Get Mystery Box with random crypto!

በድሬዳዋ ከተማ እና አጎራባች አካባቢዎች በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡ መድኃኒቶች በጤና ላይ ጉዳት እ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

በድሬዳዋ ከተማ እና አጎራባች አካባቢዎች በህገ-ወጥ መንገድ የሚገቡ መድኃኒቶች በጤና ላይ ጉዳት እያደረሱ ነው

የድሬደዋ ከተማ ነዋሪው አቶ አለማየሁ አዳነ በቅርቡ ከአንድ የታወቀ ፋርማሲ የገዙት መድኃኒት የጤና ችግር እንዳስከተለባቸው ይናገራሉ። "ለረጅም ዓመታት በአስም በሽታ ነው የምሰቃየው፤ በቅርቡ ከፍተኛ ህመም ተሰምቶኝ የወሰድኩት መድኃኒት በቆዳዬ ላይ ሽፋታ በማስከተሉ ተጠራጥሬ ማሸጊያውን ስመለከት ጊዜው ያለፈበት ሆኖ አግኝቸዋለሁ" ሲሉ ለአዲስ ዘይቤ ገልፀዋል።

የድሬዳዋ ከተማ ነዋሪና የፋርማሲ ባለሙያዋ ወ/ሪት ሞሚና ሰኢድ (ሰሟ የተቀየረ) ቀድሞ ትሰራበት የነበረው መድሀኒት ቤት ባለቤት ያለሀኪም ማዘዣ በኮንትሮባንድ ወደ ሀገር ውስጥ የገቡ መድኃኒቶችን እንዲሸጡ ያስገድድ እንደነበረ ትናገራለች።

የድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር እና የሶማሌ ክልል ሲቲ ዞን ከጎረቤት ሀገር ጅቡቲና ሶማሊያ ጋር ሰፊ ድንበር የሚጋሩ በመሆኑ ለኮንትሮባንድ ንግድ ተጋላጭ ከሆኑ ቀዳሚ አካባቢዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/dire-dawa/%E1%8C%A4%E1%8A%93/current-affairs-am/economy-am/drugs-imported-illegally-in-dredawa-city-and-neighboring-areas-are-causing-harm-to-health