Get Mystery Box with random crypto!

ብርቅዬ 13 ዓመታት – ኑር ኢስላሚክ ሴንተር . ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በካሪኩለንም በመታገ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ብርቅዬ 13 ዓመታት – ኑር ኢስላሚክ ሴንተር
.
ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን በካሪኩለንም በመታገዝ በቁርዓን ፣ በሂፍዝ ፣ በሀዲስ ፣ በፊቅሂ ፣ በተጅዊድ ፣ በነህውና በሌሎች ኢስላማዊ ዘርፎች እያፈሩ 13 ዓመታትን ተሻግረዋል።

ኢስላማዊ ተቋማት እምብዛም ባልነበሩበትና ባልታወቁበት ፣ በጊዜው በነበሩ የአገዛዝ ስርዓቶች የሚደርሱ ችግሮችንና ተግዳሮቶችን በማለፍ በአላህ ችሮታ ለዛሬ በቅተዋል። ከዲናዊ እውቀት ባሻገር ለተማሪዎች የቲቶርር እገዛዎችን በማድረግ ፣ የማንበቢያ ላይበረሪዎችን በማመቻትና ሪፈረንሶችን በማቅረብ በትምህርታቸው የበቁ በጥሩ ውጤት ወደ ውጭ ሀገር ሄደው የሚማሩና በሀገራችን በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በጀምዓ አሚርነት እያገለገሉ የሚገኙ ወጣቶችን አፍርተዋል።

ትውልዱ ካለበት የእውቀት ክፍተት ባሻገር ያሉብንን የማህበራዊ ሀላፊነቶች ለመወጣት እልፍ አይታሞችን ተንከባክበው አሳድገዋል። ብዙ ባላቸው የሞተባቸውን የቲም የሚያሳድጉ እህቶችን ቋሚ የስራ ዕድል በማመቻት ደግፈናል። የምስኪን እናቶች የፈረሱ ቤቶችን እንደአዲስ ገንብተዋል።
.
ዛሬ ላይ ኑር ኢስላሚክ ሴንተር ከ410 በላይ ታዳጊ ህፃናትንና ወጣቶችን ይዞ በዲናዊ እውቀት ለማነፅና በትምህርታቸው የበቁ እንዲሆኑ ለማስቻል እየሰራ የሚገኝ ኢስላማዊ ተቋም ነው።
.
ኑር ኢስላሚክ ሴንተር በእነዚህ ብርቅዬ 13 ዓመታት በነበሩን የጉዞ ሂደቶች ያገዙን አካላትን ሊያመሰግን ፣ ከዚህ በፊት ከሚሰራው ስራዎቹ ባሻገር ሌሎች ትልሞችን ሰንቆ ወደ ላቀ ቀጣይ ምዕራፍ መሻገሩን ሊያበስር ነገ ጁምዓ የካቲት 29 በሸራተን አዲስ ሆቴል በአላህ ፍቃድ ደማቅ ፕሮግራም አሰናድቶ ቀጠሮ ይዘናል።
.
#ብርቅዬ_13_ዓመታት

#ለተሻለ_ትውልድ