Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @addis_reporter
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.42K
የሰርጥ መግለጫ

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 7

2023-04-30 18:34:44 ነገ ሰኞ
በአዲስ አበባ መስቀል አደባባይ፣
አዳማ፣
ጅማ፣
ሐዋሳ እና
በድሬዳዋ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽ ሰላማዊ ሠልፍ ያካሂዳል።

ባህር ዳር እና ኮምቦልቻ ግን ከፀጥታ ችግር አኳያ የፓናል ውይይት ብቻ ይካሄዳል ተብሏል።

የአደባባይ ሰልፉ ለምን አስፈለገ??

በኑሮ ውድነት ምክንያት በሠራተኞች ላይ እየደረሰ ያለው ጫና መፍትሔ እንዲያገኝና ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል ምጣኔ እንዲሻሻል፣ በሰላማዊ ሠልፍ ጥያቄ ለመንግሥት እንደሚያቀርብ የኢትዮጵያ ሠራተኛ ማኅበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) አስታወቀ፡፡

‹‹ለሠራተኛው መሠረታዊ ጥያቄዎች አፋጣኝ መፍትሔ›› በሚል መሪ ቃል የዘንድሮውን ሜይዴይ በዓል ለማክበር የተነሳው ኢሰማኮ፣ ሊመለሱ የሚገባቸው አንገብጋቢ የሠራተኛው ጥያቄዎች በመደራረባቸው እንደሆነም ተገልጿል፡፡

‹‹በዘንድሮው የሜይዴይ በዓል በዋናነት የሚነሳው ጥያቄ የኑሮ ውድነት ነው፡፡ በሁለተኛ ደረጃ ደግሞ ያስቀመጥነው ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲስተካከል ነው፤›› ያሉት የኢሰማኮ ፕሬዚዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ፣ ‹‹እነዚህ ወቅታዊ ጥያቄዎች በአስቸኳይ መፍትሔ እንዲያገኙ ይፈለጋል፤›› ብለዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት እየጎላ የመጣውን የሠራተኞች የመደራጀት መብት ጥሰት እንዲቆም ጭምር ጥያቄ ይቀርባል ሲሉም አስረድተዋል፡፡

የሠራተኛው በነፃ የመደራጀትና የመደራደር መብት በሕጉ መሠረት እየተተገበረ ባለመሆኑ፣ ሕግ እንዲከበር በአዲስ አበባና በሌሎች ከተሞች በአደባባይ በሚካሄዱ ሠልፎችና በፓናል ውይይቶች ለመንግሥት እንዲደርስ እንደሚደረግ አቶ ካሳሁን ለሪፖርተር ገልጸዋል፡፡

‹‹ኢሰማኮ ሊመለስልን ይገባል ብሎ የሚያቀርበው ሌላው ጥያቄ በቀድሞ የሠራተኛና ማኅበራዊ ሚኒስቴር፣ አሁን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር የወጣውን የሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች የ20/80 መመርያን የሚመለከት ነው፤›› ብለዋል፡፡

በዚህ መመርያ መሠረት ኤጀንሲዎች ለሚያስቀጥሩት ሠራተኛ ከኩባንያዎች ከሚያገኙት ገቢ 20 በመቶውን ለአስተዳደራዊ ወጪ በማስቀረት፣ 80 በመቶውን ለሠራተኞች መክፈል አለባቸው የሚለው ድንጋጌ እየተከበረ ባለመሆኑ፣ ይህም በሕጉ መሠረት ተፈጻሚ እንዲሆን ኢሰማኮ ጥያቄ ያቀርባል ብለዋል፡፡ ይህ መመርያ በአግባቡ ሊተገበር ባለመቻሉ ሠራተኞች በከፍተኛ ሁኔታ ችግር ውስጥ መሆናቸውን አቶ ካሳሁን ገልጸው፣ መንግሥት ለጉዳዩ ትኩረት ሰጥቶ የማስተካከያ ዕርምጃ መውሰድ ይኖርበታል ሲሉ አክለዋል፡፡

‹‹በተለይ ከኑሮ ውድነት ጫና ጋር የተያያዘውን ጉዳይ አጠናክረን የምናቀርብበት ነው፤›› ያሉት አቶ ካሳሁን፣ ከሠራተኛው ደመወዝ ላይ የሚቆረጠው የሥራ ግብር ጊዜውን የዋጀና የብር የመግዛት አቅምን ያላገናዘበ በመሆኑ በአስቸኳይ ይስተካከል ዘንድ ጥያቄ እንደሚቀርብ አስታውቀዋል፡፡

የሥራ ግብር ይቀነስ ብቻ ሳይሆን በትራንስፖርት ክፍያ፣ በውሎ አበልና በመሰል ክፍያዎች ላይ የሚጣሉ ፍትሐዊ ያልሆኑ ታክሶች በሠራተኛው ላይ ከፍተኛ ጫና በማሳደራቸው ሊስተካከሉ ይገባል ብለዋል፡፡

‹‹እስካሁን ሥራ ላይ ባለው ሕግ የሥራ ግብር የማይከፈልበት ከ600 ብር በታች ሲሆን፣ ከ600 ብር በላይ ያለው ግብር ይከፈልበታል፤›› ሲሉ ገልጠዋል።

ከውሎ አበል ክፍያ ጋር በተያያዘም አንድ ሠራተኛ ሲወጣ የሚከፈለው አበል ከ500 ብር በላይ ከሆነ ግብር ይጠይቅበታል፡፡ 500 ብር ለአልጋ፣ ለቁርስ፣ ለምሳና ለእራት ይበቃል ተብሎ ሕጉ የወጣ ቢሆንም፣ አሁን ካለው የኑሮ ውድነት አንፃር በቂ ስላልሆነ፣ መሻሻል ይኖርበታል ብለዋል ሲል ሪፖርተር አስነብቧል።

የነዳጅ ዋጋ ዝቅተኛ በነበረበት ጊዜ የወጣ አሠራር የነዳጅ ዋጋ እጅግ በጨመረበት በዚህ ወቅት፣ የቀድሞውን ሕግ ይዞ መጓዝ ፍትሐዊ አይደለም።ብለዋል።
(22/08/2015ዓም)

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.9K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 18:16:24
ቀጭን ነዎት?
በቅጥነትዎስ ይሳቀቃሉ?

በአጭር ጊዜ ውስት ክበደት መጨመር      
      እና ቅርፆን ማስተካከል ይፈልጋሉ?

ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ
      ክብደት መጨመር የሚረዳ

የምግብ ፍላጎት መጨመር የሚያስችል

  የቆዳን ጥራት እና ልስላሴ ለመጨመር
       የሚረዳ

ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤
      ለቀጭን ሰዎች የሚመከር

ለሴቶችም የተስተካከለ አቋም
      እንዲጎናፀፉ የሚያግዝ

ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን ፤
     
ያሉበት እናደርሳለን



-------------------------------
ለበለጠ መረጃ +251964593642
                             +251906495051
                             +251907495051

Telegram:     t.me/AM_CS
                            t.me/AM_CS1
                            t.me/AM_CS2
-------------------------------

ተጨማሪ የዘመኑ ምርጥ ምርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/+UTXVYbFomXPc4JFm
https://t.me/+UTXVYbFomXPc4JFm
1.0K views15:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 13:43:54
ይህንን ያውቆ ኖሯል ?

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ ከ1997 እስከ 2018 ባሉት ዓመታት ከፍተኛ የአህያ ቁጥር እድገት ካሳዩት አስር ሀገራት አንዷ ነበረች።

በጠቅላላ የአህያ ቁጥር ደግሞ በዓለም ቀዳሚውን ስፍራ እንደምትይዝ ተመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.3K views10:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 09:00:24
አረብ ኢምሬትስ የኮፕ 28 ጉባኤን በከፍተኛ ኃላፊነት እንደምታስተናግድ ገልጻለች

የሀገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኮኘ 28 ስብሰባ ለሀገር መሪዎች፣ ባለሀብቶች፣ ተመራማሪዎች እና ወጣቶች እንደወሳኝ መገናኛ ይሆናል ብሏል።

የስብሰባው አዘጋጅ ከሁሉም አካላት ጋር በመተባበር በአየርንብረት ለውጥ ጉዳይ ተጨባጭ ለውጥ የሚያመጣ አጀንዳ እያዘጋጀ ስለመሆኑም ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።

የኮፕ 28 ስብሰባ ኘሬዝደንት የሆነችው አረብ ኢምሬትስ የአየር ንብረት ለውጥን ለመቋቋም የተሟላ ስራ እየተገበረች ነው።
Al-ain

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.5K views06:00
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 08:05:14 በዓመት 80,000 ያገለገሉ የከባድ መኪና ጎማዎችን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውሉ የማድረግ አቅም ያለው ፋብሪካ ተመረቀ።

ፋብሪካውን በሸገር ከተማ አስተዳደር ገላን ከተማ ላይ የገነባው ዜድ ኤም ትሬዲንግ አክሲዮን ማህበር ነው።የከባድ መኪና ጎማ መልሶ ማቀነባበሪያ ፋብሪካው በአሁኑ ሰዓት በዓመት እስከ 30,000 ጎማዎችን መልሶ ጥቅም እንዲሰጡ ማድረግ የሚችል  ሲሆን በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር በዓመት 80,000 ያገለገሉ ጎማዎችን መልሶ ያቀነባብራል ተብሏል ።

ዜድ ኤም ትሬዲንግ የከባድ መኪና ጎማ ማቀነባበሪያ  ይህን ስራ በመጀመሩ  ሀገሪቱ ለአዲስ ጎማ ግዢ በየዓመቱ  ከምታወጣው  የውጪ ምንዛሬ እሰከ 50 ሚሊዮን ዶላር እንደሚያስቀር በምርቃት ስነስርዓቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል።ፋብሪካው በ5,000  ካ.ሜ መሬት ላይ ያረፈ  ሲሆን አጠቃላይ ፕሮጀክቱ 150 ሚሊዮን ብር ወጥቶበታል ተብሏል።

ለጊዜው ለ100 ስዎችም የስራ እድል እንደተፈጠረላቸው ሰምተናል።በአሁኑ ሰዓት አንድ አዲስ የከባድ ተሽከርካሪ ጎማ ገበያ ላይ እስከ 40,000 ብር ይሸጣል የተባለ ሲሆን ዛሬ የተመረቀው ፋብሪካ መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያደርገው አንዱ ጎማ  ከ19,000 ብር በታች ይሸጣል ተብሏል።

ለአዲስ ጎማ የሚሰጠውን ዋስትናም ኩባንያው እንደሚሰጥ የተናገረ ሲሆን መልሶ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚደረገው ጎማ የአዲሱን ያህል የአገልግሎት አቅም አለው ተብሎለታል ።ፋብሪካው ያገለገሉ የከባድ መኪና ጎማዎችን መልሶ ለማቀነባበር ከየቦታው ፣ከባለንብረቶች እንደሚሰበስብ ሲነገር ሰምተናል።ፋብሪካውን የሸገር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ አቶ ጉዮ ገልገሎ መርቀውታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.3K views05:05
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-30 08:04:47
ታላቅ የምስራች

ጊዜውን የዋጀ ዘመናዊ የመኖሪያ አፓርትመንት በ 500 ሺ ብር ቅድመ ክፍያ ብቻ

በዚ ገንዘባችን እየወደቀ በሄደበት ጊዜ ብልህ ሰው ገንዘቡን ቤት ላይ ኢንቨስት ያረጋል ፤ ንብረቱም በየጊዜው ዋጋውን እየጨመረ የሚሄድ ንብረት ይሆናል

ለመኖሪያ ቢሉ ለኢንቨስትመንት ትክክለኛው ቦታ

በመሐል ከተማ ቦሌ - አትላስ እንዲሁም CMC ዋናው አስፓልት ዳር

ከልዩ የበዓል ቅናሽ ጋር

በተለያየ የካሬ አማራጭ ይዘን ቀርበናል

ባለ አንድ መኝታ 81 ካሬ

ባለ ሁለት መኝታ ከ 106 ካሬ - 160 ካሬ

ባለ ሦስት መኝታ ከ 182 ካሬ - 216 ካሬ


በተጨማሪም ለንግድ የሚሆኑ ሱቆችን በተለያየ የካሬ አማራጭ ያገኛሉ ።

ልዩ የሚያረገን ሁሉም ሽያጮቻችን በኢትዮጵያ ብር ማከናወናችን (የዶላር ጭማሪ ደንበኛን አይመለከተውም)

አጋጣሚውን በመጠቀም በየጊዜው ዋጋው እየጨመረ የሚሄድ ንብረት ላይ ገንዘቦን ኢንቨስት ያድርጉ ።

ይፍጠኑ ይደውሉ ቀድመው በመያዝ ተጠቃሚ ይሆናሉ!

0949504843 / 0927435224
4.2K views05:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 21:41:17
#ሰበር_መረጃ!

መከላከያ ዛሬ ሚያዝያ 21 /2015 ዓ.ም በጎንደር ጀግናው አርበኛ መሳፍንት ተስፉ ላይ ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ጀምሮ ተኩስ ከፍቷል! መላው የአማራ ሕዝብ በተለይም የጎንደር አካባቢ አማራ የተለመደ ውን ጀግንነትህን ለመድገም እንድትነሳ ጥሪ ተላልፏል።

መረጃው የአማራ ፋኖ አንድነት በጎንደር ነው!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.9K views18:41
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 19:45:44
የሰሜን ኮሪያ መሪ  እህት ኪም ዮ-ጆንግ የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ጆ ባይደንን " የወደፊት ዕቅድ የሌላቸው  ሽማግሌ መሪ  በማለት " ጠርታቸዋለች።

ሰሜን ኮርያ  የኑኬለር ጥቃት የምታደርስ  አሜሪካ  አሁን ያለውን አገዛዝ ልታከስም ትችላለች  በማለት የአሜሪካው ፕሬዝዳንት   ጆ ባይደን   በቅርቡ አስተያየት መስጠታቸው ይታወቃል።

ለዚህ ምላሽ የሰጡት ሰሜን ኮሪያ መሪ ኪም ጆንግ-ኡን እህት ኪም ዮ-ጆንግ " እኚ ናቸው አሁን የአሜሪካ መሪ?   በጣም ያሳዝናል።  የወደፊት  ዕቅድ  የሌላቸው ሽማግሌ መሪ ናቸው" በማለት ተናግራለች ሲሉ የሀገሪቱ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
5.0K views16:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 20:09:22
በጦርነት ይብቃ
ሰላም ይፅና መርሃግብር ላይ ጌታቸው ረዳ የተናገረው

"የፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት እንዲፋጠን የጠሚ አብይ አህመድ ቁርጠኝነት የሚደነቅ ነው። አሁንም የጠቅላይ ሚኒስትሩ ፈጣን እርምጃዎች የተጀመረውን ሰላም ዘላቂ ለማድረግ መስራት አለበት እላለሁ።

የትግራይ ህዝብ ጦርነት ሰልችቶታል። ከማንም ጋር ጦርነት መግባት አንፈልግም። ከአማራም ከአፋርም የሚያቀራርብ እንጂ የሚያቃቅር ነገር የለንም።

ትናንት በአፋር በኩል የሰላም ባስ አገር አቋራጭ አልፏል። ሐጂ አወል ይህንን ለማጠናከር መስራት ይገበዋል።

በተመሳሳይ ከአማራ ክልል ጋር በተያያዘም ዶክተር ከፋለ ኃላፊነት ወስደህ መስራት አለብህ ለማለት እፈልጋለሁ።

ዶክተር አብይ በጀመረው እጁ በሌሎች አካባቢዎች የሚታዩ ግጭቶችን በሆደ ሰፊነት ለመፍታት መስራት እንደለበት ለመጠቆም እፈልጋለሁ!

በመጨረሻ ከይዋጣልን መንፈስ ወጥተን የፍቅር፣ የስራ ቋንቋ መጀመር አለብን። ሰላም እንዲፀና የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መንግስት የበኩሉን ይሰራል"

አቶ ጌታቸው ረዳ
የትግራይ ክልል ጊዚያዊ መስተዳድር ፕሬዚደንት

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
1.9K views17:09
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-23 19:32:45
እውነተኛ ጥቆማ!

የእውነት ምንም ውሸት አልተቀላቀለበትም
በትኩሱ ስለወቅታዊ ጉዳይ ፈጣን እና ታማኝ መረጃ ለማግኘት ይሄንን  ቻናል ዝምብላቹህ ተቀላቀሉ!!

እስኪ አንዴ ከታች ያለውን ሊንክ በመጫን join

https://t.me/+NQ96aCgCktQ0MDg0
https://t.me/+NQ96aCgCktQ0MDg0
2.1K views16:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ