Get Mystery Box with random crypto!

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በ 8 ወሳኝ ፕሮጀክቶች ከ አውሮፓ | Abrehot Library

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና በ 8 ወሳኝ ፕሮጀክቶች ከ አውሮፓ ህብረት ድጋፍ ለማግኘት በብራስልስ ቤልጂየም ከፍተኛ ጥረት እያደረጉ ይገኛሉ ፡፡የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚደንትን ጨምሮ 15 የአፍሪካ ዩኒቨርሲቲዎችና የአውሮፓ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚደንቶች ከአውሮፓ ህብረት ጋር በሚደረገው ወሳኝ በሆነው ስብሰባ ላይ እየተካፈሉ ይገኛሉ ፡፡ ከቀረቡት 16 የልህቀት ማዕከላት መካካል በ 8ቱ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የተሳተፈ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ ድጋፉን የሚያገኙት ፕሮጀክቶች በነገው እለት ይታወቃሉ፡፡ ይህም ዩኒቨርሲቲው ራስ ገዝ ሲሆን ከፍተኛ እገዛ እንደሚኖረው እና ዋነኛው የ ዝግጅት ኣካል ተደርጐ ሊወስድ ይችላል።

በሌላ በኩል የአፍሪካን ችግር የሚፈቱ ምርምሮችን ለማካሄድ የሚያስፈልግ ሰፊ መዋዕለ ንዋይ ድጋፍ ለማግኘት 16 የአፍሪካ የምርምር ዩኒቨርሲቲዎች ማህበርና የአውሮፓ ጊልድ ዩኒቨርሲቲ ማህበር እየተነጋገሩ ይገኛል፡፡
የአፍሪካ የአሊያንስ ህብረቶች ከፍተኛ ምርምሮችን መደገፍ እንዲሁም የምርምርና ከፍተኛ ትምህርት መሰረተ ልማትን መገንባት፣ አሁን ለሚስተዋሉ የአፍሪካን ችግሮች ለመፍታት አይነተኛ መፍትሄ መሆኑን በማመን የአውሮፓ ህብረት በሚቀጥሉት 5 ዓመታት200 አፍሪካውያንን በፒኤች ዲ (PhD) ለማሰልጠን በሚችልበትን ሁኔታ ወሳኝ ወይይት እየተካሄደ ይገኛል።