Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @addis_reporter
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.42K
የሰርጥ መግለጫ

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 10

2023-04-21 21:30:20
መረጃ/አፈና!

በረቡዕ ገብያ ከተማ በቡድን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በመስራት ላይ የነበሩ ወጣቶች ታፍሰው ታሰሩ

በምስራቅ ጎጃም ዞን ስናን ወረዳ ረቡዕ ገብያ ከተማ የሚገኙ ወጣቶች በቡድን የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ለምን ትሰራላችሁ በሚል ነው ትናንት ጠኋት ታፍሰው የታሰሩት።

..የአካል ብቃት እንቅስቃሴ በቡድን መስራት በየትኛውም የሀገር አቀፍም ሆነ የዓለም አቀፍ ህግ ወንጀል ሆኖ አያውቅም፤ስለዚህ ልንታሰር አይገባም" ብለው የጠየቁ ወጣቶች በፀጥታ አካላት መደብደባቸው ታውቋል።

ከ30 በላይ ወጣቶች በአንዲት ጠባብ ክፍል ታጉረው እንደሚገኙ ገልፀው፣ምግብና ውሃ ይዞ የሚመጣን አካል ፖሊሶቹ እየከለከሉ እና እያሰሩ መሆኑ ተገልጿል።በትናንትናው ዕለት ምግብ ሊያደርስ የሄደ ወጣት መታሰሩንም ተነግሯል።

ይህን ግፍ የአማራ እና የኢትዮጵያ ህዝብ እንዲሁም የዓለም አቀፍ ማህበረሰቡ ይወቅልን ብለዋል።

ምንጭ :- መረጃ ቲቪ

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.0K views18:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 21:29:11
ቀጭን ነዎት?
በቅጥነትዎስ ይሳቀቃሉ?

በአጭር ጊዜ ውስት ክበደት መጨመር      
      እና ቅርፆን ማስተካከል ይፈልጋሉ?

ከአንድ ወር እስከ 45 ቀን ዉስጥ
      ክብደት መጨመር የሚረዳ

የምግብ ፍላጎት መጨመር የሚያስችል

  የቆዳን ጥራት እና ልስላሴ ለመጨመር
       የሚረዳ

ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት የሌለዉ ፤
      ለቀጭን ሰዎች የሚመከር

ለሴቶችም የተስተካከለ አቋም
      እንዲጎናፀፉ የሚያግዝ

ለወንዶችም ለሴቶችም የሚሆን አለን ፤
     
ያሉበት እናደርሳለን



-------------------------------
ለበለጠ መረጃ +251964593642
                             +251906495051
                             +251907495051

Telegram:     t.me/AM_CS
                            t.me/AM_CS1
                            t.me/AM_CS2
-------------------------------

ተጨማሪ የዘመኑ ምርጥ ምርቶችን ለማግኘት ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/+UTXVYbFomXPc4JFm
https://t.me/+UTXVYbFomXPc4JFm
1.7K views18:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 20:42:01
#እንድታውቁት

የኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በጦርነት ምክንያት ተቋርጦ የቆየውን የመማር ማስተማር ሂደት ለማስቀጠል በዝግጅት ላይ እንደሆነ ገልጿል።

በመሆኑም በሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ትምህርታቸውን እየተከታተሉ #የማይገኙ ሁሉም የዲግሪ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን፣ ክረምት) እንዲሁም የማስተርስ (መደበኛ፣ ኤክስቴንሽን ፣ ክረምት) ተማሪዎች ከዚህ በታች ባለው ሊንክ እንዲመዘገቡ ጥሪ ቀርቧል።

ሊንክ ፦ http://196.190.28.50

ምዝገባው የሚያበቃበት ቀን ሚያዚያ 18 ቀን 2015 ዓ/ም መሆኑን ተቋሙ አሳውቋል።

ለበለጠ መረጃ ደግሞ ዘውትር በየስራ ሰአት በሚከተሉት ቁጥሮች መወደወል ይቻላል ፦ 0914485592 / 0921990158

ከኣክሱም ዩኒቨርሲቲ በተጨማሪ #የራያ_ዩኒቨርሲቲም በጦርነት የተቋረጠውን መደበኛ ትምህርት ለማስቀጠል እየሰራ ይገኛል።

በዚህም ከ2ኛ እስከ 5ኛ ዓመት በራያ ዩኒቨርሲቲ መደበኛ ትምህርት ሲከታተሉ የነበሩና ወደ ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎች ተመድበው የመማር እድል ያላገኙ ተማሪዎች ከ09/08/2015 ዓ/ም እስከ 13/08/2015 ዓ/ም ባሉ የስራ ቀናት እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርቧል።

ተማሪዎች የሚመዘገቡት ለዩኒቨርስቲው ረጅስትራር እየደሉ ሲሆን የስልክ ቁጥሮቹ 0970140000፣ 0970240000 ፣ 0970230000 ናቸው። ተማሪዎች ዘውትር በስራ ሰዓት ብቻ እንዲደውሉ ጥሪ ቀርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.0K views17:42
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 14:56:28
ዶ/ር ወንድወሰን አሰፋ አዲስአበባ ሶስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መታሰሩን ጋዜጠኛ መዓዛ መሀመድ ገልፃለች! በመንግሥት ደህንነቶች ጎንደር ላይ አፈና ከተደረገበት አምስተኛ ቀኑን ቢይዝም እስካሁን ፍርድ ቤት እንዳላቀረቡት ተናግሯል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.0K views11:56
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 11:14:23
#ባህርዳር

የባህር ዳር ከተማ የእስልምና ምዕመናን የረጅም ጊዜ ጥያቄ የነበረው የመስገጃ ቦታ ጥያቄ ምላሽ ማግኘቱ ተሰማ።

የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር ለእስልምና እምነት ተከታዮች ለመስገጃ የሚሆን 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ መሰጠቱን ዛሬ አስታውቋል።

የከተማው ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ድረስ ሳህሉ (ዶ/ር) ዛሬ የኢድ አልፈጥር በዓል በባህር ዳር ስታዲየም በሚከበርበት ወቅት ነው ይህንን የምስራች ለምዕመኑ ያበሰሩት።

ዶ/ር ድረስ ሳህሉ ምን አሉ ?

" ለብዙ ጊዜ ስትጠይቁት የነበረ የመስገጃ ቦታ አሁን በክልልም ፀድቆ የመጣ ስለሆነ ምናልባትም በሚቀጥለው ዓመት በደንብ ሰርታችሁት እዚህ ሳይሆን እዛው ከተፈቀደላችሁ ቦታ ላይ የምታከብሩት ይሆናል።

ክልሉ ያቀረባችሁትን ጥያቄ እኛ አፅድቀን ልከን ክልሉም ተቀብሎት 20 ሺህ ካሬ ሜትር ቦታ የኢድ አልፈጥር በዓል የምናከብርበት ቦታ ተፈቅዷል። "

ከንቲባው ይህንን ንግግራቸውን ሲያደርጉ የባህር ዳር ከተማ ሙስሊም ምእመን እጅግ በደስታ ስሜት " አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! አላሁ አክበር ! " እያለ ድምፁን አሰምቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.4K views08:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 10:20:41
ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የሱዳን ጦርነት ዛሬም በኢድ አልፈጥር በዓል እንደቀጠለ ነው።አል ቡርሃን ጦርነቱ ከተጀመረ ወዲህ ትናንት አመሻሽ ካልታወቀ ቦታ ሆነው መግለጫ ሰጥተዋል።
   
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.1K views07:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 10:19:01
#UPDATE

ቅዱስ ሲኖዶስ ያቋቋመው የሰላም ልኡክ በቀጣይ ሳምንታት ወደ ትግራይ ክልል ሊጓዝ ነው።

ይኸው የሰላም ልዑክ ትላንት መግለጫ ሰጥቷል።

በመግለጫውም ፤ በሰሜን ኢትዮጵያ ጦርነት ምክንያት በመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ሥር በትግራይ በሚገኙ አኅጉረ ስብከት መካከል የነበረው ግንኙነት መቋረጡን አስትውሷል።

በትግራይ ክልል የተፈጠረውን አንጻራዊ ሰላም ተከትሎ በቅዱስ ሲኖዶስ በኩል በትግራይ ከልል ለሚገኙ ብፁዓን አባቶች የግንኙነት ማስቀጠያ ደብዳቤዎች ሲጻፉ መቆየታቸውንም ገልጿል።

ልኡኩ የደብዳቤው ግንኙነት እንደታሰበው የተፈለገውን ውጤት ባለማምጣቱ ምክንያት ፤ ቅዱስ ሲኖዶስ ከብፁዓን አባቶች፣ ከሊቃውንተ ቤተክርስቲያን ፣ ከታዋቂ ሰዎችና ከምዕመናን የተወጣጣ ኮሚቴ በቅዱስ ሲኖዶስ መሰየሙን አመልክቷል።

ልዑኩ " የኮሚቴው ዓላማም የሰላም መድረክ ማመቻቸት፣ የምንቀራረብበትና አንድ የምንሆንበትን መንገድ በጋራ ማፈላለግ ነው " ያለ ሲሆን ከጉዞ ጋር በተያያዘ ማሟላት ያሉባቸውን ጉዳዮች ለማሟላት ሲባል ከሚያዝያ 12 ቀን 2015 ዓ/ም ጀምሮ ሊደረግ የነበረውን ጉዞ ማራዘሙን አሳውቋል።

ልኡኩ በሚቀጥሉት ሳምንታት ወደ ክልል ትግራይ በመጓዝ በቅዱስ ሲኖዶስ የተሰጠውን ኃላፊነት የሚወጣ መሆኑን ትላንት በሰጠው መግለጫ አረጋግጧል።

መረጃውን ከEOTC TV ነው ያገኘነው።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.8K views07:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 08:25:04
የዒድ አልፈጥር በዓል እየተከበረ ነው

የ2015 ዓ.ም የዒድ አልፈጥር በዓል በእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት እየተከበረ ነው።

1 ሺህ 444ኛው የዒድ አልፈጥር በዓል በመላው ኢትዮጵያ በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የፌዴራል ጠቅላይ ሼሪዓ ፍርድ ቤት በዓሉ የሰላም፣ የደስታ፣ የመተዛዘን እና የመረዳዳት እንዲሆን የመልካም ምኞት መልዕክት አስተላልፏል።

በታላቁ የረመዷን ወር መጨረሻ የሚከበረውን የዒድ አልፈጥር በዓልን በሰላምና በመተሳሰብ እንዲሁም የተቸገሩ ወገኖችን በማገዝ ማሳለፍ እንደሚገባም ጥሪ አቅርቧል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.5K views05:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 13:18:49
የኦሮሙማ ፋሽስታዊ አገዛዝ የ190 አማራዎችን ስልክ አስጠልፎ እየተከታተለ ነው!

ይሔ የኦሮሙማ ፋሽዝም ስልካቸውን ያስጠለፋቸው  አማራዎች  የአማራ ብልፅግና አመራሮች ፣ የአብን ምክር ቤት አባላት ፣ የታወቁ የአማራ ባለሀብቶች ፣ የኃይማኖት አባቶች፣ ሌሎች ታዋቂ ግለሰቦችን ያካተተ ነው።

ይሔንን የአማራዎች ስልክ ጠለፋ እና ክትትል እየሠሩ የሚገኙት አርቴፊሻል ኢንቴሌጀንስ ፣ ኢንሳ ፣ መከላከያ ሚኒስቴር እና ጠቅላይ ሚኒስትር ፅ/ቤት ያሉ ቡድኖች ናቸው። የMeta access መብት የጠየቀው የፋሽስቱ አብይ አሕመድ አገዛዝ የwhatsup ፅሑፍ ውይይቶችን ለመሰለል እየሠራ ይገኛል።

ይሔ በአማራ ደም የጨቀዬ ሰው በላ ፋሽስት ፣ በንፁሐን ደም ላይ በፈፀመው ግፍ  ሕዝብ አንቅሮ ተፍቶታል።  እናም ከእለት ወደእለት ወደመቃብሩ እየተቃረበ ያለው የኦሮሙማ ፋሽዝም አገዛዝ  ስልክ በመጥለፍ የሚያስቀረው የሕዝብ ትግል የለም!!

ዳጆቻችን ዓለም የፈጠራቸውን የቴክኖሎጂ እድሎች ሁሉ በመጠቀም አረመኔያዊው አገዛዝ የፈለገውን የቴክኖሎጂ አፈና ባዶ የሚያስቀር ወርቃማ ዘመን ላይ በመሆናችን በሁሉም ረገድ ትግላችንን አጠናክረን መስሬት ይኖርብናል።

በአማራ ልጆች የሞላቸው እሥርቤቶች፣ በአማራ ተፈናቃዮች የሞላቸው ከተሞች መቀበሪያዎቹ ይሆናሉ !!

መረጃው:-የሙሉጌታ አንበርብር ነው!

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
2.3K views10:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 12:46:26
አዳዲሶቹ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የንግድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ብሮድካስት አገልግሎት ጣቢያ ለመጀመር ፈቃድ ለጠየቁ አምስት አዳዲስ የቴሌቭዥን ጣቢያዎች ፍቃድ መስጠቱን አስታውቋል።በዚህም መሰረት:—

1/ ለጎህ ቴሌቪዥን

2/ ለኤፕላስ ቲቪ

3/ ለሸካል ቲቪ

4/ ለከገበሬው ቴሌቪዥን እና

5/ ለኢሲኤን ቴሌቪዥን የንግድ የሳተላይት ቴሌቪዥን ብሮድካስት አገልግሎት ፈቃድ እንዲሰጣቸው በባለሥልጣኑ ፍቃድ ማግኘታቸው ተገልጿል።

አመልካቾች በባለሥልጣን መ/ቤቱ በመቅረብና ውል በመዋዋል ፈቃድ እንዲወስዱም የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን በይፋዊ ገፁ አሳውቋል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
2.4K views09:46
ክፈት / አስተያየት ይስጡ