Get Mystery Box with random crypto!

Addis Ababa University

የቴሌግራም ቻናል አርማ aauethiopianuniversty — Addis Ababa University A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aauethiopianuniversty — Addis Ababa University
የሰርጥ አድራሻ: @aauethiopianuniversty
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 15.68K
የሰርጥ መግለጫ

Addis Ababa University|Seek Wisdom,Elevate your Intellect and Serve Humanity

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች

2023-06-17 08:10:13
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ 11 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ፥ ቀሪው 1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ኮምፒዩተሮች እና የህክምና መሳሪያ ቁሳቁሶች መሆናቸው ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ልዩ አማካሪ ኢንጅነር ውብአየሁ ማሞ እንደተናገሩት ዛሬ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው መሰል ድጋፎችን በቀጣይነት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ፥ በምርምርና ቴክኖሎጂዎች ረገድ በመልሶ ማቋቋሚያ ስራዎች ላይ የራሱን እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።
6.1K views05:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-09 16:44:58
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክቶችን አሸነፈ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ከሚደግፋቸው አስራ ሰባት (17) የምርምር እና የትምህርት ልህቀት ማዕከላት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘጠኙ አሸናፊ ሆነ።
ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ውጤት በመጪው ጥቂት ወራት የሚታወቅ ይሆናል።

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በ2022 November የARUA እና Guild የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በነበራቸው ስብሰባ በአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ የምርምር እና የ ትምህርት ልህቀት ማእከላት ለማቋቋም ወስነው መለያየታቸው ይታወሳል።
በዚሁ መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ፕሮፖዛሎች የቀረቡ ሲሆን ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ግምገማ መሰረት 17 የልህቀት ማእከል ተመስርተዋል። ከነዚህ የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክቶች ውስጥም በዘጠኙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊ ሆኗል።
 
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቶቹን በማሸነፉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ የሚያገኝ ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ይህ ውጤት ለአዲስ አበባ ዩኒርሲቲም ሆነ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል አለ ብለዋል፡፡  በተጨማሪም ለዚህ ውጤት አስተዋጽኦ ያደረጉ የዩኒቨርሲቲው ብርቱ ተመራማሪዎችን አመስግነዋል፡፡
 
3.3K views13:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-06-07 22:23:29
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በ 8 ወሳኝ ፕሮጀክቶች ከ አውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለማግኘት በብራስልስ ቤልጂየም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትን ጨምሮ 15 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎችና የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚደንቶች ከአውሮፓ ህብረት ጋር በሚደረገው ወሳኝ በሆነው ስብሰባ ላይ እየተካፈሉ ይገኛሉ ፡፡ ከቀረቡት 16 የልህቀት ማዕከላት መካካል በ 8ቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሳተፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ድጋፉን የሚያገኙት ፕሮጀክቶች በነገው እለት ይታወቃሉ፡፡ ይህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ሲሆን ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው እና ዋነኛው የ ዝግጅት ኣካል ተደርጐ ሊወስድ ይችላል።

በሌላ በኩል የአፍሪካን ችግር የሚፈቱ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚያስፈልግ ሰፊ መዋዕለ ንዋይ ድጋፍ ለማግኘት 16 የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ማህበርና የአውሮፓ ጊልድ ዩኒቨርሲቲ ማህበር እየተነጋገሩ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ የአሊያንስ ህብረቶች ከፍተኛ ምርምሮችን መደገፍ እንዲሁም የምርምርና ከፍተኛ ትምህርት መሰረተ ልማትን መገንባት፣ አሁን ለሚስተዋሉ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን በማመን የአውሮፓ ህብረት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት200 አፍሪካውያንን በፒኤች ዲ (PhD) ለማሰልጠን በሚችልበትን ሁኔታ ወሳኝ ወይይት እየተካሄደ ይገኛል።
5.4K views19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-17 13:35:37
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጥናታዊ የምርምር ፅሑፎች ህትመትና የማጣቀስ ምጣኔ ከሌሎች የሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በምስራቅ አፍሪቃ ካሉ ዩንቨርሲቲዎች እና እንደ አሀጉር ከ አፍሪቃ ያለው ደረጃ ምን ይመስላል ?

ዩንቨርሲቲው ከ ኢትዮጵያ እና ከምስራቅ አፍሪቃ የመጀመሪያ ደረጃን የያዘ ሲሆን ከአፍሪቃ ደግሞ በሶስተኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
 

(source:Research4Life)
11.4K views10:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 10:57:27
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በጥናታዊ የምርምር ፅሑፎች ህትመትና የማጣቀስ ምጣኔ ከሌሎች የሀገር በቀል ዩኒቨርሲቲዎች እንዲሁም በምስራቅ አፍሪቃ ካሉ ዩንቨርሲቲዎች እና እንደ አሀጉር ከ አፍሪቃ ያለው ደረጃ ምን ይመስላል ?

ዩንቨርሲቲው ከ ኢትዮጵያ እና ከምስራቅ አፍሪቃ የመጀመሪያ ደረጃን የያዘ ሲሆን ከአፍሪቃ ደግሞ በሶስተኝነት ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
 

(source:Research4Life)
3.1K views07:57
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 06:18:25
ለመላው እስልምና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለ 1444 ኛው ዓመተ ሂጅራ ኢድ ኣልፈጥር በዓል በሰላም አደረሳችሁ።

በዓሉ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ የሠላም፣የፍቅር፣የጤና እና ደስታ የተሞላበት መልካም በዓል እንዲሆንልዎ ዩኒቨርስቲው ይመኛል!!

መልካም በዓል!!
የአአዩ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት::
2.4K views03:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-16 13:54:11
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐና ከምክትል ፕሬዝዳቶች ጋር በመሆን የፋሲካ በዓልን አስመልክተው ከተማሪዎች ጋር የምሳ ማዕድ አብርው አድርገዋል ::

ፕረፌሰር ጣሰወልደሐና
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት
2.8K views10:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-15 15:18:00
ለመላ የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ
እንኳን ለብርሃነ ትንሳኤዉ በሰላም አደረሳችሁ!
በዓሉ ብሩህ ተስፋን የሰነቀ የሠላም፣የፍቅር፣የጤና እና ደስታ የተሞላበት
መልካም የትንሳኤ በዓል እንዲሆንልዎ ዩኒቨርስቲው ይመኛል!!
መልካም በዓል!!
የአአዩ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት
3.8K views12:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 18:02:24
የሠላም ሥምምነቱ የአፍሪካ የመሪነት ሚና ጥቅም የታየበት መሆኑን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል የተከሰተውን ጦርነት ለመቋጨት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረሰው የሠላም ሥምምነት የአፍሪካ የመሪነት ሚና ጥቅም የታየበት ነው ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ።

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አማምሻውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሠላም ሥምምነት የአፍሪካ የመሪነት ጥቅም የታየበት ነው ብለዋል።

ሥምምነቱ የነበረውን ግጭት እንዲቆምና ሰብዓዊ ድጋፉን በአፋር፣ በትግራይና በአማራ ይበልጥ እንዲሳለጥ አስችሏል ነው ያሉት።

ያም ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የተቋረጡ የሕዝብ አገልግሎቶች ዳግም እንዲመለሱና የመልሶ ማቋቋም ሥራ ለመሥራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የፌዴራል መንግሥቱና ሥምምነቱን የፈረሙት የሕወሃት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

በተጓዳኝም፤ የአፍሪካ ኅብረት፣ የኬንያና የደቡብ አፍሪካ መንግሥታት ላበረከቱን አስተዋጽዖም እውቅና ሰጥተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በሰላም አተገባበሩ ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም
አሁንም ደግሞ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጓን ጠቁመው፤ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አሜሪካ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እንዲጠናከር እያደረገች ያለው ድጋፍ በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጡት።
3.5K views15:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-08 17:24:29
3.0K views14:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ