Get Mystery Box with random crypto!

በዚህ አመት ሀጅ ማድረግ ያልቻላችሁ ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡- አራፋ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

በዚህ አመት ሀጅ ማድረግ ያልቻላችሁ ኢብኑ ረጀብ አላህ ይዘንላቸውና እንዲህ ብለዋል፡-

አራፋ ተራራ ላይ የመቆም እድል ያላገኘ፣በሚያውቀው የአምላኩ ወሰን ላይ ታቅቦ ይቁም።

በሙዝደሊፋም ማደር ያልቻለ ሰው እሱ ዘንድ ይቃረብበት ዘንድ ለአምላኩ ታዘዥ ሆኖ ይደር።

ስጦታንም በሚና ማረድ ያልቻለው ሰው ለአምላኩ ሲል ፍላጎቱን ይረድ(ዝንባሌውን ይቃረን)።

ወደ ቤቱ (ከዕባ) ድረስ በርቀት ምክንያት መድረስ ያልቻለም ከደም ስሩ ቅርብ ወደ ሆነው የቤቱ ጌታ ዘንድ ይከጅል!"

(ኢብኑ ረጀብ ሊጣኢፍ አል-ማዓረፍ ገፅ 633)