Get Mystery Box with random crypto!

በአማራ ክልል ሁለት የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት መቁሰላቸው ታወቀ የኢ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በአማራ ክልል ሁለት የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅት ሰራተኞች ሲገደሉ ሌሎች ሁለት መቁሰላቸው ታወቀ

የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር በአማራ ክልል የሰሜን ጎንደር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አምቡላንስ ሾፌርና አዋላጅ ነርስ የሆኑ ሠራተኞች ላይ “ማንነታቸው ያልታወቁ ታጣቂ ኃይሎች” ጥቃት ፈፅመዋል ብሏል። የዩናይትድ ስቴትስ የካቶሊክ ዓለም አቀፍ ተራድዖ ድርጅት የሆነው 'ካቶሊክ ሪሊፍ ሰርቪስስ'ም በተመሳሳይ ሁለት ሠራተኞቹ በታጣቂዎች መገደላቸውን አስታውቋል።

እሁድ ሚያዝያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ቹኦል ቶንጊክ የተባለው የደህንነት ስራ አስኪያጅ እንዲሁም አማረ ክንደያ የተባለው የአሜሪካ ካቶሊክ እርዳታ ድርጅት ሹፌር በአማራ ክልል በድርጅቱ ተሽከርካሪ ወደ አዲስ አበባ ሲመለሱ ተገድለዋል ሲል ድርጅቱ በድረ ገፁ አስታውቋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ -
https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/%E1%8B%9C%E1%8A%93/politics-am/current-affairs-am/in-the-amhara-region-two-humanitarian-aid-workers-were-killed-and-two-others-were-injured