Get Mystery Box with random crypto!

ታሪካዊው የድሬዳዋ አሸዋ ሜዳ በቆሻሻ መሞላት በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጠረ በድሬዳዋ ከተማ የሚገ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

ታሪካዊው የድሬዳዋ አሸዋ ሜዳ በቆሻሻ መሞላት በነዋሪዎች ዘንድ ቅሬታ ፈጠረ

በድሬዳዋ ከተማ የሚገኘው ታሪካዊው የአሸዋ ሜዳ ታሪኩን በማይመጥን ቆሻሻ መሞላቱ ነዋሪዎች ላይ ቅሬታ ፈጥሯል። የከተማው ፅዳትና ውበት ኤጀንሲ ሜዳው አሁን ላይ በቀላሉ ማፅደት ወደማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱን ገልጿል።

ኢንስትራክተር መሰረት ማኔ በአፍሪካ ግዙፍ መደበኛ ውድድሮች ወይም በፕሪምየር ሊግ ውድድር ላይ የመጀመሪያዋ ሴት አሰልጣኝ ናት። ኢንስትራክተር መሠረት እስካሁን በስፖርቱ ዓለም ያገኛቻቸው ስኬቶች መነሻ ይኸው ታሪካዊ የአሸዋ ሜዳ መሆኑን ትናገራለች።

ላገኘችው ዝናና ክብር ያበቃት አሸዋ ሜዳ አሁን ላይ በቆሻሻ ተሞልቶ መመልከቷ እንደሚያሰቆጫት ለአዲስ ዘይቤ የተናገረችው ኢንስትራክተር መሠረት ማኔ፣ የሚመለከተው አካል ቁጥጥር ማነስ እና የህብረተሰቡ የግንዛቤ እጥረት ለሜዳው ታሪክ መጠለሸት ምክንያት እንደሚሆኑ አስቀምጣለች።
https://am.addiszeybe.com/featured/dire-dawa/%E1%8C%A4%E1%8A%93/history/current-affairs-am/the-filling-of-the-historical-dredawa-sand-field-with-garbage-caused-complaints-among-the-residents