Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የቴሌግራም ቻናል አርማ addiszeybe — አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe
የሰርጥ አድራሻ: @addiszeybe
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 11.27K
የሰርጥ መግለጫ

ለፈጣን መረጃዎች አዲስ ዘይቤ
Twitter : https://twitter.com/AddisZeybe
Facebook : https://bit.ly/2SeU3Ev
Website : https://addiszeybe.com/
YouTube : https://youtube.com/c/AddisZeybe
Instagram : https://bit.ly/3D1tEwC
ስልክ 251954903850
ኢሜይል info@addiszeybe.com

Ratings & Reviews

3.67

3 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

2

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 9

2023-04-12 12:18:46
የአማራ ልዩ ኃይል፣ ፋኖና ሚሊሻን መበተን የአማራ ህዝብ ጥቃት እንዲፈፀምበት ማመቻቸት ነው ሲል ባልደራስ ፓርቲ አስታወቀ

ሚያዝያ 04፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) "የጎሳ ፖለቲካ አራማጆች የአማራ ህዝብ ቀጣይ ጥቃት እንዲፈፀምበት ሁኔታዎችን ለማመቻቸት የአማራን ልዩ ኃይል፣ ፋኖን እና ሚሊሻውን ለማፍረስ ቀን ከሌት እየባዘኑ ይገኛሉ" ሲል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ ገለፀ።

"በንፁሀን ህይወት ላይ የሚቆምሩ ፖለቲከኞች" ብሎ ፓርቲው የጠራቸው አካላት የአማራን ህዝብ ትጥቅ አስፈታለሁ በማለት ሀገሪቱን "መውጫ ወደሌለው መቀመቅ እያስገቧት እንደሆነ ሊሰመርበት ይገባል" ሲል አሳስቧል።

ወቅታዊውን ሁኔታ "ትግል" ሲል የጠራው ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ በሰላማዊ ሰልፈኞች ላይ ጥቃት በመሰንዘር "ትግሉን ወደኋላ" መጎተት አይቻልም ሲል አስታውቋል።
1.1K views09:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 20:24:12
በደቡብ ጎንደር ዞን ውስጥ ለዓመታት የቆየ ከፍተኛ የውሃ እጥረት አጋጥሟል ተባለ

በደቡብ ጎንደር ዞን የእስቴ፣ መካነ እየሱስ ከተማ አስተዳደር እና የአንዳቤት ወረዳዎች ነዋሪዎች የተበከለ የምንጭና የወንዝ ውሃ መጠጣት ከጀመሩ ዓመታት እንዳስቆጠሩ ለአዲስ ዘይቤ ገለፁ።

ከ160 ሺህ በላይ ህዝብ የሚኖርባት የእስቴ ወረዳ የውሃ ማማው ጉና ተራራ ስር ብትገኝም ከፍተኛ የመጠጥ ውሃ እጥረት በመፈጠሩ ነዋሪዎች ቆሻሻ የምንጭ እና ወራጅ ውሃ ከሌሊት 9 ሰዓት እስከ እኩለ ቀን ድረስ ወረፋ ጠብቀው በመቅዳት ለመጠጣት መገደዳቸውን ይናገራሉ።

በተመሳሳይ የአንዳቤት ወረዳ አንዳቤት ከተማ ነዋሪዎች በውሃ እጦት ከሁለት ዓመታት በላይ እንዳሳለፉና ነዋሪዎቹ ንፅህናው ያልተጠበቀ የምንጭና ወንዝ ውሃ እየተጠቀሙ በመሆናቸው ለበሽታ እየተዳረጉ እንደሆነም ነግረውናል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/gonder/current-affairs-am/it-is-said-that-there-has-been-a-severe-water-shortage-in-the-south-gondar-zone-for-years
625 views17:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 16:40:09 በጦርነቱ የተሳተፉ ቤተሰቦቻቸው የት እንዳሉ ማወቅ እንፈልጋለን ሲሉ የመቀሌ ነዋሪዎች ጠየቁ

አቶ ገብረመስቀል አበበ የተባሉት ሌላኛው ነዋሪም የአንድ ወንድ ልጅ አባት ሲሆኑ “ከአንድ ቤት አንድ ሰው ወደ ጦርነት መግባት አለበት፣ ካልሆነ እርዳታ አይሰጠውሙ” በተባለ ጊዜ አንዱ ልጃቸው በግዳጅ ወደ ውጊያ ማምራቱን በሀዘን ድባብ ውስጥ ሆነው ነግረውናል።

አሁን በተደረሰው ስምምነት መሰረት “ልጄ ከዛሬ ነገ ይመጣል እያልኩ በሀዘንና በተስፋ እገኛለሁ” የሚሉት አቶ ገብረመስቀል ልብ በሚሰብር ሁኔታ እያለቀሱ ልጄ ካለ መንግስት ምላሽ ይስጠኝ ሲሉ ይማፀናሉ።

ወ/ሮ ለምለም ኃይሉ የመቀሌ ከተማ ነዋሪ ናቸው። ለሁለት ዓመታት በቆየው ጦርነት ሁለት ልጆቻቸው ወደበረሃ ወርደው ጦርነቱን እንደተቀላቀሉ ይገልፃሉ። ጦርነቱ በሰላም ስምምነት ተቋጭቶ ግልፅነት ይጎድለዋል የሚሉ አካላት ቢኖሩም አንፃራዊ ሰላም ሰፍኖ ክልሉም ጊዜያዊ አስተዳደር ተሹሞለታል።

ይሁን እንጂ ወ/ሮ ለምለም ሁለት ልጆቻቸው እስካሁን ድረስ የት እንዳሉ እንደማያውቁ ገልፀው የልጆጃቸውን መገኛ በጉጉት እንደሚጠብቁ ነግረውናል። ከቤት በወጡበት ሰሞን ልጆቻቸው ደብዳቤ ይሉኩላቸው እንደነበር ለአዲስ ዘይቤ የተናገሩት አዛውንቷ፣ ለመጨረሻ ጊዜ የልጆቻቸውን ወሬ ከሰሙ 1 ዓመት ከ8 ወር ማለፉንም ገልፀዋል።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/politics-am/current-affairs-am/news-am/we-want-to-know-where-their-families-who-participated-in-the-war-are-asked-the-residents-of-mekele
907 views13:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 16:23:32
በኮምቦልቻ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ ላይ ከነበሩ ግለሰቦች 2 ሰዎች ሲሞቱ ከ12 የሚበልጡ ተጎድተዋል ተባለ

ሚያዝያ 3፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ ባህር ዳር) ዛሬ ረፋድ ላይ በኮምቦልቻ ከተማ ሰላማዊ ሰልፍ እየተደረገ በነበረበት ወቅት “የልዩ ኃይል አባላት የተያዙ አሉ” የሚል መረጃ በመሰራጨቱ ከመከላከያ ሰራዊት ጋር ግጭት ውስጥ መገባቱን ነዋሪዎች ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

በኮምቦልቻ አንድ ጤና ጣቢያ ውስጥ የሚገኙ የአዲስ ዘይቤ ምንጮች እንደገለፁት አንድ ሰው እዛው ተኩስ የተከፈበት ስፍራ ላይ ህይወቱ ማለፉን እና ሌላ አንድ ሰው በአምቡላንስ ወደጤና ጣቢያ እየተወሰደ ህይወቱ አልፏል ብለዋል።

በተጨማሪም 12 የሚሆኑ ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸው ወደ ኮምቦልቻ ጠቅላላ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የሚገልፁት ነዋሪዎች፣ አምቡላንስ በተደጋጋሚ ሲመላለስ እንደነበረና የተጎጂዎች ቁጥር ከፍ ሊል ይችላል ሲሉ ለአዲስ ዘይቤ ተናግረዋል።

በአሁኑ ሰዓት በኮምቦልቻ ከተማ ከመደበኛ ጊዜው የተቀዛቀዘ እንቅስቃሴ መኖሩን ነዋሪዎች ነግረውናል።
901 views13:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 15:45:29
ስራ ሲገኝ ሰሪው ይጠፋል፤ ሰሪው ሲኖር ደግሞ ስራው ይታጣል ። አዲስ ቢዝነስ እንዴት በሁለት እግሩ መቆም ይችላል? - Startup Corner

ወጣት ቸርነት መኳንንት - የMedstore.et መስራች እና ዋና ስራ አስኪያጅ

በአዲስ ዘይቤ ዩ-ትዩብ ቻናል ይጠብቁን
https://www.youtube.com/@AddisZeybe/videosd

#startupcorner
907 views12:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 14:36:56 ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ቤት የፈረሰባቸው ተፈናቃዮች ተበራክተዋል- የደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር

ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች በችግር ውስጥ የሚገኙበት ደብረብርሃን ከተማ ከአዲስ አበባ ዙሪያና ከኦሮሚያ ክልል ተጨማሪ ተፈናቃዮችን በመቀበሉ የደብረ ብርሃን ከተማ አስተዳደር ከአቅሙ በላይ እንደሆነበት አስታወቀ።

በደብረብርሃን ከተማ ከ1 ዓመት በላይ በመጠለያ ጣብያ የቆዩ ተፈናቃዮች የሚገኙ ሲሆን እስከአሁን ድረስ የደብረብርሃን ከተማ ህዝብና ከአንዳንድ ድርጅቶች ውጭ መንግስት ተገቢውን ድጋፍ እያደረገላቸው ባለመሆኑ ለችግር በመጋለጣቸውን ተፈናቅዮች ቅሬታቸውን ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

በደብረብርሃን ከተማ አስተዳደር ከንቲባ ፅህፈት ቤት የተፈናቃዮች አስተባባሪ አቶ አንተነህ ገብረእግዚአብሄር በተለይ ለአዲስ ዘይቤ እንደገለፁት በከተማዋ ከሰዎች ተጠግተውና ቤት ተከራይተው የሚኖሩትን ሳይጨምር ከኦሮሚያ ክልል የተፈናቀሉ በ6 መጠለያ ካምፕ ውስጥ የሚገኙ ከ28 ሺህ በላይ ተፈናቃዮች ይገኛሉ።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/bahir-dar/%E1%8C%A4%E1%8A%93/politics-am/current-affairs-am/economy-am/the-number-of-evacuees-from-around-addis-ababa-and-from-the-oromia-region-has-increased-debreberhan-city-administration
1.0K views11:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 13:58:16 በድሬዳዋ ከተማ እና አጎራባች አካባቢዎች በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡ መድኃኒቶች በጤና ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው

የድሬደዋ ከተማ ነዋሪው አቶ አለማየሁ አዳነ በቅርቡ ከአንድ የታወቀ ፋርማሲ የገዙት መድኃኒት የጤና ችግር እንዳስከተለባቸው ይናገራሉ። "ለረጅም ዓመታት በአስም በሽታ ነው የምሰቃየው፤ በቅርቡ ከፍተኛ ህመም ተሰምቶኝ የወሰድኩት መድኃኒት በቆዳዬ ላይ ሽፋታ በማስከተሉ ተጠራጥሬ ማሸጊያውን ስመለከት ጊዜው ያለፈበት ሆኖ አግኝቸዋለሁ" ሲሉ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪና የፋርማሲ ባለሙያዋ ወ/ሪት ሞሚና ሰኢድ (ሰሟ የተቀየረ) ቀድሞ ትሰራበት የነበረው መድሀኒት ቤት ባለቤት ያለሀኪም ማዘዣ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ መድኃኒቶችን እንዲሸጡ ያስገድድ እንደነበረ ትናገራለች።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲና ሶማሊያ ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆኑ ለኮንትሮባንድ ንግድ ተጋላጭ ከሆኑ ቀዳሚ አካባቢዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/dire-dawa/%E1%8C%A4%E1%8A%93/current-affairs-am/economy-am/drugs-imported-illegally-in-dredawa-city-and-neighboring-areas-are-causing-harm-to-health
1.0K views10:58
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 12:55:57
አርቲስት ቴዲ አፍሮ በኢትዮጵያ ከእስራኤል አምባሳደር ጋር ተገናኘ
ሚያዝያ 3፤ 2015 ዓ.ም.

(አዲስ ዘይቤ፤ አዲስ አበባ) ኢትዮጵያዊው የሙዚቃ ባለሙያ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በኢትዮጵያ የእስራኤል አምባሳደር የሆኑትን አምባሳደር አለልኝ አድማሱ ጋር ተገናኙ።

አምባሳደር አለልኝ በትዊተር ገፃቸው እንዳሰፈሩት ከአርቲስት ቴዲ አፍሮ ጋር በነበራቸው ቆይታ የኢትዮጵያ እና እስራኤልን የባህል ግንኙነት ስለማሳደግ ተወያይተናል ብለዋል። የባህል ግንኙነቱም በዋናነት በፈጠራ ባለሙያዎች እና የጥበብ ሰዎች እንዲታገዝ ለማድረግ ትኩረት ማድረጋቸውንም በኢትዮጵያ የእስራኤል አማባሳደሩ ገልፀዋል።

እንደ አውሮፓውያኑ አቆጣጠር ቴዲ አፍሮ በ2019 በእስራኤል ሀገር የሙዚቃ ጉዞ በማድረግ የሙዚቃ ስራዎቹን አቅርቦ ነበር።
1.1K views09:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 11:47:00
በዚህ ሳምንት በፈራንካ ዝግጅት ዶላርን ከዓለም አቀፍ መገበያያነት ለማስወገድ የሚደረገውን እንቅስቃሴ ምን ያስከትላል በሚለው ርዕስ ላይ ከባለሙያ ጋር ቆይታ ያደርጋል። ጥያቄ እና አስተያየታችሁን ላኩልን ::

#ፈራንካ #business #feranka #investment #Ethiopia #DeDollarization #us #AddisAbaba #europe
1.1K views08:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-11 10:55:17
"ህወሓት በጦርነቱ ሰሜን ሸዋ ሲደርስ ቁጣውን የተወጣው ህዝቡ ላይ ነው፤ ይሄኔ በርካታ የክልሉ አመራሮች ሸሽተው አዲስ አበባ ነበሩ"- ያማረ ዱካ

ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ማስፈንጠሪያውን ይጫኑ -

1.1K views07:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ