Get Mystery Box with random crypto!

ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን እኛ የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን! | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ኢና ሊላሂ ወዒና ኢለይሂ ራጂዑን
እኛ የአላህ ነን ወደሱም ተመላሾች ነን!


በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 በአስኮ አዲስ ሰፈር የበድር መስጂድ ኢማምና ኸጢብ እንዲሁም በመስጂዱ የተለያዩ ኪታቦችን በማቅራት የሚታወቁት አቅሪ ሸይኽ አብዱ ያሲን ዛሬ ቅዳሜ ምሽት ከዒሻ ሰላት በኃላ ባልታወቁ ሰዎች በተተኮሰባቸው ጥይት ተመተው ወደ አኼራ ሄደዋል::

መንግስትና ባለድርሻ አካላትም አስቸኳይ የማጣራት ተግባር በማድረግ የኢማሙን ገዳይ ለሕግ እንዲያቀርቡ እንዲሁም ህብረተሰቡ የጸጥታ አካላት ለሚያደርጉት ምርመራ አጋዥ ሊሆን የሚችል መረጃ በማቀበል የኢማሙ ገዳዮች እንዲታወቁ ለህግ እንዲቀርቡ የበከሉን ሚና እንዲወጣ ጥሪዬን አቀርባለሁ።


አሳዛኝ እና አስደንጋጭ በሆነ ሁኔታ ህይወታቸውን ላጡት ኢማም ሼይኽ አብዱ ያሲን አላህ እንዲምራቸው፣ ማረፊያቸውንም በጀነተል ፊርዶስ እንዲያደርግላቸው፣ የሸሂድነትን ማዕረግም እንዲያጎናፅፋቸው እንዲሁም ለቤተሰባቸውና ለመላው ሙስሊም ማህበረስሰብ መፅናናትን እንዲሰጥ አላህን እንለምነዋለን።