Get Mystery Box with random crypto!

በካርቱም በተነሳው ግጭት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ ሚያዝያ 7፤ 20 | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በካርቱም በተነሳው ግጭት ኢትዮጵያዊያን ስደተኞች ስጋት ውስጥ መግባታቸውን ገለጹ

ሚያዝያ 7፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) በካርቱም የኢትዮጵያ ማህበረሰብ በአሁን ወቅት በአየር ማረፊያ እና የተለያዩ አካባቢዎች ተኩስ እየተሰማ መሆኑን ምንጮች ለአዲስ ዘይቤ ገልፀው ውግያው መጠኑ እየጨመረ እንደሆነ ተናግረዋል።

ከነብስ ወከፍ መሳሪያ ወደ ከባድ መሳሪያ መቀየሩን የገለፁት ምንጮቹ ከፍተኛ ስጋት እንዳደረባቸውም ገልፀዋል።

ከኢትዮጲያ ኤንባሲ በኩል የተደረገላቸው ድጋፍ እና የመረጃ እገዛ እንዳለ የጠየቅናቸው አስተያየት ሰጪዎች የአሜሪካ ኤንባሲ ለዜጎቹ ከሰጠው ማስጠንቀቂያ ውጪ ምንም የለም ብለዋል።

በአሁን ወቅት ካርቱም ውስጥ ከፍተኛ አለመረጋጋት መኖሩን ዓለም አቀፍ ሚዲያዎችም ጭምር እየዘገቡ ይገኛሉ።