Get Mystery Box with random crypto!

በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ ለዓመታት የቆየ ከፍተኛ የውሃ እጥረት አጋጥሟል ተባለ በደቡብ ጎንደር | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ ለዓመታት የቆየ ከፍተኛ የውሃ እጥረት አጋጥሟል ተባለ

በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ፣ መካነ እየሱስ ከተማ አስተዳደር እና የአንዳቤት ወረዳዎች ነዋሪዎች የተበከለ የምንጭና የወንዝ ውሃ መጠጣት ከጀመሩ ዓመታት እንዳስቆጠሩ ለአዲስ ዘይቤ ገለፁ።

ከ160 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርባት የእስቴ ወረዳ የውሃ ማማው ጉና ተራራ ስር ብትገኝም ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ እጥረት በመፈጠሩ ነዋሪዎች ቆሻሻ የምንጭ እና ወራጅ ውሃ ከሌሊት 9 ሰዓት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወረፋ ጠብቀው በመቅዳት ለመጠጣት መገደዳቸውን ይናገራሉ።

በተመሳሳይ የአንዳቤት ወረዳ አንዳቤት ከተማ ነዋሪዎች በውሃ እጦት ከሁለት ዓመታት በላይ እንዳሳለፉና ነዋሪዎቹ ንፅህናው ያልተጠበቀ የምንጭና ወንዝ ውሃ እየተጠቀሙ በመሆናቸው ለበሽታ እየተዳረጉ እንደሆነም ነግረውናል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/gonder/current-affairs-am/it-is-said-that-there-has-been-a-severe-water-shortage-in-the-south-gondar-zone-for-years