Get Mystery Box with random crypto!

5 ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ካርቱም በተነሳው ግጭት መገደላቸው ተገለፀ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ሶ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

5 ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ካርቱም በተነሳው ግጭት መገደላቸው ተገለፀ

በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ሶስተኛ ቀኑን በያዘው ግጭት ሳቢያ አምስት ኢትዮጵያውያን መሞታቸው እና ቢያንስ ዘጠኝ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን መቁሰላቸው ታወቀ።

በመሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ በሚመራው የሱዳን የፈጥኖ ደራሽ ኃይል እና በጀነራል አብዱልፈታል አልቡርሃን በሚመራው የሱዳን ብሔራዊ ጦር መካከል በካርቱም እያካሄዱት ባለው ውጊያ ሳቢያ ነው የአምስት ኢትዮጵያዊያን ሞት የተሰማው።

የካርቱም ነዋሪ የሆኑት የአዲስ ዘይቤ ምንጮች እንደገለፁት ጦርነቱ እየተስፋፋና በከባድ መሳሪያ ጭምር የታገዘ መሆኑ ጉዳቱ እንዲጨምር አድርጓል። ኢትዮጵያዊያን በብዛት በሚኖሩበት እና "ዴም" ተብሎ በሚጠራ አካባቢ በተደረገ ጦርነት ሦስት ኢትዮጵያን መሞታቸውን የገለጹት የመረጃ ምንጩ አደጋው የደረሰው ጠዋት ቢሆንም የሟቾች ቀብር አለመፈጸሙን ገልጸው፣ የሟቾች አስክሬን በአካባቢው አል-ጃውዳ ሆስፒታል እንደሚገኝ ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/current-affairs-am/5-Ethiopians-were-killed-in-the-conflict-in-Khartoum-Sudan