Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-04-06 12:27:35
በመቀሌ ከተማ የወይን ምርት 160 ብር በኪሎ ለገበያ እያቀረበ መሆኑን ቶም ጎልድ የእርሻ ማእከል አስታወቀ፡፡

በኣሁኑ ሰኣት የወይን ዋጋ በመቐለ ገበያ ከ190 እስከ 210 ብር በኪሎ እየተሸጠ ሲሆን የቶም ጎልድ እርሻ ማእከል በ130 ብር በኪሎ ዋጋ እያቀረበ መሆኑን የተናገሩት የማእከሉ ስራ ስኪያጅ ኣቶ ገ/መድህን ሃደራ ማአከሉ በክልሉ ተፈጥሮ በነበረው ጦርነት ምክንያት በቂ ግብአት ባልማግኘቱ ስራውን በአግባቡ ሲሰራ እንዳልነበር ገልጸዋል፡፡

ከእስልምና እምነት ተከታዮች የረመዳን ፆም ጋር ተያይዞ ወይን ተፈላጊ በመሆኑ የእርሻ ማእከሉ ለማሕበረሰቡ በቅናሽ እያቀረበ ነው ያሉት የቶም ጎልድ የእርሻ ማእከል ኦፕርሽናል ማናጀር ኣቶ ፍስሃ ኣብራሃ ናቸው።

በእርሻ ማእከሉ ወይን ሲገዙ ያገኘናቸው ወ/ሮ ለምለም ገብረመስቀል እና ወ/ሮ ሚዛን ገብረአእግዛብሄር ማእከሉ ያቀረበው ወይን በዋጋም ሆነ በጥራት ተመራጭ መሆኑንና ድርጅቱ በጦርነቱ ወቅት የሽንጉርት ፥ቲማቲም እና የበቆሎ እሽት በቅናሽ ዋጋ ሲያቀርብ እንደነበር ተናግረዋል።

ቶም ጎልድ የእርሻ ማእከል በመቐለ ከተማ ኣይናለም ኣከባቢ 100 ሄክታር መሬት ስፋት ያለው የእርሻ ልማት ድርጅት ሲሆን በኣሁኑ ሰኣት የ24 ሄክታር የወይን ምርት፣ 7 ሄክታር ቀይ ሽንጉርት፥ 5 ሄክታር ጎመንና 2 ሄክታር ላይ ደግሞ በቆሎ በማልማት ላይ ይገኛል፡፡
1.1K views09:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 11:44:36
#ሰበር
ከባህር ዳር ወደ ጎንደር የሚወሰደው መንገድ በመከላከያ ሰራዊት እንደተዘጋ ታወቀ

ከተዘጋው መንገድ በቅርብ ርቀት ላይ የክልሉ ልዩ ኃይል ካምፕ ይገኛል
መጋቢት 28፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) ከዛሬ ማለዳ ጀምሮ ከባህር ዳር ወደ ጎንደር የሚወስደው መንገድ ወረታ ከተማ አካባቢ በመከላከያ ሠራዊት መዘጋቱን የአዲስ ዘይቤ ምንጮች ከስፍራው ገለፁ።

መንገዱ በመንግስት የመከላከያ ሠራዊት ኃይል አባላት የተዘጋ ሲሆን አዲስ ዘይቤ ምክንያቱን ለማጣራት ያደረገችው ሙከራ አልተሳካም። መንገዱ የተዘጋው ደቡብ ጎንደር ወረታ ከተማ ላይ ሲሆን ከተዘጋው መንገድ በቅርብ ርቀት ትልቅ የአማራ ክልል የልዩ ሀይል ካምፕ ይገኛል።

ሰሞኑን የልዩ ሀይል ትጥቅ መፍታት ወሬ በማህበራዊ የትስስር ገፆች በስፋት መዘዋወሩን ተከትሎ በክልሉ መዲና ባህር ዳር ጨምሮ አንዳንድ የክልሉ አካባቢዎች ውጥረት ተፈጥሯል።
1.2K viewsedited  08:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-06 11:01:07 ለህዝብ በማያስቡ ፖለቲከኞች መቸገር ሊበቃ ይገባል - ያማረ ዱካ

ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ


1.1K views08:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 18:18:57 የቡና ቅምሻ ዉድድር አለመካሄዱ ቡና አምራችና አቅራቢዎችን ለኪሳራ ዳርጓል

በኢትዮጵያ ለ3 ተከታታይ ዓመታት ሲካሄድ የነበረዉ የባለ ልዩ ጣዕም ቡና ቅምሻ ዉድድር ( ካፕ ኦፍ ኤክሰለንስ) በዘንድሮው ዓመት እንደማይካሄድ የኢትዮጵያ ቡናና ሻይ ባለስልጣንን ማስታወቁን ተከትሎ በግዢ እና በቅድሚያ ዝግጅት ወቅት ባለመነገሩ ለከፍተኛ ኪሳራ መጋለጣቸዉን ቡና አምራች አርሶአደሮችና አቅራቢዎች ለአዲስ ዘይቤ ገልጸዋል።

በ2015 ዓ.ም መጨረሻ ለሚካሄደው ውድድር ከፍተኛ መጠን ያለዉ ቡና ያዘጋጁት አርሶአደሮች እና ወደ ላኪዎች የሚያቀርቡ የግል ቡና ሳይት ባለቤቶች ካፕ ኦፍ ኤክስለንስ ከመምጣቱ በፊት ከአርሶአደሩ በአማካኝ ከ20 እስከ 30 ብር ይገዙ የነበረውን 1 ኪሎ እሽት ቡና በዚህ አመት እስከ 90 ብር ግዥ መፈጸማቸውን አስረድተዋል።

በሲዳማ ክልል በአርቤጎና የሚገኘው ሲፋሙ የተባለው የግል ሳይት "ለ4ኛ ጊዜ ለሚካሄደው የቡና ጥራት ዉድድር ከ11 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ በማድረግ ግዢ መፈፀሙንና ውድድሩ ሲቀር እስከ 4 ሚሊዮን ብር ኪሳራ እንደሚደርስበት ስጋቱን አስፍሯለ፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/hawassa/current-affairs-am/failure-to-hold-the-coffee-tasting-competition-has-led-to-losses-for-coffee-producers-and-suppliers
1.2K views15:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 17:22:01
ሳፋሪኮም ኢትዮጵያ ከአንድ ሚልየን በላይ ደንበኞቹን በሚቀጥሉት 3 ወራት በእጣ ይሸልማል - Zeybe +
1.0K views14:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 16:44:11
ፖለቲከኞች ስለፖለቲካ ገበያ እንጂ ስለህዝቡ ተጨንቀው አያውቁም፣ ለምን እንከተላቸዋለን ታዲያ? - ያማረ ዱካ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd
970 views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 16:16:27
994 views13:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 15:53:32 ከሰሜን ወሎ በህወሃት ኃይሎች የተወሰዱ ከ460 በላይ ነዋሪዎች የት እንዳሉ አይታወቅም ተባለ

በፌደራል መንግስትና በህውሃት ሃይሎች ተቀስቅሶ በነበረው የሰሜኑ ጦርነት የአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ሙሉ ለሙሉ በትግራይ ክልል ሃይሎች በቁጥጥር ስር ውሎ በነበረት ወቅት በተለይም የህውሃት ሃይሎች ወልዲያንና አካባቢዋን ሲቆጣጠሩ የጦር መሳሪያ ይዘው የተገኙ የቀድሞው ሰራዊት አባል ወይም ሚሊሻ ናችሁ በሚል ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም በርካታ ሰዎችን ወደ መቀሌ እየጫኑ እንደወሰዷቸው አዲስ ዘይቤ ያነጋገረቻቸው የጥቃቱ ሰለባ ቤተሰቦች አስረድተዋል።

አዲስ ዘይቤ በሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ደቦት እና በቅሎ ማነቂያ ተብሎ በሚጠራ ስፍራ ተገኝታ በህውሃት ሃይሎች አባቶቻቸው የተወሰዱባቸውን ልጆች አነጋግራለች። አቶ ስለሺ ተስፋ በሰሜን ወሎ ዞን ጉባ ላፍቶ ወረዳ ደቦት ቀበሌ ነዋሪ ሲሆን ጥቅምት 23 ቀን 2014 ዓ.ም አባቱ፣ አጎቱና ሌሎች ሶስት ጎረቤቶቹ በህውሃት ሃይሎች ተወስደውበታል።

አባቱ አቶ ተስፋ ቢክስ እና አጎቱ አቶ አረጋ ቢክስ በደቦት ቀበሌ አርሶ አደሮች ሲሆኑ ቤታቸው ሲፈተሽ የግል መሳሪያ ስለተገኘባቸው የቀድሞው ሰራዊት አባላት (ሚሊሻ) በመሆናችሁ ለፌደራል መንግስት መረጃ ታቀብላላችሁ ተብለው እንደተወሰዱ አቶ ስለሺ ተስፋ ይናገራል።
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/%E1%8B%9C%E1%8A%93/politics-am/current-affairs-am/it-was-said-that-the-whereabouts-of-more-than-460-residents-who-were-taken-from-north-wolo-by-hhwat-forces-are-unknown
1.1K views12:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-05 15:16:57
በሁዋዌ የዓለም አቀፍ የአይሲቲ ውድድር ላይ የሚሳተፉት ኢትዮጵያውያን ተማሪዎች Zeybe +
979 views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-04 17:21:16 በኢትዮጵያ የበልግ ዝናብ ከሚያገኙ አካባቢዎች አንዱ የሆነው የድሬዳዋ አስተዳደር ሰሞኑን ባሰራጨው ማስጠንቀቂያ የበልግ ወቅት መግባትን ተከትሎ በድሬዳዋና በአካባቢዋ እየጣለ ያለው ዝናብ ካለፋት ሦስት ተከታታይ ዓመታት ጋር ሲነፃፀር በእጅጉ የጨመረና በሰውና በንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል የሚችል መሆኑን የሜትሮሎጂ ትንበያዎች መጠቆማቸውን ገልጿል።

በድሬዳዋ ከተማ በቀበሌ 06 ቀፊራ ተብሎ በሚታወቀው የገበያ ስፍራ አቅራቢያ በሚገኘው የአሸዋ ሜዳ ላይ በጉልት ድንችና ቲማቲም በመሸጥ ኑሮዋን የምትገፋው የ27 ዓመቷ መይሙና ዩዬ እንደምትናገረው ሰሞኑን ሳያቋርጥ የሚጥለውን ዝናብ ተከትሎ የመጣው ጎርፍ ለሳምንት ልትሸጥ ያዘጋጀቸውን ሶሰት ማዳበሪያ ድንች ወስዶባታል።

አቶ ዚያድ ሸለላ የተባሉ ልባሽ ጨርቆችን በዳስ ሱቅ ውስጥ በመሸጥ የሚተዳደሩ ነዋሪም በተመሳሳይ የሚተዳደሩበት ለመሸጥ የተዘጋጁ ሰልባጅ ልብሶችን “ጎርፋ ጠራርጎ ወስዶብኛል፣ እኔ የምፈራው ዝናቡ በዚሁ ከቀጠለ ትልቅ ጎርፍ አምጥቶ እንደከዚህ ቀደሙ ሰው እንዳይጨርስ ነው" ሲሉም ያደረባቸውን ስጋት ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/dire-dawa/societal-issues/business-am/news-am/the-residents-of-dredawa-said-that-they-are-in-danger-of-flooding
622 views14:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ