Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ | Abrehot Library

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ከ12 ሚሊየን ብር በላይ ድጋፍ አደረገ

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለትግራይ ክልል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የአይነትና የገንዘብ ድጋፍ አድርጓል።

ድጋፉ 11 ሚሊየን ብር በጥሬ ገንዘብ ሲሆን ፥ ቀሪው 1 ሚሊየን ብር የሚያወጡ ኮምፒዩተሮች እና የህክምና መሳሪያ ቁሳቁሶች መሆናቸው ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ጽህፈት ቤት ልዩ አማካሪ ኢንጅነር ውብአየሁ ማሞ እንደተናገሩት ዛሬ በትግራይ ክልል ለሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መልሶ ማቋቋሚያ ከ12 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የዓይነትና የገንዘብ ድጋፍ ተደርጓል፡፡

ዩኒቨርሲቲው መሰል ድጋፎችን በቀጣይነት ለማድረግ ቁርጠኛ መሆኑን ገልፀው ፥ በምርምርና ቴክኖሎጂዎች ረገድ በመልሶ ማቋቋሚያ ስራዎች ላይ የራሱን እገዛ እንደሚያደርግ ገልፀዋል።