Get Mystery Box with random crypto!

ስንቶች እየተመኙት ያላገኙትን እድል አገኘን። ወዳጆቻችን ቀብር ውስጥ ክንዳቸውን ተንተርሰዋል። እኛ | Ahmedin Jebel - አሕመዲን ጀበል

ስንቶች እየተመኙት ያላገኙትን እድል አገኘን። ወዳጆቻችን ቀብር ውስጥ ክንዳቸውን ተንተርሰዋል። እኛ ግን ይኸው አለን።ረመዳንን ደርሰን። ይህ መታደል ነውና አመስግኑ። የአላህ ችሮታ ነውና ተደሰቱ። ከዚህስ በላይ መታደል አለን? “አልሀምዱሊላህ” በሉ። በደስታ እንግዳችሁን አክብሩ። ክብሩን ጠብቃችሁ አስተናግዱት። ይሄ እንግዳ ጀነታችሁ ነው። ከእሳት መድህናችሁ ነው። ሽልማታችሁ ነው። ምሽጋችሁ ነው። ጋሻችሁ ነው። ያደረግንለትን አቀባበል ነገ አላህ ፊት የሚመሰክረው እንግዳችን ከኛ ጋር በእንግድነት የሚቆየው ጥቂት ቀናትን ነውና ሐቁን ጠብቁለት።