጠቀም የተዘጋጁትን ቀላል መጠይቆች በመሙላት ይላኩልን:: እናመሰግናለን

https://docs.google.com/forms/d/e/1FAIpQLSdGs2rR_hWfxQVx8rVxHUCyN6-SuCnqZ3PXLT0mJjEG86AgBQ/viewform
14.3K views16:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-12-10 20:05:50

16.5K views17:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ