Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-14 18:22:26 ህውሓት ለኮረምና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መመደቡ ታወቀ

የኮረም እና አላማጣ አካባቢዎችን ለማስተዳደር የህወሓት ቡድን ለአካባቢዎቹ አመራር መድቦ የመከላከያ ሠራዊትን ከአካባቢው መውጣት እየተጠባበቀ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ከምንጮቿ አረጋግጣለች።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎች እና ኢ-መደበኛ ታጣቂዎችን ወደ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል እና የከተማ ፖሊስ ሆነው እንዲቀላቀሉ ባቀረበው ጥሪ ሳቢያ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላትና ፋኖዎች ጥሪውን ተቃዉመው መቆየታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባለፈ “ትጥቅ አንፈታም” ባሉ ታጣቂዎች እና መከላከያ ሰራዊት መካከል ተኩስ ተከፍቶ ነበር።

ይሁን እንጂ በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች እና በዙሪያው ሰፍረው የቆዩት በርካታ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የፋኖ ታጣቂዎች ከትጥቅ ፍቱ ጥሪ ጋር ተያይዞ ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ህውሓት ለአካባቢዎቹ አመራሮችን እንደመደበ አዲስ ዘይቤ ከትግራይ ክልል ህጋዊ ታጣቂ አባላት አረጋግጣለች።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/current-affairs-am/It-is-known-that-the-TPLF-has-been-assigned-the-leadership-of-Korum-and-Alamata-areas
945 views15:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-14 08:58:17
Startup Story - ሜድስቶር እንዴት ተጀመረ? ቢዝነሱ የሚፈታው ችግርስ ምንድነው? ቸርነት መኳንንት - Startup Corner

ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ

1.1K viewsedited  05:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 12:31:33 ታሪካዊው የድሬዳዋ አሸዋ ሜዳ በቆሻሻ መሞላት በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጠረ

በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የአሸዋ ሜዳ ታሪኩን በማይመጥን ቆሻሻ መሞላቱ ነዋሪዎች ላይ ቅሬታ ፈጥሯል። የከተማው ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ሜዳው አሁን ላይ በቀላሉ ማፅደት ወደማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጿል።

ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ በአፍሪካ ግዙፍ መደበኛ ውድድሮች ወይም በፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ የመጀመሪያዋ ሴት አሰልጣኝ ናት። ኢንስትራክተር መሠረት እስካሁን በስፖርቱ ዓለም ያገኛቻቸው ስኬቶች መነሻ ይኸው ታሪካዊ የአሸዋ ሜዳ መሆኑን ትናገራለች።

ላገኘችው ዝናና ክብር ያበቃት አሸዋ ሜዳ አሁን ላይ በቆሻሻ ተሞልቶ መመልከቷ እንደሚያሰቆጫት ለአዲስ ዘይቤ የተናገረችው ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ፣ የሚመለከተው አካል ቁጥጥር ማነስ እና የህብረተሰቡ የግንዛቤ እጥረት ለሜዳው ታሪክ መጠለሸት ምክንያት እንደሚሆኑ አስቀምጣለች።
https://am.addiszeybe.com/featured/dire-dawa/%E1%8C%A4%E1%8A%93/history/current-affairs-am/the-filling-of-the-historical-dredawa-sand-field-with-garbage-caused-complaints-among-the-residents
533 views09:31
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 11:32:46
የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች የውኃ ችግር እንዳጋጠማቸው ገለፁ

የውኃ ክፍል ሠራተኞች ወደ ጦርነት መሄዳቸውን ተከትሎ የባለሙያ እጥረት ማጋጠሙ ተጠቁሟል

ሚያዝያ 05፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ መቀሌ) በትግራይ ክልል በተለይም በመዲናዋ መቀሌ ከተማ የከፋ የንፁህ መጠጥ ውኃ እጥረት እየተቸገሩ መሆኑን የከተማዋ ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናገሩ። በችግሩ ሳቢያ ነዋሪዎች የምንጭ ውኃ ለመጠቀም የተገደዱ ሲሆን ይህም ለእንግልት፣ ላልተገባ ወጭ እና ለህመም መጋለጣቸውን ጠቁመዋል።

ወ/ሮ ሃረግ ይልማ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ናቸው፣ የምንጭ ውኃ ለመቅዳት ወረፋ እየጠበቁ ከአዲስ ዘይቤ ጋር ቆይታ አድርገዋል። “በውኃ እጥረት ምክንያት ትልቅ ችግር ደርሶብናል፤ ልጆች ይዘን ያለ ውኃ ቀናትን ማሣለፍ ከባድ ሆኖብናል” ሲሉ አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

የወ/ሮ ሃረግን ችግር የሚጋሩ በርካታ የመቀሌ ከተማ ነዋሪዎች ችግሩ የከፋ መሆኑን ጠቁመው የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲያፈላልግላቸው ለአዲስ ዘይቤ ቅሬታቸውን ገልፀዋል። አቶ ገብረዮሃንስ ወልደስላሴ የመቀሌ ከተማ ኩኋ ክፍለከተማ የውሃ አገልግሎት ኃላፊ ናቸው።

የውሃ አገልግሎት በሰፊው ችግር ውስጥ ነው የሚሉት ኃላፊው፣ የአገልግሎቱ ሰራተኞች ወደ ጦርነት በመግባታቸው የሰራተኛ እጥረት ማጋጠሙን ተናግረዋል። ከባለሙያ እጥረት ባለፈ ውኃ ሙሉ ለሙሉ ለማዳረስ የመሳሪያ ችግር መኖሩን ገልፀዋል።

ላለፉት ሁለት ዓመታት አገልግሎት ባይቋረጥም ሙሉ አገልግሎት ሳይሰጥ መቆየቱን የሚገልፁት አቶ ገብረዮሃንስ አሁን ላይ በአገልግሎት ሂደት ብልሽት ሲያጋጥም ለማስተካከል ብዙ ጊዜ እንደሚወስድ ይገልፃሉ። አሁን የተመሰረተው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር በዚህ ጉዳይ በሰፊው መስራት እንደሚገባው ኃላፍው ከአዲስ ዘይቤ ባደረጉት ቆይታ ተናግረዋል።
633 views08:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-13 07:52:29 Startups that are on the path to success or just starting out can offer valuable insights that even established companies may not have.

At Startup Corner, we focus on the startups that are facing real challenges, hopes, and work, as they navigate their journey towards success.

By observing these companies, you can better understand how to apply their lessons and experiences to your own business or personal ventures.


761 viewsedited  04:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 20:47:53 "ብአዴንን የአማራ ህዝብ ሊበላው ይችላል"- ያማረ ዱካ



517 views17:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 18:04:11
ልዩ ኃይል ይፈርሳል መባሉን ተከትሎ በሶማሌ ክልል ፊቅ ከተማ የተቃውሞ ሰልፍ ተካሄደ
ሚያዝያ 04፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ድሬዳዋ) በሶማሌ ክልል ኖጎብ ዞን በፊቅ ከተማ አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ሰልፈኞች ወደ አደባባይ በመውጣት የክልሉን ልዩ ኃይል መልሶ ለማደራጀት የተወሰነውን ውሳኔ ተቃውመዋል።

የሶማሌ ክልል ሚያዝያ 02 ቀን 2015 ዓ.ም ባካሄደው 12ኛው ምክር ቤት ጉባኤ የክልሉን ልዩ ኃይሎች መልሶ ለማደራጀት ያወጣውን ውሳኔ ማፅደቁን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፋ ኡመር በትዊተር ገጻቸው ማስፈራቸው ይታወሳል።

የልዩ ኃይሉ ቤተሰብ አባል ናቸው የተባሉት የፊቅ ከተማ ነዋሪዎች የክልሉ መንግስት የደረሰበት ውሳኔ ህይወታቸውን አደጋ ላይ የሚጥል በመሆኑ የሚቃወሙት መሆኑን አንዳንድ የሰልፋ ተሳታፊዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

ናዲያ ፋራ እና ዴቃ ያሲን (ስማቸው ተቀይሯል) የተባሉ ነዋሪዎች ልዩ ኃይሉ መልሶ ሲደራጅ አንድም አባል ከስራ እንደማይሰናበት፣ የደሞዝ መቀነስና እና ከማዕረግ ዝቅ የሚደረግ እንደማይኖር የዞኑ አስተዳደር በመግለፁ ሰልፉ በስምምነት ተበትኗል ብለዋል።

ጉዳዩን አስመልክተን የሶማሌ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮንና የዞኑን አስተዳዳሪዎች በስልክ ለመግኘት ያደረግነው ጥረት የሞባይል ስልካቸው ባለመነሳቱ ልናገኛቸው አልቻልንም፡፡
881 views15:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 17:24:26
ሀሳብዎን ያጋሩን!!!
የኢትዮጵያ የክልል ልዩ ኃይሎች መፍረስ አለባቸው ወይስ የለባቸውም?
869 views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 17:17:46
"ብአዴንን የአማራ ህዝብ ሊበላው ይችላል"- ያማረ ዱካ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd
850 views14:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-12 16:41:53 በአማራ ክልል ሁለት የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት መቁሰላቸው ታወቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አምቡላንስ ሾፌርና አዋላጅ ነርስ የሆኑ ሠራተኞች ላይ “ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች” ጥቃት ፈፅመዋል ብሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊክ ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት የሆነው 'ካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስስ'ም በተመሳሳይ ሁለት ሠራተኞቹ በታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል።

እሁድ ሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ቹኦል ቶንጊክ የተባለው የደህንነት ስራ አስኪያጅ እንዲሁም አማረ ክንደያ የተባለው የአሜሪካ ካቶሊክ እርዳታ ድርጅት ሹፌር በአማራ ክልል በድርጅቱ ተሽከርካሪ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ተገድለዋል ሲል ድርጅቱ በድረ ገፁ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ -
https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/%E1%8B%9C%E1%8A%93/politics-am/current-affairs-am/in-the-amhara-region-two-humanitarian-aid-workers-were-killed-and-two-others-were-injured
885 views13:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ