Get Mystery Box with random crypto!

በወልዲያ እና መርሳ ከተሞች መንገድ እና ተቋማት ተዘግተዋል፡፡ በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ እና መር | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በወልዲያ እና መርሳ ከተሞች መንገድ እና ተቋማት ተዘግተዋል፡፡

በሰሜን ወሎ ዞን ወልዲያ እና መርሳ ከተሞች መጋቢት 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጧቱ 2 ስዓት ጀምሮ ተቋማት ተዘግተዋል፣ተሽከርካሪ በከተማዋ እንዳይንቀሳቀስ ተደርጓል ሲሉ ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ተናገሩ።

በከተማዋ የባንክ አገልግሎትን ጨምሮ ሁሉም የህዝብ መገልገያ ተቋማቶች እና የተሽከርካሪ መንገድ የተዘጋ ሲሆን በአማራ ክልል ልዩ ሃይል እና ፋኖ  ላይ ከመንግስት በወረደ ትዕዛዝ ትጥቅ ፍቱ ከመባሉ ጋር በተያያዘ ህዝቡ ባለመስማማቱ እንዲዘጋ እንደተደረገ ነው ነዋሪዎች የገለፁት።

በትላንትናው እለት በከተማዋ ዙሪያ በምትገኜው ጎብየ ተብላ በምትጠራ አካባቢ በሁለቱ ሃይሎች መካከል አለመግባባት በመፈጠሩ ተኩስ ገጥመው እንደነበር በመግለፅ ከዛሬ ጧት 2 ስዓት ጀምሮ የስራ ማቆም እና የመንገድ መዝጋት አድማ እያደረጉ እንደሆነ ተገልፇል ።