Get Mystery Box with random crypto!

ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ግጭት የማንነት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ሰግተዋል ባለፈው ቅዳሜ ለተነሳው የ | አዲስ ዘይቤ ~ Addis Zeybe

ኢትዮጵያዊያን በሱዳን ግጭት የማንነት ጥቃት እንዳይደርስባቸው ሰግተዋል

ባለፈው ቅዳሜ ለተነሳው የሱዳን ግጭት “የኢትዮጵያ እና ኤርትራ መንግስታት ጣልቃ ገብነት አለበት” በሚል እየተወራ መሆኑን ተከትሎ የሃገራቱ ዜጎች ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብተዋል።

በካርቱም ከተማ ጅሬፍ በተባለው አካባቢ ነዋሪ የሆንችው ኢትዮጵያዊት ኤዶም ንጉሴ (ስሟ የተቀየረ)  ቃለ-መጠይቁን እየሰጠችን ባለችበት ወቅት እንኳን በቅርብ ርቀት የተኩስ ድምጽ እንደሚሰማት ትናገራለች።

ከወራት በፊት በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አቅራቢያ አል-ፋሻጋ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተፈጠረ ግጭት የሱዳን ወታደሮች ተገድለዋል በሚል በሱዳናዊያን ዘንድ "እኛ እያኖርናችሁ መንግስታችሁ ወታደሮቻችንን ይገድላል" የሚል ተቃውሞ በኢትዮጵያውያን ላይ መድረሱን የመረጃ ምንጫችን ታስታውሳለች።
ዝርዝሩን ያንብቡ - https://am.addiszeybe.com/featured/addis-ababa/current-affairs-am/Ethiopians-are-afraid-of-being-attacked-in-the-Sudanese-conflict