Get Mystery Box with random crypto!

አዲስ ሪፖርተር - NEWS

የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የቴሌግራም ቻናል አርማ addis_reporter — አዲስ ሪፖርተር - NEWS
የሰርጥ አድራሻ: @addis_reporter
ምድቦች: ዜና
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 40.42K
የሰርጥ መግለጫ

🔖 ይህ የአዲስ ሪፖርተር የቴሌግራም ገፅ ነው !
=> በቻናሉ
📌 ፈጣን ፥
📌 ትኩስ ፥
📌 ወቅታዊ እና
📌 አዳዲስ መረጃዎች እንደወረዱ በቅፅበት ፥ በትኩሱ ይደርሳችኋል !
🔖 ይወዳጁን ፤ በእርግጥም ይወዱታል !
For promotion @Addis_reporter_bot
#ADDIS ABABA, ETHIOPIA

Ratings & Reviews

4.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

1

2 stars

0

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 206

2022-05-12 23:28:13
ለእግር ኳስ አፍቃሪያን የተከፈተ ምርጥ ቻናል
LIVE ትኩስ ትኩስ ስፖርታዊ መረጃ የዝውውር ዘገባ ምን አለፋዎት ሁሉንም በአንድ እዚህ ያገኛሉ ይቀላቀሉን
https://t.me/+H2MPRPLiI4o3YjNk
https://t.me/+H2MPRPLiI4o3YjNk
1.2K views20:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 23:01:28
ልዩ መረጃ

ከሀዲው እና በአማራ ስም የሚነግደው ካሳ ተክለብርሀን አማራን ለሁለተኛ ጊዜ ሊሸጥ መሆኑ በውስጥ መረጃ ተደረሰበት ።ከዚህ በፊት ወልቃይት እና ሁመራ የትግራይ ነው ይህ በህገመንግስቱ የተዘጋ ነው ብሎ በአማራ ላይ ሲያላግጥ የነበረው ካሳ ተክለብርሀን ዛሬ ደግሞ በተቃራኒው ህወሀቶችን ወልቃይትን ለአማራ ስጡና ከአማራ ጋር አስታርቃቸሗለሁ እያለ ይገኛል።

ከሀዲው ካሳ ተክለብርሀን የአማራዎችን ልብ እኔ አውቀዋለሁ አፋቸውን ማስያዝም እችላለሁ ብቻ እናንተ ወልቃይትን ለአማራ ስጡ በማለት ከህወሀቶች ጋር እየመከረ እንደሆነ የውስጥ መረጃዎች አጋልጠዋል። ካሳ ተክለብርሀን ቀንደኛ የህወሀት ተላላኪ የነበረና የአማራን ክልል ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ እና ደባ ሲሸርብ የነበረ ድልብ ወያኔ ዛሬም እንደለመደው በአማራ ህዝብ ላይ ቁማር እየቆመረ ይገኛል የቁማሩ ማስያዣም ወልቃይትን እንዳደረገ የውስጥ መረጃዎች አሳውቀዋል ።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
1.5K viewsedited  20:01
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 21:37:11 መረጃ
ወደ ጦርነትም ይሁን ወደ ማሰልጠኛ ተቋም አንገባም ያሉ የትግራይ ወጣቶችን ህወሃት በአዲስ መልኩ እንደልማዱ ማሰር ጀምሯል። በትግራይ ክልል የሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ጭምር የእስረኞች መቀመጫ አድርጎታል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
2.7K views18:37
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 20:52:07
ኣሸባሪው ህወሓት በማይጋባ ኣቅጣጫ ጦርነት ከፍቷል!

ኣሸባሪው ህወሃት በወልቃይት እና ሑመራ መካከል በሚገኘው ማይጋባ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በይፋጦርነት ከፍቷል።
በተመሳሳይ ትላንት ሌሊት በኣዲ ዓርቃይ ማያ ጊዮርጊስ አካባቢ ከፍተኛ ተኩስ ከፍቶ የነበረ ሲሆን፤በደባርቅ አዋሳኝ
ልዩ ስሙ አንበራ ወደ እሚባል አካባቢም ህወሃት መድፍ በመተኮስ በኣንድ ኣርሶ ኣደር ቤት ላይ ኣርፎ ኣንድ ሰላማዊ ሰው ህይወቱ ሲያልፍ የቆሰሉም መኖራቸው ታውቋል።
አሸባሪው ቡድን በባድመ ኣቅጣጫ ወደ ኤርትራ ከባድ መሳሪያ ሲተኩስ ያደረ ቢሆንም በኤርትራ ጦር ላይ የደረሰ
ጉዳት የለም። የኤርትራ ጦርም እስካሁን ምንም ኣይነት ምላሽ ኣልሰጠም።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.2K views17:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 20:28:05 መረጃ
በሰሜን ወሎ ዞን ፋኖን ትጥቅ ለማስፈታት የመንግስት ሰራተኞች ተባባሪ እንዲሆኑ የሚያትተው ሰነድ ተቃውሞ ገጠመው።
ውይይቱ በሰነድ የቀረበው በላስታ ወረዳ፣ በላሊበላ ከተማ፣ በአንጎት ወረዳ ሲሆን፣ መንግስት ሠራተኞች ይሄንን አንቀበልም በማለት መድረኩን ረግጠው መውጣታቸው ታውቋል።
ይህንን ያልተቀበለ የመንግስት ሠራተኛ ከስራው እንደሚባረርም መድረኩን የመሩት የወረዳና የዞን አመራሮች መዛትና ማስፈራራታቸው ተሰምቷል።
@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.2K views17:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:53:15 በህገ- ወጥ መንገድ 7 ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ዋለ

በህገ- ወጥ መንገድ ሰባት ሕፃናቶችን ሲያዘዋውር የተገኘው ግለሰብ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን የቤንች ሸኮ ዞን ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ።

ፖሊስ እንዳስታወቀው፥ ተጠርጣሪው ግለሰብ ከካፋ ዞን ጨና ወረዳ ባላ ሻሻ ቀበሌ ከአስር ዓመት በታች የሆኑ ሰባት ሕፃናቶችን ከሚኖሩበት ቤተሰብ ከብቶችን ትጠብቃላችሁ በማለት ወደ ቤንች ሸኮ ዞን ሸኮ ወረዳ ጉፍቃ ቀበሌ ግንቦት 1 ቀን 2014 ዓ/ም ከጠዋቱ 3:00 በተሽከርካሪ ህፃናቶቹን ይዞ በመጓዝ ላይ እንዳለ ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ እየተደረገበት ይገኛል።

ህብረተሰቡ ህፃናቶች በህገወጥ መንገድ ከቦታ ወደቦታ እያዘዋወሩ ለጉልበት ብዝበዛ የሚዳርጉ ግለሰቦችን ለህግ አካላት አሳልፎ መስጠት እንዳለበትም ፖሊስ ማሳሰቡን ከደቡብ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.8K views14:53
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 17:25:09 በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ ነገ እንደሚጠናቀቅ ኤጀንሲው ገለፀ!

በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ በተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያቀርቡ የከተማዋ የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጀማል ሀጅ እንደገለፁት፥ ለይዞታ ማርጋገጫ በተመረጡ 25 ቀጠናዎች እና 112 ሰፈሮች የሚገኙ የመሬት ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እያቀረቡ ነው፡፡

ኤጅንሲው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ሀሙስ ሚያዚያ 20 መቀበል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 6 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ11 ሺህ 300 በላይ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመለከቻዎችን ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡

የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ የመቀበል ሂደቱ እስከ ግንቦት 5 ብቻ የሚቆይ በመሆኑ በተመረጡ ቀጠናዎች እና ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ባለይዞታዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድና አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት የክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ባዘጋጁት ቦታ በመገኘት ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለ ይዞታዎች ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን ተገንዝበው ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ሃላፊው አሳስበዋል፡፡የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ አቀራረቡንና አመዘጋገቡን ሂደት የሚታዘቡ ከህብረተሰቡ የተመረጡ 336 ታዛቢዎች እየተሳተፉ መሆናቸው የኤጅንሲው መግለጫ አመላክቷል።

በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ማቅረቢያ ቀነ ገደብ ነገ እንደሚጠናቀቅ ኤጀንሲው ገለፀ!

በአዲስ አበባ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ በተሰጠው የጊዜ ገደብ እንዲያቀርቡ የከተማዋ የመሬት ይዞታ፣ ምዝገባና መረጃ ኤጀንሲ አሳሰበ፡፡የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር ኢንጅነር ጀማል ሀጅ እንደገለፁት፥ ለይዞታ ማርጋገጫ በተመረጡ 25 ቀጠናዎች እና 112 ሰፈሮች የሚገኙ የመሬት ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ እያቀረቡ ነው፡፡

ኤጅንሲው የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ ሀሙስ ሚያዚያ 20 መቀበል ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ባሉት 6 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ11 ሺህ 300 በላይ ባለይዞታዎች የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመለከቻዎችን ማቅረባቸውን ገልፀዋል፡፡

የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ የመቀበል ሂደቱ እስከ ግንቦት 5 ብቻ የሚቆይ በመሆኑ በተመረጡ ቀጠናዎች እና ሰፈሮች ውስጥ የሚገኙ ባለይዞታዎች ማንነታቸውን የሚገልጽ መታወቂያ፣ ፓስፖርት፣ መንጃ ፍቃድና አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት የክፍለ ከተማ ቅ/ጽ/ቤቶች ባዘጋጁት ቦታ በመገኘት ማመልከቻ እንዲያቀርቡ ጥሪ አስተላልዋል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ ባለ ይዞታዎች ኤጀንሲው አረጋግጦ ላልመዘገበው ይዞታ ምንም ዓይነት ህጋዊ ዋስትናና ከለላ የማይሰጥ መሆኑን ተገንዝበው ቀነ ገደቡ ከመጠናቀቁ በፊት የነቃ ተሳትፎ ማድረግ እንዳለባቸው ሃላፊው አሳስበዋል፡፡የይዞታ ይረጋገጥልኝ ማመልከቻ አቀራረቡንና አመዘጋገቡን ሂደት የሚታዘቡ ከህብረተሰቡ የተመረጡ 336 ታዛቢዎች እየተሳተፉ መሆናቸው የኤጅንሲው መግለጫ አመላክቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.7K views14:25
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 15:59:55 በአሜሪካ በኮቪድ ህይወታቸዉን ያጡ ሰዎች ቁጥር ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሆነ

ዋይት ሀውስ እንዳስታወቀዉ በዩናይትድ ስቴትስ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ሰዎች ከኮቪድ ወረርሽኝ ጋር በተያያዘ ህይወታቸዉን ማለፉን ይፋ አድርጓል፡፡ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ሀገሪቱ “በአሳዛኝ ምዕራፍ” እያለፈች ነው ያሉ ሲሆን እያንዳንዱ ሞት ደግሞ “የማይተካ ኪሳራ ነው” ሲሉ ገልጸዋል፡፡

Addis_Reporter
@Addis_Reporter
3.7K views12:59
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 13:38:59 በሶማሌ ክልል በባህላዊ የምርጫ ሥነ ሥርዓት ላይ በፀጥታ ኃይሎች የተፈጸመውን ግድያ ኢሰመኮ ኮነነ!

በሶማሌ ክልል ቦምባስ ከተማ በባህላዊ ሥነ ሥርዓት የጎሳ መሪ ለመምረጥ በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ በፀጥታ ኃይሎችና በታጠቁ ግለሰቦች በተፈጸሙ ጥቃቶች የ11 ሰዎች ህይወት መጥፋቱን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን (ኢሰመኮ) ኮነነ።በሶማሌ ክልል ከሚገኙት የሶማሌ ጎሳዎች መካከል የሆኑት የአኪሾ ጎሳ አባላት መጋቢት 11 እና 12 ቀን 2014 ዓ.ም. የጎሳ መሪያቸውን ለመምረጥ በተሰበሰቡበት ዕለት ከግድያ በተጨማሪ 33 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት መድረሱን ማረጋገጡን ኢሰመኮ ዛሬ ግንቦት 04/2014 ዓ.ም. ባወጣው የምርመራ ሪፖርቱ አስታውቋል።

ኢሰመኮ በስፍራው ተገኝቶ ባደረገውም ምርመራ የክልሉ መንግሥት የፀጥታ አካላት ከመጠን ያለፈ የኃይል አጠቃቀም ለሞትና ለአካል ጉዳት ምክንያት ሆኗል ብሏል።ኢሰመኮ በሁለቱ ቀናት ስለተፈጸሙ ግድያዎችና የአካል ጉዳቶች የደረሰውን ጥቆማ ተከትሎ በቦታው በመገኘት የዓይን ምስክሮችን፣ ተጎጂዎችን፣ የተጎጂ ቤተሰቦችን፣ የአገር ሽማግሌዎችን ማናገሩን አስታውቋል።

በተጨማሪም ከሆስፒታል ምንጮች መረጃ በማሰባሰብ እንዲሁም ፈቃደኛ የሆኑ የክልሉ ኃላፊዎችን በማነጋገር የምርመራውን ሪፖርት አጠናቅሯል።በተጨማሪም ቦምባስ ከተማ የሚገኝ የጥቃቱ ሰለባዎች የተቀበሩበትን መካነ መቃብር መጎብኘቱን ገልጾ በዚህም በመጀመሪያው ቀን የተገደሉ ሰዎች የተቀበሩበትን የጅምላ መቃብር እንዲሁም በሁለተኛው ቀን የተገደለች ሴት ተቀብራበታለች የተባለ መካነ መቃብር መመልከቱንም በዚሁ የምርመራ ሪፖርቱ አካቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.1K views10:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-05-12 13:23:11 ሰበር ዜና !

ህወሓት በወልቃይት እና በሁመራ መካከል በምትገኘው "ማይጋማ" በምትባል ሥፍራ ላይ በመሆን በሁለት አቅጣጫ ጦርነት ከፍቷል።

@Addis_Reporter
@Addis_Reporter
4.0K views10:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ