Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-19 09:10:04
የውጭ ጣልቃ ገብነት ያለበት የሱዳን ግጭት እንዲሁም የኢትዮጵያ እና ኤርትራ ዜጎች በሱዳን ጉዳይ - ያማረ ዱካ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd
937 views06:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 19:43:06 ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ግጭት የማንነት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ሰግተዋል

ባለፈው ቅዳሜ ለተነሳው የሱዳን ግጭት “የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት ጣልቃ ገብነት አለበት” በሚል እየተወራ መሆኑን ተከትሎ የሃገራቱ ዜጎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

በካርቱም ከተማ ጅሬፍ በተባለው አካባቢ ነዋሪ የሆንችው ኢትዮጵያዊት ኤዶም ንጉሴ (ስሟ የተቀየረ)  ቃለ-መጠይቁን እየሰጠችን ባለችበት ወቅት እንኳን በቅርብ ርቀት የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማት ትናገራለች።

ከወራት በፊት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አቅራቢያ አል-ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሱዳን ወታደሮች ተገድለዋል በሚል በሱዳናዊያን ዘንድ "እኛ እያኖርናችሁ መንግስታችሁ ወታደሮቻችንን ይገድላል" የሚል ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ላይ መድረሱን የመረጃ ምንጫችን ታስታውሳለች።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/current-affairs-am/Ethiopians-are-afraid-of-being-attacked-in-the-Sudanese-conflict
1.3K views16:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 14:04:19
በዚህ ሳምንት በ Startup Corner!!!

ቤት ለመከራየት በየሰፈሩ መንከራተት እና የደላላን እንግልት የሚያስቀረውን "ቤቶት" መተግበሪያ ሰርቶ ወደ ቢዝነስ የገባው ወጣት ኑርሁሴን መሀመድ ጋር ቆይታ ይኖረናል ፡፡

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd፦
470 views11:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 09:57:53
በዚህ ሳምንት በ Startup Corner!!!

ቤት ለመከራየት በየሰፈሩ መንከራተት እና የደላላን እንግልት የሚያስቀረውን "ቤቶት" መተግበሪያ ሰርቶ ወደ ቢዝነስ የገባው ወጣት ኑርሁሴን መሀመድ ጋር ቆይታ ይኖረናል ፡፡

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd፦
730 views06:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 19:51:42 Five Ethiopians killed and Nine more injured, amid crisis in Sudan worsens

Read more - https://addiszeybe.com/featured/addis-ababa/politics/currentaffairs/five-ethiopians-killed-and-nine-more-injured-amid-crisis-in-sudan-worsens
523 viewsedited  16:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 16:24:09 5 ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ካርቱም በተነሳው ግጭት መገደላቸው ተገለፀ

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ግጭት ሳቢያ አምስት ኢትዮጵያውያን መሞታቸው እና ቢያንስ ዘጠኝ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን መቁሰላቸው ታወቀ።

በመሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና በጀነራል አብዱልፈታል አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ጦር መካከል በካርቱም እያካሄዱት ባለው ውጊያ ሳቢያ ነው የአምስት ኢትዮጵያዊያን ሞት የተሰማው።

የካርቱም ነዋሪ የሆኑት የአዲስ ዘይቤ ምንጮች እንደገለፁት ጦርነቱ እየተስፋፋና በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ መሆኑ ጉዳቱ እንዲጨምር አድርጓል። ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሚኖሩበት እና "ዴም" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በተደረገ ጦርነት ሦስት ኢትዮጵያን መሞታቸውን የገለጹት የመረጃ ምንጩ አደጋው የደረሰው ጠዋት ቢሆንም የሟቾች ቀብር አለመፈጸሙን ገልጸው፣ የሟቾች አስክሬን በአካባቢው አል-ጃውዳ ሆስፒታል እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/current-affairs-am/5-Ethiopians-were-killed-in-the-conflict-in-Khartoum-Sudan
830 views13:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-17 12:31:59 በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ዳውሮና ኮንታ ዞኖች ከመጋቢት 6/2015 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገልጿል።

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች የመብራት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀዉስ መዳረጋቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

ሁለቱንም ዞኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርገዉ እና በዳዉሮ ዞን የሚገኘው " አባ" የተባለዉ ትልቁ የኃልይ ማሰራጫ ጣቢያ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ብልሽት ምክንያት ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መሉ በሙሉ መቋረጡን ታውቋል ።

የዳዉሮ እና ኮንታ ዞን ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይልን የሚጠቀሙ እንደ ግንባታ፣ ማሽን፣ የእህል ወፍጮ ቤትና የመሣሠሉት ሥራዎች መቆማቸውን ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/hawassa/current-affairs-am/It-has-been-reported-that-there-has-been-a-power-outage-in-Daurona-and-Konta-zones-of-South-West-Ethiopia-since-March-6-2015
1.2K views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 17:05:15
አዲስ ዘይቤ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች ሁሉ መልካም የፋሲካ በአል ትመኛለች ፡፡
577 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 16:12:22
በካርቱም በተነሳው ግጭት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ

ሚያዝያ 7፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በካርቱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በአሁን ወቅት በአየር ማረፊያ እና የተለያዩ አካባቢዎች ተኩስ እየተሰማ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ ዘይቤ ገልፀው ውግያው መጠኑ እየጨመረ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከነብስ ወከፍ መሳሪያ ወደ ከባድ መሳሪያ መቀየሩን የገለፁት ምንጮቹ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸውም ገልፀዋል።

ከኢትዮጲያ ኤንባሲ በኩል የተደረገላቸው ድጋፍ እና የመረጃ እገዛ እንዳለ የጠየቅናቸው አስተያየት ሰጪዎች የአሜሪካ ኤንባሲ ለዜጎቹ ከሰጠው ማስጠንቀቂያ ውጪ ምንም የለም ብለዋል።

በአሁን ወቅት ካርቱም ውስጥ ከፍተኛ አለመረጋጋት መኖሩን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ጭምር እየዘገቡ ይገኛሉ።
686 views13:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 20:31:54
ፋሲካን ሽንኩርት ሳይከትፉ ፡ በርበሬ ሳያቁላሉ ፡ ዶሮ ሳይበለቱ ፡ ጥፍጥ ያለ ዶሮ ወጥ ቤትዎ ድረስ!!!

የኢትዮጵያዊት ቆንጆ ሞያ በጥራት በጥንቃቄ ተዘጋጅቶ ለትንሳኤ ይቅመሱ የበዓል ድካምና ሃሳቦን እኔ ላይ ጣሉ ብላችኋለች መልካም ፋሲካ!!!

Facebook page - https://www.facebook.com/profile.php?id=100091600037729&mibextid=ZbWKwL
716 views17:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ