Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ዳውሮና ኮንታ ዞኖች ከመጋቢት 6/2015 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ዳውሮና ኮንታ ዞኖች ከመጋቢት 6/2015 ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡ ተገልጿል።

በደቡብ ምእራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል ዳዉሮና ኮንታ ዞኖች የመብራት አገልግሎት ሙሉ በሙሉ በመቋረጡ ለኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ቀዉስ መዳረጋቸውን ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

ሁለቱንም ዞኖች የኤሌክትሪክ ኃይል ተጠቃሚ የሚያደርገዉ እና በዳዉሮ ዞን የሚገኘው " አባ" የተባለዉ ትልቁ የኃልይ ማሰራጫ ጣቢያ ላይ በደረሰ ከፍተኛ ብልሽት ምክንያት ከመጋቢት 6 ቀን 2015 ዓ.ም. ጀምሮ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መሉ በሙሉ መቋረጡን ታውቋል ።

የዳዉሮ እና ኮንታ ዞን ነዋሪዎች የኤሌክትሪክ ኃይልን የሚጠቀሙ እንደ ግንባታ፣ ማሽን፣ የእህል ወፍጮ ቤትና የመሣሠሉት ሥራዎች መቆማቸውን ገልጸዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/hawassa/current-affairs-am/It-has-been-reported-that-there-has-been-a-power-outage-in-Daurona-and-Konta-zones-of-South-West-Ethiopia-since-March-6-2015