2023-07-23 21:54:35
" እኛ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እየጠበቅን ነው " - ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ
የአማራ እና የትግራይ ክልሎች የሚዋሰኑባቸውን የወልቃይት፣ የጠለምትና የራያ አካባቢዎችን " ይገባኛል " ጥያቄን በተመለከተ የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሚሰጠውን ውሳኔ እየተጠበቁ መሆናቸውን ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ለሪፖርተር ጋዜጣ በሰጡት ቃል አሳውቀዋል።
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ በአሁን ሰዓት የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ምክትል አስተዳዳሪ እና የሰላምና የፀጥታ መምርያ ኃላፊ በመሆን እያገለገሉ ሲሆን በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በፓርላማ በቀረቡበት ወቅት " ሁለቱ ክልሎች የሚዋሰኑባቸውን አካባቢዎች በሕዝብ ውሳኔና በሕጋዊ መንገድ መፍታት አለባቸው " በሚል ስለሰጡት አስተያየት ተጠይቀው መልሰዋል።
ኮሎኔል ደመቀ ዘውዱ ምን አሉ ?
" በወልቃይት ጉዳይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ውሳኔ እናደርጋለን ሲሉ በግልጽ አልሰማንም፡፡
ነገር ግን በሕጋዊ መንገድ ቢፈታ ይሻላል የሚለውን ምክር አዘል ነገር ለፓርላማው ሲናገሩ ሰምተናል፡፡
ግን በዚህኛው ቀጣና በዚህኛው ዞን ብለው ሲያነሱ እኔም በግል አልሰማሁም፣ እኛም የምናውቀው ነገርም የለም። ነገር ግን የወልቃይት ጉዳይ በየትኛው መንገድ ነው ሊፈታ የሚገባው የሚለውን ቀደም ሲል በተደጋጋሚ ተናግረናል፡፡
ሊፈታ በሚገባው መንገድ እንዲፈታ ለመንግሥት አመልክተናል።
ራያም፣ ጠለምትም፣ ወልቃይትም ስላሉ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለየትኛው እንደተናገሩ ግልጽ አልሆነልኝም። በግምት መልስ ለመስጠት ያስቸግራል።
ብዙ ሰው መላምት ሊኖረው ይችላል፡፡ ነገር ግን የወልቃይት ጉዳይ ሊፈታ የሚገባበትን መንገድ ጠቅሰን ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ስላቀረብን ውሳኔውን እየጠበቅን ነው።
በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ወቅትም ሆነ አሁን ከማኅበረሰቡ ጋር ነኝ ፤ የአገር መከላከያ ሠራዊት የወልቃይት አካባቢን እየተከላከለና እየጠበቀ እንዳለ ነው የምናውቀው።
በአካባቢው ከመከላከያ ጋር ምንም ዓይነት ጦርነት የለም፣ ተባብረን ነው እየሠራን ያለነው፡፡ አካባቢው ሰላማዊ በመሆኑ ፋኖ በሚል ምክንያት ምንም ዓይነት ግጭትም ሆነ ጦርነት የለም። "
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳዳር በበኩሉ የክልሉ አስተዳደራዊ ወሰን ከጦርነቱ በፊት ወደ ነበረበት እንዲመለስ፣ በጦርነቱ ምክንያት ከምዕራብ ትግራይና ከሌሎች የአማራ ክልል አዋሳኝ አካባቢዎች የተፈናቀሉ የክልሉ ነዋሪዎቸ በአፋጣኝ ወደ ቀዬአቸው እንዲመለሱ በተደጋጋሚ ጥያቄ እያቀረበ ነው፡፡
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5.0K views18:54