Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 12

2023-04-07 17:56:16
የአማራ ልዩ ኃይል ለምን ትጥቅ አይፈታም? - ያማረ ዱካ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd
828 views14:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 17:07:03
በአማራ ክልል ደጀን ከተማ አካባቢ "መከላከያ ሠራዊት ወደአካባቢው ይመጣል" በሚል ነዋሪዎች መንገድ መዝጋታቸውን ከስፍራው ለአዲስ ዘይቤ የደረሱ የምስል መረጃዎች እና ነዋሪዎች ጠቁመዋል።
892 views14:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 15:48:01
በወልዲያ እና መርሳ ከተሞች መንገድ እና ተቋማት ተዘግተዋል፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ እና መርሳ ከተሞች መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 2 ስዓት ጀምሮ ተቋማት ተዘግተዋል፣ተሽከርካሪ በከተማዋ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል ሲሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናገሩ።

በከተማዋ የባንክ አገልግሎትን ጨምሮ ሁሉም የህዝብ መገልገያ ተቋማቶች እና የተሽከርካሪ መንገድ የተዘጋ ሲሆን በአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ፋኖ  ላይ ከመንግስት በወረደ ትዕዛዝ ትጥቅ ፍቱ ከመባሉ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ባለመስማማቱ እንዲዘጋ እንደተደረገ ነው ነዋሪዎች የገለፁት።

በትላንትናው እለት በከተማዋ ዙሪያ በምትገኜው ጎብየ ተብላ በምትጠራ አካባቢ በሁለቱ ሃይሎች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ተኩስ ገጥመው እንደነበር በመግለፅ ከዛሬ ጧት 2 ስዓት ጀምሮ የስራ ማቆም እና የመንገድ መዝጋት አድማ እያደረጉ እንደሆነ ተገልፇል ።
946 views12:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 15:19:02
ከ90 በላይ የውጭ ዜጎች በማእድን ማውጣት ስራ ተሰማርተው ተገኝተዋል ተባለ፡፡

በጋምቤላ ክልል በህገ ወጥ መንገድ ወርቅን ጨምሮ ማእድን ማውጣት ሰራ ላይ የተሰማሩ 45 የውጭ ሀገራት ዜጎች መያዛቸውን   የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ገለጸ፡፡

የኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ደኤታ ሰላማዊት ካሳ በሰጡት መግለጫ በክልሉ 3 ኢትዮጵያውያንም ተይዘዋል ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል 47 የውጭ ዜጎች ወርቅን ጨምሮ በማእድን ማውጣት ስራ ላይ ተሰማርተው ሲያዙ 9 የግል ማህበራትና 7 ኢትዮጵያውያንም በቁጥጥር ስር ስለመዋላቸው አንስተዋል፡፡

በመግለጫውም በአጠቃላይ 92 የውጭ ዜጎችና ሌሎች ኢትዮጵያውያን ከውጭ አካላት ጋር ትስስር በመፍጠር ሲመዘብሩ እንደነበር ሚኒስትር ደኤታዋ ተናግረዋል፡፡

የተያዙት አካላት የመኖሪያም ሆነ የመስሪያ ፈቃድ እንደሌላቸው ተጠቁሟል፡፡
892 views12:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 15:01:15
የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ በአገር ውስጥ በማምረት ሂደት ላይ 18 ፋብሪካዎች የተሳተፉ መሆኑን ገልጸው በዚህም 60 ሚሊዮን ዶላር የውጭ ምንዛሬ ማዳን መቻሉን የኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አስታወቀ ::
851 views12:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 12:27:26
#startupcorner #comingsoon
170 views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 11:44:04 Residents of Diredawa claims perils of flooding
In Dire Dawa city's ‘Ashewa meda’, near Kefira, the popular marketplace; a 27-year-old lady named Maimuna Yuye makes a living by selling tomatoes and potatoes. She alleges that the recent rains washed away three composting potatoes she had planned to sell for a week.

"The flood has swept me away. I am afraid that if the rain continues like this, it will cause a large flood and result in another disaster like the last one," Mr. Ziad Shelala, a resident who works in a stall shop selling used items, expressed his concern to Addis Zeybe.

Following the forecasted rainfall, the Mayor of Dire Dawa City Administration urges residents to be cautious and work together to mitigate, as there could be catastrophic harm to people and property.
Read more - https://addiszeybe.com/featured/dire-dawa/health/news/residents-of-diredawa-claims-perils-of-flooding
287 views08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-07 10:19:23 በጎንደር፣ ባህር ዳር እና ወልዲያ ከተማዎች ባለው ውጥረት የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጧል
በወልዲያ ከተማ ዙሪያ በቅርብ ርቀት በምትገኜው ጎብየ ተብላ በምትጠራ ቦታ በልዩ ሃይሎችና በሃገር መከላከያ ሰራዊት መካከል ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር ነዋሪዎች ገልፀዋል።

የፌደራል መንግስት “የየክልሉ ልዩ ኃይሎች ወደ ተለያዩ የፀጥታ መዋቅሮች እንዲገቡ የሚያስችላቸውን ተግባራዊ እንቅስቃሴ ማካሄድ” መጀምሩን ከመግለፁ አስቀድሞ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች ጉዳዩ ውጥረት ፈጥሯል።

ከትላንት ጀምሮ በይፋ እንደተጀመረ የተገለፀው የክልል ልዩ ኃይልን በማፍረስ ወደ ሌሎች የፀጥታ መዋቅሮች የማስገባት እንቅስቃሴ ከመጋቢት 28 ቀን 2015 ዓ.ም ጀምሮ በባህር ዳር፣ ጎንደር እና ወልዲያን ጨምሮ በተለያዩ አካባቢዎች ውጥረት መፍጠሩን አዲስ ዘይቤ ከነዋሪዎች ሰምታለች።

በዚህ ድርጊት የተነሳም በልዩ ኃይል አባላት እና በኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል አለመግባባት መፈጠሩ በአካባቢዎቹ ለተከሰተው ውጥረት መንስዔ ሆኗል ተብሏል።

በወልዲያ ከተማ ዙሪያ በቅርብ ርቀት በምትገኘው ጎብየ ተብላ በምትጠራ ቦታ ላይ በልዩ ኃይል አባላትና በሀገር መከላከያ ሠራዊት አባላት መካከል ተኩስ ተከፍቶ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ የገለፁ ሲሆን “ማረጋገጥ ባንችልም የሞቱ ሰዎች መኖራቸው እየተወራ ነው” ሲሉም ገልፀውልናል።
ዝርዝር ዘገባውን https://am.addiszeybe.com/featured/bahir-dar/politics-am/current-affairs-am/business-am/news-am/economy-am/due-to-the-tension-in-the-cities-of-gondar-bahr-dar-and-woldia-the-internet-service-has-been-cut-off
509 views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 17:27:34 የአክሱም ኤርፖርት መውደም ኑሯችንን አክብዶታል ሲሉ ነዋሪዎች ገለፁ

በሰሜን ኢትዮጵያ ክፍል በህወሓት እና በፌደራል መንግስቱ መካከል በነበረው ጦርነት የወደመው የአክሱም ከተማ አጼ ዮሃንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ አሁንም ወደ ስራ አልተመለሰም። ከጦርነቱ አስቀድሞ ከተማዋ ከቱሪዝም ከፍተኛ ገቢ ታገኝ የነበረ ሲሆን “አሁን ግን ሁሉም ነገር ቆሟል” ሲሉ አስተያየታቸውን ለአዲስ ዘይቤ የሰጡ ነዋሪዎች።

የአክሱም ከተማ ነዋሪዎችም በስፋት በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ኑሯቸውን የሚገፉት ስራ እና ሙያ ከሀገር ውስጥና ዓለም አቀፍ ጎብኚዎች ጋር የተቆራኘ በመሆኑ በአየር ማረፊያው መጎዳት በርካቶች ለከፋ የኢኮኖሚ ችግር ተጋልጠዋል።

የቀድሞ የአክሱም ከተማ የባህልና ቱሪዝም ባለሙያ አቶ ገብረመድህን ፍፁምብርሃን ለአዲስ ዘይቤ እንዳሉት “አውሮፕላን ማርፊያው ሙሉ በሙሉ በመውደሙ እና ወደ ስራ የሚመለስበት ተስፋም እስካሁን አለመታየቱ ነዋሪዎች ላይ ከፍተኛ ቅሬታ ፈጥሯል”።
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/current-affairs-am/business-am/news-am/economy-am/residents-said-that-the-destruction-of-aksum-airport-has-made-our-life-difficult
1.0K views14:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 17:05:25
ገዢው ፓርቲ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በግዴታ ትጥቅ ለማስፈታት ተንቀሳቅሷል ሲል አብን ወቀሰ

መጋቢት 28፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) ገዢው ብልፅግና ፓርቲ “የአማራ ክልል ልዩ ኃይልን በግዴታ ትጥቅ ለማስፈታት እንቅስቃሴው ውስጥ” ገብቷል ሲል የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ወቀሰ።

ፓርቲው ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የገዥው ፓርቲ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የክልል ልዩ ኃይሎችን አስመልክቶ ያሳለፈውን ውሳኔ” መቃወሙን አስታውሶ “ገዥው ፓርቲ ድርጅታችን የሰጠውን ማሳሳቢያ ወደ ጎን” ብሏል ሲል ገልጿል።

አዲስ ዘይቤ ምንጮቿን ዋቢ አድርጋ ዛሬ ረፋድ ላይ ከባህር ዳር ወደ ጎንደር የሚወሰደው መንገድ ላይ የክልሉ ልዩ ኃይል ካምፕ በቅርብ ርቀት በሚገኝበት ስፍራ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊት መዘጋቱን መዘገቧ ይታወሳል።

የመንግስትን እንቅስቃሴ ተከትሎ በአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በክልሉ ልዩ ኃይል እና በፌዴራል የፀጥታ ተቋማት መካከል ከፍተኛ ውጥረት መፈጠሩን ተገንዝቤያለሁ ሲልም የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ገልጿል።

የልዩ ኃይሉ ቀጣይ እጣ ፈንታ ከአመራሮች፣ ከመላው የሠራዊቱ አባላት እና ከክልሉ ሕዝብ ጋር በሚደረግ ውይይት እና የጋራ መግባባት “ብቻ” እንዲወሰን አብን በጥብቅ አሳስቧል።
988 views14:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ