2023-04-23 09:06:26
የግብፆች ርግማን ወደ ሔሚቲ እና ቢን-ዛይድ
የግብፅ ማህበራዊ ሚዲያዎች ወደ ሱዳን መጮህ ጀምረዋል። በሱዳኑ ጦርነት ውስጥ አንደኛውን መልአክ ሌላኛውን በተቃራኒው አድርገው በመሳል በዲጂታሉ ዘርፍ ዘምተዋል። የውጭ ሃያላን የሚዘውሩት ጦርነት መሆኑን ሱዳኖች ጠንቅቀው የሚያውቁት ነው። የግብፅ ሰዎች ዛሬ ነገሩን እንዳዲስ በማጉላት አልቡርን ከሱዳናዊያን ድጋፍ እንዲሰጠው ተማፅኗቸውን እያሰሙ ናቸው። ከውጭ ሀገራት ደግሞ አረብ ኢማራትንና እና ኤርትራን ያጠለሻሉ። ከመሳሪያ እስከ ወታደር በማቅረብ ይወነጅሏቸዋል። ቻድ፣ ሊቢያ እንዲሁም በስም ያልጠቀሷቸው ሀገራትንም አንድ ላይ አስገብተው እየረገማቸው ነው። ይህ ዘመቻ ለሱዳኖች "..አይናችሁን ጨፍኑ፣ ላሞኛችሁ.." እንደ ማለት ነው።
በአዲሱ የካይሮ ዲጂታል ጩኸት የሙሐመድ ሐምዳን ዳጋሎ ( ሔሜቲ) ፈጣን ድጋፍ ሰጪ RSF ኃይሎች በተለያዩ ግንባሮች ያስመዘገበውን ድል ተከትሎ የመጣ ነው። የአልቡርሐን ሰራዊት SAF ከአባይ በስተምስራቅ በሚገኝ የ RSF ኃይሎች ላይ የሰነዘረውን ጥቃት ተከትሎ በአፃፋው ከፍተኛ ርምጃ መውሰዱን ቡድኑ ገልጿል። በዚህ ማጥቃት ባላንጣውን እስከ ጦር ካምፑ ስለማሳደዱ ያስታወቀ ሲሆን ባሕሪ ከተማ ውስጥ ደግሞ 60 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ከነሙሉ ትጥቃቸው መማረካቸውን፣ 10 ወታደራዊ ተሽከርካሪዎችን ማውደመማቸውን GeoConfirmed በተደረገ ቪዲዮ በይፋ አሳይተዋል። ቪዲዮው በአልቡርን የሚመራውን ሐሱዳን ወታደራዊ ኢንዱስትሪያልዜሽን ፋብሪካ ከዋና መስሪያ ቤቱ በቁጥጥር ስር ሲያውሉ ጭምር ያሳያል።
ይህን ተከትሎ አልሲሲ በቢን ዛይድ ላይ ከጀመረው ለቅሶ ባሻገር የአቡ ዳቢ ጂኦፖለቲካል ተቀናቃኟ ሳዑዲ አረቢያም ብስጭቷን መደበቅ አልቻለችም። ከመሸ የሚወጡ መረጃዎችም ይህንኑ የሚጠቁሙ ሲሆን ሪያድ በሀገሯ የሚገኙ የኢማራት ድርጅቶች ላይ እገዳ ጥላለች እየተባለ ይገኛል።
[ ሳዑዲ ይህን መሰል የበቀል ርምጃ ከጀመረች በተዘዋዋሪ እኛንም መነካካቱ የማይቀር ነው ]
ወደዛሬው የካይሮ ዘመቻ ይዘት እንመለስና በፅሁፉ የተካተቱት ማጭበርበሪያዎችን እንመልከት። ፅሁፉ የሚረግማቸው ሀገራት የመኖራቸውን ያህል የሱዳኑ ጦርነት የሕዝብ አሰፋፈርን የመለወጥ Demographic Change ለማድረግ የተጠነሰሰ ሴራ ነው ይላል። ይህ ወቀሳ ደግሞ በሔሜድቲ በኩል አርጎ የተባበሩት አረብ ኢማራት የነደፈችው ነው ይላል። እዚጋ በሱዳን የ Denographic Change ሴራ እየተከናወነ የሚገኘው በማን በኩል ነው? ብሎ መጠየቅ ተገቢ ነው። እውነታው ግን የግብፅ የስለላ ድርጅት ነው በሱዳን የ Demographic Change ሴራ ላይ የሚገኘው። ይኸው የግብፅ የስለላ ተቋም EGIS 15 ሚሊዮን የሚደርሱ እጅግ አክራሪ የተባሉ የ ፉላኒ እና ሃውሳ ሕዝቦችን ከናይጄሪያ ድረስ በማንቀሳቀስ ሱዳን ውስጥ ራስ ገዝ መንግስት እንዲመሰርቱ ሁኔታዎችን እያመቻቸ ነው የቆየው። ይህ የካይሮ ፕሮጀክት ከአልቡርሐን ጋር የሚደረግ ሲሆን ለሔሜቲ ደግሞ ስጋት ፈጥሮ የቆየ ነበር። በዚሁ ዙሪያ ሄሚቲ ንግግር ማድረጉ የሚታወስ ሲሆን ይህ የግብፅ ፕሮጀክተር ቀይ መስመር ነው" ማለታቸውም ይታወሳል። (ቀደም ሲል በዚሁ ዙሪያ ፅሁፍ አጋቼያለሁኝ)።
የሕዝብ አሰፋፈር ለውጥን ለበጎ ሳይሆን ለፖለቲካዊ ተንኮል በሱዳን የምትተገብረው ካይሮ ይህን ለማሳካት ቀደም ባሉ ዘመናት በተለይም በሱዳኑ ኑሜሪ ዘመነ ስልጣን ወቅት ከሀገር ተሰድደው የቆዩ አንዳንድ የአረብ ጎሳ አባላት በተመረጡ ቦታዎች መልሶ በማስፈር ነበር ግብፅ ስትሰራ የቆየችው።
በበርካታ ምሁራን እንደተገለፀውም እነዚህ በካይሮ የሰፈራ ፕሮጀክት ስር ታላሚዎች በኢትዮጵያውያንና በኤርትራውያን ላይ ከፍተኛ ጥላቻን ያነገቡ ናቸው። ሕዝቦቹ በኢትዮጵያ እና በኤርትራ ድንበር ላይ እንዲሰፍሩ ስራ ላይ የቆየችው ግብፅ ሂደታዊ ግቧ የሚያስጠላ ሰይጣናዊ አላማ የነደፈችለት ነው።
ዝርዝር ብዙ ነውና በዚህ ፅሁፍ የሚቋጭ አይሆንም ለጊዜው ግን ሔሜድቲ የካይሮን የሴራ ካብ ማንደድና ማፍረሱ እየተስተዋለ ሲሆን የግብፅ ብቸኛው የጦር መሳሪያ ደግሞ Disinformation በመሆኑ ባለቻቸው አማራጭ ሱዳኖችን ለማሞኘት እየተንደፋደፉ ናቸው። ጆሮ የሚሰጣቸው ሱዳናዊ ማግኘት ዘበት ቢሆንም..። ግብፅ ለዘመናት በሱዳን ላይ ምን ያህል የክህደት ተግባራት እንደፈፀመችባቸው ሱዳኖች ጠንቅቀው መረዳት በመጀመራቸው። ከሱዳናዊ ወንድሞቼ ጋር ለአመታት በዲጂታሉ አውድ የነበረኝ ውይይትም ይህንኑ ሐቅ ስለሚያስረግጥ .... ሱዳኖችም ድጋሚ በግብፅ የውሸት ዘመቻ ስለማይሸወዱ...!!
ሰላም ለሱዳናዊያን
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.7K views06:06