Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @addis_reporter
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.42K
የሰርጥ መግለጫ

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-01 15:00:55
ሰበር ጎንደር!

በጎንደር ህዝብ ላይ በሞርተር እና በዲሽቃ የታገዘ ጦርነት በኦህዴድ ሠራዊት ተከፈተ።

ሻለቃ አርበኛ መሳፍንትን ከ1 ሺህ በላይ የኦህዴድ ሠራዊት አጅሬ ጃኖራ በራ የምትባል ቦታ ላይ በመክበብ በሞርተር እና በዲሽቃ ተኩስ ከፍተውበታል ሲል የመረጃ ምንጫን አድርሶናል።

አርበኛ መሳፈንትን እንይዛለን በሚል ዛሬ ከነገ በቡድን መሳሪያ ጦርነት የከፈተው የኦህዴድ ሠራዊት በህፃናት፣ሴቶች እና ሌሎች ንፁሃን አማሮች ላይ ጭፍጨፋ እየፈፀመ ነው ተብሏል።

የጎንደር ህዝብ ወደ ስፍራው በማቅናት መንገድ እንዲዘጋ፣መረጃ እና ስንቅ በአስቸኳይ እንዲያቀርብ ጥሪ ቀርቧል።

መረጃው የአማራ ሚዲያ ማዕከል ነው!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
1.1K views12:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 10:22:39
ሰበር ማጀቴ!

የብርሃኑ ጁላ መከላከያ ማጀቴ ላይ ጦርነት ከፈተ።

የኦህዴዱ መከላከያ ሃይል ማጀቴ ላይ በዚህ ሰአት ጦርነት መክፈቱን ተገለፀ። አበላምባ ጎጥ ቀበሌ ይሄው ሃይል ጦርነቱን የከፈተው በፋኖ ህዝባዊ ሃይልና በህዝብ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል። በከባድ መሳሪያ በመታገዝ ጦርነት የከፈተውን ይሄንን ሃይል ፋኖና ህዝቡ በጋራ ለመከላከል እየሞከሩ መሆኑንም ነው የተናገረዋል።ይሄ ዜና እየተጠናቀረ ባለበት ሰአትም ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው።

( ኢትዮ 360 )

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
2.9K views07:22
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 09:43:40 “የሽብር ክሱ ሊያስገድል ወይም የእድሜ ልክ እስራት ሊያስቀጣ ይችላል!” -ሀብታሙ ምናለ

ሀገር ውስጥ ያለነው ባልገባን ነገር አንሳቅ! በዘመነ ኢሕአዴግ፤ የቅንጅት ፖለቲካዊ አመራሮች ከያሉበት ተለቃቅመው ታስረው ክስ ይጀመርባቸዋል። ክሳቸውም "በሀገር ክህደት" ነው። ይሄን ክስ ሲሰሙ፦ ሁሉም ክሱን ቀለል አድርገው ይሳሳቃሉ፤ አንዳንዶቹም በክሳቸው ያሾፋሉ።

በዚህ ወቅት ነው አንድ የህግ እውቀት ያለው ሰው በሁኔታቸው በመናደድ:- "የተከሰሳችሁበትን ክስ ምንነት ግን በውል አውቃችሁታል? የተከሰሳችሁበት ወንጀል ምን እንደሚያስቀጣ ታውቃላችሁ?" የሚል ፈታኝ ጥያቄ ያነሳላቸዋል። ጠያቂው የህግ ባለሙያ በመሆኑ ጥያቄው አስደነገጣቸው! ሁሉም ጸጥ ረጭ ብለው ፤ አንተ ታውቃለህ፣ አንተ ታውቃለህ? በሚል አኳኋን እርስ በእርስ ተያዩ።

አንድም ሰው ደፍሮ የቅጣቱን እርከን መናገር የቻለ አልተገኘም - ምክንያቱም እውቀቱ የላቸውም።

"ቅጣቱ ከፍ ካለ ሞት፣ ዝቅ ካለ ደግሞ እድሜ ልክ እስራት ነው" ብሎ ለታሳሪዎቹ አረዳቸው።

በሳቅ ጥርሳቸውን በከንፈራቸው መከለል ያቃታቸው፣  አሁን በተራቸው በንዴት እና በቁጭት ከንፈራቸውን በጥርሳቸው ይነክሱበት ጀመር - አለማወቅ ደፋር ያደርጋል! እንደዚህ ነው!

ትላንት መንግሥት "በሽብርተኝነት ፈርጄ አስሬያቸዋለሁ፤ ሌሎችንም ደግሞ አድኜ አመጣለሁ" ብሏል። እኛ ግን አሁንም ሳናውቅ እንስቃለን።

ችግሩን አሁን ልንገርህ:-

ይህቺ አዋጅ ተደብቃበት ከነበረችበት መሳቢያ ተስባ ወጥታለች። በሌላ አገላለጽ ጂኒው ከጠርሙሱ ወጥቷል ማለት ነው።

አፈጻጸሙስ እንዴት ነው የሚለውን ማሰብ ደግሞ ብልህነት ነው። አሁን ያሉት ከኢሕአዴግ የማይሻሉ የኢሕአዴግ ልጆች መሆናቸውን አንዘንጋ።

  በአዋጁ መሠረት ከዚህ በኋላ  በሽብርተኝነት የተከሰሱት እና የሚፈለጉትን፤ በግል ህይወታቸውም ሆነ በፖለቲካዊ ተግባራቸው ማድነቅ፣ ንግግራቸውን በማኅበራዊ ሚዲያ ማባዛት፣ በኢሜል፣ በስልክ፣ በማኅበራዊ ሚዲያ ጤናማ የሚባለውን መልእክት መለዋወጥ፣ የእነሱን መልካም ገጽታ ማስነበብ፣ ከእነሱም ጋር ሻይ መጠጣት፣ ፎቷቸውን ይዞ መገኘት፣ በስልክ ውስጥ የእነሱ ምስል፣ ቪዲዮ፣ ፅሁፍ ይዞ መገኘት፣ እነዚህ እና እነዚህ መሰል ጉዳዮች በሽብርተኝነት ሊያስከስሱ ስለሚችሉ ቀለል አድርገን ልንመለከተው አይገባም።

ከዚህ በፊት ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ እንዳለው "የሽብር አዋጁ፣ የጠሉትን መምቻ" ብሏል። ከውጭ የጀመረው ወደ ውስጥ መግባቱ አይቀሬ ነው።  በዚህ መንግሥት የተጠላ ሁሉ ይመታበታል።

አሁንም ወደፊትም መንግሥት አምባገነን ለመሆን ሲጥር መቀለዱን ማቆም ይገባናል። መረር ብለን ልናየው ይገባል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.1K views06:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:13:10
ከአቶ ግርማ የሺጥላ ጋር የተገደሉ ሰዎች ቁጥር 6 ደረሰ!

በተኩስ ልውውጡ አቶ ግርማ የሽጥላን ጨምሮ የስድስት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና ከ14 በላይ ሰዎች መቁሰላቸው ተገለፀ።

አቶ ግርማ የሺጥላን ሲጠብቁ ከነበሩ አራት ጠባቂዎች ውስጥ ሁለቱ ከባድ የመቁሰል አደጋ፣ ሁለቱ ቀላል የመቁሰል አደጋ ደርሶባቸው በሆስፒታል እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኙ  ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በተኩስ ልውውጡ

ዋና ሳጅን በላይ አስማማው  በመንዝ ጌራ ወረዳ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት የግንዛቤ ማስጨበጫ ንዑስ ክፍል ኀላፊ የነበሩት

ረዳት ሳጅን አስማረ አንተነህ፣ በመንዝ ጌራ ወረዳ ፖሊስ ኦፊሰር ኾነው ሲያገለግሉ የቆዩት 

ድምር ከተማ ከለለው በመንዝ ጌራ ወረዳ የጸጥታ መዋቅረ ውስጥ ሲሠሩ የቆዩ፣

ከበደ አሰፋ መንዝ ጌራ ወረዳ ሚሊሻ ጽሕፈት ቤት ንብረት ክፍል ባለሙያ፣

ሾፌር ልየው መንጌ፣ አብረው መሰዋታቸውን ጠቁመዋል።

ግለሰቦቹ አቶ ግርማ የሺጥላን ወደሌላ ወረዳ እየሸኙ በነበረበት ሰዓት በተከፈተ ተኩስ መሰዋታቸውን ተናግረዋል። የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በተወለዱበት አካባቢ መፈጸሙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን መረጃ ያሳያል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.2K views05:13
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:09:05
የጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ምላሽ!

«ዛሬ የትኛው ነርቭ ሲነካ እንደሚያማቸው በደንብ ተረድቼአለሁ። ምርጫ የለኝም። የሚያማቸውን ነርቭ ጠብሰቅ አድርጎ መመዥለግ በቀጣይ የማደርገው የሙሉ ጊዜ ስራዬ ይሆናል። እንኳን የሚያማቸውን ቦታ አወኩት። እንኳንም ነካካሁት። በዚህ ደረጃ ህመሙ የሚሰማቸው ከሆነ እንግዲህ መጪው ቁንጥጫ የባሰ እንደሚሆን ለማረጋገጥ እወዳለሁ። ለእነሱ ዝባዝንኬ መልስ መስጠት ድካም እንጂ ትርፍ የለውም። ከደረቀና ከመከነ ጭንቅላት የሚፈልቅ የተሻለ ነገር አልጠብቅም። ህወሀት ቤት አድገው የህወሀትን ያህል እንኳን መተወን የማይችሉ ቀሽም ሰዎች መሆናቸውን ከማረጋገጥ ያለፈ የተጻፈበትን ወረቀት ያህል ዋጋ የማያወጣ ባዶ ክስ ነው። እንዲህ ተሸብረዋል ለካ? እውነት ሲነገር የሚደነግጡትና የሚርበተበቱት ለምንድን ነው? የያዛቸው ሴጣን እስኪለቃቸው ድረስ የእውነትን ጸበል እየረጨሁባቸው የተለመደውን ስራዬን አጠናክሬ ለመቀጠል ለራሴ ቃል ገብቼአለሁ። በድጋሚ እንኳን የሚያማችሁን ቦታ አወኩት። ይኸው ነው።»

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
2.8K views05:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-01 08:07:51
ታላቅ የምስራች

ጊዜውን የዋጀ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት በ 500 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ

በዚ ገንዘባችን እየወደቀ በሄደበት ጊዜ ብልህ ሰው ገንዘቡን ቤት ላይ ኢንቨስት ያረጋል ፤ ንብረቱም በየጊዜው ዋጋውን እየጨመረ የሚሄድ ንብረት ይሆናል

ለመኖሪያ ቢሉ ለኢንቨስትመንት ትክክለኛው ቦታ

በመሐል ከተማ ቦሌ - አትላስ እንዲሁም CMC ዋናው አስፓልት ዳር

ከልዩ የበዓል ቅናሽ ጋር

በተለያየ የካሬ አማራጭ ይዘን ቀርበናል

ባለ አንድ መኝታ 81 ካሬ

ባለ ሁለት መኝታ ከ 106 ካሬ - 160 ካሬ

ባለ ሦስት መኝታ ከ 182 ካሬ - 216 ካሬ


በተጨማሪም ለንግድ የሚሆኑ ሱቆችን በተለያየ የካሬ አማራጭ ያገኛሉ ።

ልዩ የሚያረገን ሁሉም ሽያጮቻችን በኢትዮጵያ ብር ማከናወናችን (የዶላር ጭማሪ ደንበኛን አይመለከተውም)

አጋጣሚውን በመጠቀም በየጊዜው ዋጋው እየጨመረ የሚሄድ ንብረት ላይ ገንዘቦን ኢንቨስት ያድርጉ ።

ይፍጠኑ ይደውሉ ቀድመው በመያዝ ተጠቃሚ ይሆናሉ!

0949504843 / 0927435224
3.0K views05:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 20:26:49
ሰበር ዜና!

የአማራ ፋኖ አንድነት የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ እና የምስራቅ አማራ ፋኖ ስልጠና እና መምሪያ ኃላፊ ፋኖ መንበር አለሙ በጎንደር ከተማ ታፈነ፤ ከሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ እንዲወጣ ተደርጎ ወዳልታወቀ ስፍራ መወሰዱ ተሰምቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.4K views17:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:32:15 የመከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ቆቦ ወረዳ ኦፕሬሽን መጀመሩ ተገለጸ

ማምሻውን ጀምሮ መከላከያ ሠራዊት በአማራ ክልል ሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ወረዳ በነዋሪዎች ላይ የቤት ለቤት ፍተሻ እያደረገ መሆኑን አዲስ ማለዳ ከሥፍራው ነዋሪዎች አረጋግጣለች፡፡

<<የአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላን የገደላችሁት እናንተ ናችሁ።>> በማለት ፋኖዎች እየተሳደዱ እና ቤተሰቦቻቸውም እየታሰሩ መሆኑን ነው ነዋሪዎች የገለጹት፡፡

በዚህም፤ ከአርብ ዕለት ጀምሮ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ከቆቦ ወደ አላማጣም ይሁን ወደ ወልድያ ለመሄድ መንገድ ተዘግቶ እንደነበር የገለጹት ነዋሪዎች፤ ከቀናት በፊት ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በሽምግልና ታርቀው ወደማህበረሰቡ የተቀላቀሉ የፋኖ አባላትም እየተሳደዱ ነው ብለዋል፡፡

ከአስር በላይ የፋኖ አባላት ቤተሰቦች ለእስር እንደተዳረጉም ጠቅሰው፣ ሌሊት በሚደረገው የቤት ለቤት ፍተሻ በተለይ ሴቶች እየተሳቀቁ እንደሆነ ተናግረዋል።

<<ሰውዬው የተገደሉት ሰሜን ሸዋ ሆኖ ሳለ ገዳዮቹ ቆቦ ውስጥ ናቸው ብሎ ማህበረሰቡን ሰላም መንሳት ተገቢ አይደለም።>> ያሉት ነዋሪዎቹ እየተደረገ ያለው ነገር ህዝብን ለአመጽ ከማነሳሳት ውጭ ፋይዳ የለውም ብለዋል፡፡

<<እንደ ሸኔ ያሉ ታጣቂ ኃይሎች ዜጎችን ከቀያቸው እያፈናቀሉ እና መንገድ ላይ እያገቱ ብዙ ጥፋት የሚያደርሱ ኃይሎችን ችላ በማለት፤ ምንም ባልተፈጠረበት ቆቦ ላይ ይህን ሁሉ ግርግር መፍጠር የመንግሥት አካሄድ ፍትሃዊነት የጎደለው አገዛዝ መሆኑን በተግባር የሚያሳይ ነው።>> ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

በዚህ ወቅት ተዘግተው የነበሩ መንገዶች ተከፍተው መደበኛ እንቅስቃሴ የቀጠለ ቢሆንም ማህበረሰቡ አሁንም መደናገጥና ስጋት ላይ ነው ተብሏል።

ከአማራ ክልል ብልፅግና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ግርማ የሺጥላ መገደል በኋላ፤ የጸጥታና የደኅንነት የጋራ ግብረ ኃይል በአማራ ክልል ሕገ መንግስታዊ ሥርዓቱን በማፍረስ ክልላዊ ስልጣንን በኃይል ለመቆጣጠር በሚጥሩ ጽንፈኛ ኃይሎች ላይ የማያዳግም እርምጃ እየወሰድኩኝ ነው ሲል ማስታወቁ ይታወሳል፡፡

ግብረ ኃይሉ ‹‹ፅንፈኛ ኃይሎች›› ብሎ የሚጠራቸው አካላት የአማራ ሕዝብ የልማትና የሰላም ተጠቃሚ እንዳይሆንና የተረጋጋ ሕይወት እንዳይኖረው እንዲሁም በመንግሥት የሚወሰኑ ውሳኔዎች እንዳይተገበሩ እንቅፋት ሲፈጥሩ መቆየታቸን ነው የገለጸው፡፡

ይሁን እንጂ በተለይ ግብረ ኃይሉ በክልሉ እርምጃ መውሰድ መጀመሩን ካሳወቀ በኋላ በህዝቡ ዘንድ ከፍተኛ ግራ መጋባት መፈጠሩን አዲስ ማለዳ ተገንዝባለች፡፡

ብዙዎች <<ምን እየተካሄደ ነው>> የሚል ጥያቄ እያነሱ ሲሆን፤ ጽንፈኛ ተብለው የሚጠሩ አካላትም እነማን እንደሆኑ መንግሥት በግልጽ እንዲያሳውቅ ጠይቀዋል፡፡ 

መንግሥት ሰበብ ፈልጎ የፋኖ አባላትን ለመምታት እንዲሁም ክልሉን የቀውስ ማዕከል ለማድረግ የታሰበ ተገቢ ያልሆነ አካሄድ ነው የሚሉም በርካታ ቅሬታዎች እየተነሱ ይገኛል፡፡(አዲስ ማለዳ)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.5K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 19:27:38
የኦሮሞ አፓርታይድ የአብይ አህመድ አገዛዝ ቡድን የአማራ ህዝብ አይን የሆኑ ልጆችን “አገር በማፍረስ ወንጀል” እፈልጋቸዋለሁ ሲል የአፋልጉኝ ማስታወቂያ አውጥቷል። በወንጀል እፈልጋቸዋለሁ ካላቸው ውስጥ

1. ከሀገር ውስጥ

ጎበዜ ሲሳይ
ምህረት ወዳጆ (ምሬ ወዳጆ)
በለጠ ጋሻው እና
ሙሉጌታ አንበርብር

2. ከሐገር ውጪ

ሀብታሙ አያሌው፣
ምንአላቸው ስማቸው፣
ብሩክ ይባስ እና
እየሩሳሌም ተ/ፃዲቅ 
ዘመድኩን በቀለ
ልደቱ አያሌው
መሳይ መኮንን ናቸው

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.2K views16:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:37:27
ሰበር ዜና!

የባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ ፓርቲ አስተዳደር ጽ/ቤት ኃላፊ ወ/ሮ ቀለብ ስዩም በፌደራል ፖሊሶችና የደህንነት አባላት እስከ አራስ ጨቆላዋ ጋር አፍነው ወደ ሜክስኮ ፓሊስ መምሪያ ወስደዋታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.1K views15:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ