Get Mystery Box with random crypto!

የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻን መበተን የአማራ ህዝብ ጥቃት እንዲፈፀምበት ማመቻቸት ነው ሲል ባ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻን መበተን የአማራ ህዝብ ጥቃት እንዲፈፀምበት ማመቻቸት ነው ሲል ባልደራስ ፓርቲ አስታወቀ

ሚያዝያ 04፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) "የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የአማራ ህዝብ ቀጣይ ጥቃት እንዲፈፀምበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የአማራን ልዩ ኃይል፣ ፋኖን እና ሚሊሻውን ለማፍረስ ቀን ከሌት እየባዘኑ ይገኛሉ" ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።

"በንፁሀን ህይወት ላይ የሚቆምሩ ፖለቲከኞች" ብሎ ፓርቲው የጠራቸው አካላት የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት ሀገሪቱን "መውጫ ወደሌለው መቀመቅ እያስገቧት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል" ሲል አሳስቧል።

ወቅታዊውን ሁኔታ "ትግል" ሲል የጠራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥቃት በመሰንዘር "ትግሉን ወደኋላ" መጎተት አይቻልም ሲል አስታውቋል።