Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክቶችን አሸነፈ፡፡ የአውሮፓ ህብረት ከሚደግ | Abrehot Library

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ዘጠኝ የአውሮፓ ህብረት ፕሮጀክቶችን አሸነፈ፡፡
የአውሮፓ ህብረት ከሚደግፋቸው አስራ ሰባት (17) የምርምር እና የትምህርት ልህቀት ማዕከላት ፕሮጀክቶች አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በዘጠኙ አሸናፊ ሆነ።
ከዚህም በተጨማሪ ሁለት የፕሮጀክት ፕሮፖዛሎች ውጤት በመጪው ጥቂት ወራት የሚታወቅ ይሆናል።

በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን በ2022 November የARUA እና Guild የዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንቶች በነበራቸው ስብሰባ በአውሮፓ ህብረት የሚደገፉ የምርምር እና የ ትምህርት ልህቀት ማእከላት ለማቋቋም ወስነው መለያየታቸው ይታወሳል።
በዚሁ መሰረት በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በርካታ ፕሮፖዛሎች የቀረቡ ሲሆን ባለፉት ሁለት ተከታታይ ቀናት በቤልጂየም ብራስልስ በተካሄደው ግምገማ መሰረት 17 የልህቀት ማእከል ተመስርተዋል። ከነዚህ የልህቀት ማዕከል ፕሮጀክቶች ውስጥም በዘጠኙ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ አሸናፊ ሆኗል።
 
በተጨማሪም ዩኒቨርሲቲው ፕሮጀክቶቹን በማሸነፉ በሚሊዮኖች የሚቆጠር ዩሮ የሚያገኝ ይሆናል፡፡
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በፊርማ ስነስርዓቱ ላይ ይህ ውጤት ለአዲስ አበባ ዩኒርሲቲም ሆነ ለአገር ትልቅ ፋይዳ ይኖረዋል አለ ብለዋል፡፡  በተጨማሪም ለዚህ ውጤት አስተዋጽኦ ያደረጉ የዩኒቨርሲቲው ብርቱ ተመራማሪዎችን አመስግነዋል፡፡