Get Mystery Box with random crypto!

ህውሓት ለኮረምና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መመደቡ ታወቀ የኮረም እና አላማጣ አካባቢዎችን ለማስ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

ህውሓት ለኮረምና አላማጣ አካባቢዎች አመራር መመደቡ ታወቀ

የኮረም እና አላማጣ አካባቢዎችን ለማስተዳደር የህወሓት ቡድን ለአካባቢዎቹ አመራር መድቦ የመከላከያ ሠራዊትን ከአካባቢው መውጣት እየተጠባበቀ መሆኑን አዲስ ዘይቤ ከምንጮቿ አረጋግጣለች።

ከሰሞኑን የኢትዮጵያ ፌደራል መንግስት የክልል ልዩ ኃይሎች እና ኢ-መደበኛ ታጣቂዎችን ወደ መከላከያ ሠራዊት፣ ፌደራል እና የከተማ ፖሊስ ሆነው እንዲቀላቀሉ ባቀረበው ጥሪ ሳቢያ የአማራ ክልል ልዩ ኃይል አባላትና ፋኖዎች ጥሪውን ተቃዉመው መቆየታቸው ይታወሳል። ከዚህም ባለፈ “ትጥቅ አንፈታም” ባሉ ታጣቂዎች እና መከላከያ ሰራዊት መካከል ተኩስ ተከፍቶ ነበር።

ይሁን እንጂ በአላማጣ እና ኮረም ከተማዎች እና በዙሪያው ሰፍረው የቆዩት በርካታ የአማራ ክልል ልዩ ኃይልና የፋኖ ታጣቂዎች ከትጥቅ ፍቱ ጥሪ ጋር ተያይዞ ከአካባቢው ለቀው መውጣታቸውን ተከትሎ ህውሓት ለአካባቢዎቹ አመራሮችን እንደመደበ አዲስ ዘይቤ ከትግራይ ክልል ህጋዊ ታጣቂ አባላት አረጋግጣለች።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/mekelle/current-affairs-am/It-is-known-that-the-TPLF-has-been-assigned-the-leadership-of-Korum-and-Alamata-areas