Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 11

2023-04-09 12:56:35 በክልል ልዩ ሃይል መፍረስ ላይ ህዝብ ሊመክርበት ይገባል- አስተያየት ሰጪዎች

የፌዴራል መንግስት የክልል ልዩ ሃይል አባላት ወደ መከላከያ ሰራዊት፣ ፌደራል ፖሊስ፣ መደበኛ ፖሊስ እና ሲቪል መሆን እንደሚችሉ ማስታወቁን ተከትሎ በአማራ ክልል ውጥረት ተከስቷል።

ከዚህ ውሳኔ ጋር በተገናኘ በአማራ ክልል በአንዳንድ አካባቢዎች መንገድ መዝጋትን ጨምሮ የተኩስ ልውውጦች መኖራቸውን ዘግበን ነበር። ከዚህ ጋር በተያያዘ አዲስ ዘይቤ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች አስተያየት ሰጪዎችን አነጋግራልች፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/gonder/%E1%8B%9C%E1%8A%93/politics-am/societal-issues/current-affairs-am/the-people-should-be-consulted-on-the-disbandment-of-regional-special-forces-commentators
685 views09:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 10:01:48
#አሁን

ጎንደር ከተማ ውስጥ ተደጋጋሚ የጥይት ተኩስ እየተሰማ ይገኛል

ሚያዚያ 1፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) ጎንደር ከተማ በዚህ ሰዓት ተደጋጋሚ የጥይት ተኩስ እየተሰማ ይገኛል።

ልዩ ኃይሎች በከተማው ውስጥ በተሽከርካሪዎች እየተዟዟሩ ጥይት በመተኮስ ላይ መሆናቸውን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገልፀዋል። የከተማው ነዋሪ ሰላማዊ ሰልፍ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።
818 views07:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 09:45:58 በጉራጌ ለሁለት ቀን የሚቆይ የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ሲምጡ የስራ ማቆም አድርጋችኋል በሚል የታሸጉ ሱቆች ዛሬ ለተጀመረው 5ኛ ዙር አድማ ምክንያት ሆኗል ተብሏል

ሚያዚያ 1፤ 2015 ዓ.ም.
(አዲስ ዘይቤ፤ ሐዋሳ) በጉራጌ ዞን ወልቂጤ ከተማ መንግስት በንግድ ድርጅቶች ላይ የወሰደዉን የማሸግ እርምጃ ተከትሎ ዛሬ ሚያዚያ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ለአምስተኛ ጊዜ የስራ ማቆም አድማ እየተደረገ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ወደ ወልቂጤ ከተማ መምጣታቸዉን ተከትሎ ለ4ኛ ጊዜ ተካሂዷል በተባለዉ የስራ ማቆም አድማ ላይ ተሳትፋችኋል በተባሉ ከ47 በላይ የንግድ ድርጅቶች መታሸጋቸው መደረጉን መቃወም ዛሬ ለአምስተኛ ጊዜ ለተጠራዉ አድማ ምክንያት መሆኑን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ገልፀዋል።

መደበኛ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴን ጨምሮ የንግድ ተቋማት ዝግ የተደረጉ ሲሆን የተወሰደው እርምጃ የማይቀለበስ ከሆነ አድማዉ ለሁለት ቀናት ይቆያል ሲሉም ተናግረዋል። በወልቂጤ ከተማ ነዋሪ የሆኑት የመረጃ ምንጮቻችን እንደተናገሩት የንግድ ድርጅቶች እንዲታሸግ ከመደረጉ በላይ ተመልሶ አገልግሎት ለመስጠት ከፈለጉ “ለምን እንደዘጉት ምክንያቱን ተናግረው ይቅርታ እንዲጠይቁና እስከ 50 ሺህ ብር የገንዘብ መቀጮ ክፍያ እንዲፈፅሙ” ተጠይቀናል ብለዋል።

ትላንት ቅዳሜ ምሽት ላይ በማህበራዊ ሚዲያ በተበተነ የስራ ማቆም አድማ እንዲደረግ በሚገልፅ የበራሪ ወቀቶች ላይ ዛሬን ጨምሮ ሁለት ቀን ይቆያል የተባለ ሲሆን ምንጮቻችንም ይህንን በማረጋገጥ "የተወሰደው እርምጃ ህገ ወጥ ነዉ፣ አግባብነት የለዉም" የሚል አቋም መያዛቸዉ ተነግሯል።

በወልቂጤ ከተማ ጨምሮ በሌሎች ወረዳዎች እና ከተማዎች ላይ በተደጋጋሚ እየተነሳ የሚገኘዉ የክልልነት ጥያቄዎች ይመለስልን በሚል የዛሬዉን ሳይጨምር ለ4ኛ ጊዜ ቤት ዉስጥ የመቀመጥና የስራ ማቆም አድማ ማድረጋቸዉ ይታወሳል።
823 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-09 09:45:56
758 views06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 17:02:41 በኢትዮጵያ በቅርቡ የሚጀምረው የመዋዕለ ነዋይ ገበያ (ካፒታል ማርኬት) ምንድን ነው? ኢትዮጵያንስ ይጠቅማል? - ፈራንካ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል እየተላለፈ ነው ፡ ይከታተሉን!!!





#capitalmarket #business #investment #finance #ethiopia
608 views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 12:46:35
በኢትዮጵያ በቅርቡ የሚጀምረው የመዋዕለ ነዋይ ገበያ (ካፒታል ማርኬት) ምንድን ነው? ኢትዮጵያንስ ይጠቅማል? - ፈራንካ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd

#capitalmarket #business #investment #finance #ethiopia
802 views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-08 08:13:44 "They are abusing me. They are insulting me. They are going to abduct me. I don't know where they are going to take me or what they are going to do to me"

Journalist Genet Asmamaw

Read more - https://addiszeybe.com/featured/addis-ababa/politics/news/currentaffairs/an-audio-recording-exposed-the-security-men-who-abducted-the-journalist-gent-asmamaw
62 views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 20:09:56 የአማራ ልዩ ኃይል ለምን ትጥቅ አይፈታም? - ያማረ ዱካ

ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ


674 views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 20:02:34 An audio recording exposed the security men who abducted the journalist, Gent Asmamaw

Journalist Genet Asmamaw, who was abducted by security men while she was at work at the Yeneta Media Office, exposed her abductors with a recorded audio of the incident on her phone at the time. 

The journalist called her family on the phone and heard that "about five security men in civilian clothes are trying to take me away, saying they want me. They are abusing me. They are insulting me. They are going to abduct me. I don't know where they are going to take me or what they are going to do to me, so tell me that I am kidnapped," she said to her family on the phone. 
Read more - https://addiszeybe.com/featured/addis-ababa/politics/news/currentaffairs/an-audio-recording-exposed-the-security-men-who-abducted-the-journalist-gent-asmamaw
689 views17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 19:55:16 ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ነገ በድጋሜ ወደ ጉራጌ ዞን በድጋሚ ያመራሉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ በወርሃ መጋቢት ለ2ኛ ጊዜ ከፌደራል እና ከክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ጋር በመሆን ወደ ደቡብ ክልል ጉራጌ ዞን ነገ ቅዳሜ መጋቢት 30 ቀን 2015 ዓ.ም. እንደሚሄዱ ምንጮች ለአዲስ ዘይቤ ገለፁ። 

ነገ በድጋሚ ወደ ዞኑ የሚያቀኑት ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዋናነት የጢያ ተክል ድንጋይ ፕሮጀክትን ለማስጀመር መሆኑም ተነግሯል። 

በተባበሩት መንግስታት የትምህርት ሳይንስና ባህል ተቋም (ዩኔስኮ) በ1972 ዓ.ም. በዓለም መካነ ቅርስነት የተመዘገበው የጢያ ትክል ድንጋይን ለማደስ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቅርብ ካሳተሙት "የመደመር ትዉልድ” መፅሐፋቸዉ በደቡብ ክልል ብቻ የሚሸጠዉን ገቢ ለፕሮጀክቱ እንዲዉል ማለታቸዉ ይታወሳል።
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/hawassa/politics-am/current-affairs-am/economy-am/prime-minister-abiy-ahmed-will-again-go-to-gurage-zone-tomorrow
861 views16:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ