Get Mystery Box with random crypto!

Abrehot Library

የቴሌግራም ቻናል አርማ aauethiopianuniversty — Abrehot Library A
የቴሌግራም ቻናል አርማ aauethiopianuniversty — Abrehot Library
የሰርጥ አድራሻ: @aauethiopianuniversty
ምድቦች: ያልተመደበ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 12.44K
የሰርጥ መግለጫ

Abrehot Library is a public national library and the biggest library in Ethiopia also in East Africa.

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 2

2023-03-07 21:11:01
የቻይና መንግሥት በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ለሚማሩ ለ116 ተማሪዎች በቻይና ነጻ የትምህርት እድል በዛሬው ዕለት ሰጥቷል።

በዚህም መሰረት በመጀመሪያ ዲግሪ ለ80 ተማሪዎች፣ ለ18 ተማሪዎች የቻይንኛ ቋንቋ፣ ለ6 የሦሰተኛ ዲግሪ ተማሪዎች፣ ለ12 የአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ተማሪዎች እንዲሁም ለአንድ ተማሪ የጥናትና ምርምር ነጻ የትምህርት እድል ተሰጥቷል።

ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ከመጀመሪያ እስከ ሦሰተኛ ዲግሪ የሚማሩ ተማሪዎች ናቸው ።

የአዲሰ አበባ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና እንደገለጹት የትምህር እድል የተሰጣቸው ተማሪዎች በትምህርታቸው እገዛ የሚያስፈልጋቸው ናቸው።

ዩኒቨርስቲው በትምህርታቸው እገዛ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ድጋፍ እንዲያገኙ ከተለያዩ ተቋማት ጋር እየሰራ እንደሚገኝ ገልጸው የቻይና መንግሥት ለሰጠው የትምህርት እድል አመስግነዋል።

እድሉን ያገኙ ተማሪዎች ትምህርታቸውን ጠንክረው በመማር አገራቸውንና እራሳቸውን እንዲጠቅሙ ያስችላል ብለዋል።

በኢትዮጵያ የቻይና ኤምባሲ ምክትል አምባሳደር ሺን ቺንሚን ቻይና ለተማሪዎች የሰጠችው የትምህርት እድል የሁለቱን አገሮች ወዳጅነት የበለጠ እንደሚያጠናክር ገልጸዋል።

በቀጣይም የቻይና መንግሥት ለኢትዮጵያን ጥናትና ምርምር እንዲሁም ትምህርት እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደሚቀጥል አረጋግጠዋል።

የትምህርት ዕድሉን ያገኙ ተማሪዎች በበኩላቸው ባገኙት እድል መደሰታቸውን ገልጸው ተምረው እራሳቸውንና አገራቸውን ለመጥቀም ዝግጁ መሆናቸውን ተናግረዋል

የቻይና ኢትዮጵያ ወዳጅነት ነጻ የትምህርት እድል ከአምስት አመት በፊት የተጀመረ ሲሆን በትምህርታቸው ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸው ተማሪዎች ሲሰጥ መቆየቱ ተገልጿል።
2.4K views18:11
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-25 14:07:38
የአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ በመሪነትና አመራር ሰጭነት ስልጠና አካሔደ

ስልጠናውን የሰጠው በአዲስ አበባ ዪንቨርሲቲ ስር የሚገኘው የ ትምህርት ምርምር ተቋም እና የከፍተኛ ትምህርት አመራር መአከል ነው።

ስልጠናው ዩኒቨርሲቲው ወደፊት ለሚያገኘው የራስ ገጽ አስተዳደር ታስቦ እንደተሰጠ እና እንደሚያግዝ ተነገሯል።

ስልጠናው የሚቀጥል ሲሆን በአሁኑ ሰዓት የዩኒቨርሲሲቲው ከፍተኛ አመረራሮችን ጨምሮ በየደረጃው በሚገኙ የትምህርት ክፍሎች ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እንዲሁም የተቋማት ሃላፊዎች ተሳትፈውበታል።

ተሳታፊዎችም ስልጠናው በጣም ጠቃሚና አቅምን የሚገነባ በአዲስ የለውጥ መርህ ተቋሙን የሚቀይር እንደሆነም ገልፀዋል።
ስልጠናዉም ለ አንድ ወር ሲሰጥ ቆይቷል።

መጨረሻም በስልጠናው ለተሳተፉ አባለትም የሰርተፊኬት ሽልማት ተሰጥቷል።
1.5K views11:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-19 10:04:40  
የካቲት 12 ቀን 2015
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 ዓ.ም በማታ መርሃ ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት በዲፕሎማችሁ ወይም ደረጃ 4 ለምታመለክቱ አመልካቾችን ይጋብዛል
 
 
በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል
 
1. የዲፕሎማችሁን ወይም ደረጃ 4 ትምህርት ማስረጃ ከCOC ደረጃ 4 ጋር ማቅረብ
2. ዲፕሎማችሁ የአስተማሪነት ሆኖ ለምታመለክቱ ዲፕሎማ በጨረሳችሁበት የትምህርት አይነት ብቻ በመመዝገብ የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ
 
ማሳሰቢያ፡-
 
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 / ሶስት መቶ / በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን መላክ፤
4. ምዝገባዉን ካከናወኑ በኋላ የትምህርት  ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. ለመግቢያ ፈተና 600 ብር በኢትዮዺያ ንግድ ባንክ አካዉንት ቁጥር 1000087392067 ከፍላችሁ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ የመፈተኛ ቦታ ይዞ መገኘት ይጠበቅባችኋል
6. በዲፕሎማ አመልካቾች የዩኒቨርስቲዉን የመግቢያ ፈተና ጊዜን፤ በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (www.aau.edu.et) እና (https:\\portal.aau.edu.et) ወደፊት ይገለጻል፡፡
7. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 
 
    የምዝገባቀን፡   ከየካቲት 13 እስከ የካቲት 17 2015 ዓ.ም 
የምዝገባቦታ ፡    በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
 
  
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
1.3K views07:04
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-18 17:10:30 የካቲት 11 ቀን 2015
 
ማስታወቂያ
 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አዲስ ለተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ
 
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015  የትምህርት ዘመን በመደበኛ የዲግሪ ትምህርት መርሃ-ግብር በትምህርት ሚ/ር መስፈርት መሠረት አዲስ የተመደባችሁ ተማሪዎች በሙሉ፡
የካቲት 15 ቀን እና የካቲት 16 ቀን 2015 ዓ.ም በየተመደባችሁበት የዩኒቨርስቲው ካምፓሶች በመገኘት ሪፖርት እንድታደርጉ ያሳውቃል፡፡ በተጨማሪም ተማሪዎችም ለምዝገባ ስትመጡ
1ኛ - የአስራ ሁለተኛ ክፍል ማጠቃለያ ፈተና ውጤት ዋናውንና ፎቶ   ኮፒ፣
2ኛ - ስምንት ጉርድ ፎቶግራፍ፣
3ኛ - ብርድልብስና አንሶላ እንዲሁም የስፖርት ትጥቅ ይዛችሁ መምጣት እንዳለባችሁ ያስታውቃል፡፡
➢ በተጠቀሱት ቀናት ከአዲስ አበባ ውጪ ለሚመጡት ተማሪዎች በመርካቶ አውቶብስ ተራ፣ በላም በረት፣ በአቃቂ እና በአስኮ የመኪና መናኸሪያዎች በመገኘት ዩኒቨርስቲው የትራንስፖርት አገልግሎት ያቀርባል፡፡ ፡
➢ ከተገለጸው ቀን በፊት ለሚመጡ ተማሪዎች ምንም ዓይነት አገልግሎት ዩኒቨርስቲው አይሰጥም፡፡
➢ ለተጨማሪ መረጃ የዩኒቨርስቲውን ድረገጽ https://portal.aau.edu.et/ ወይም www.aau.edu.et ማየት የሚቻል ሲሆን
➢ ነዋሪነታችሁ አዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ሆኖ ወደ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች ሪፖርት የምታደርጉትና ስለ ዩኒቨርስቲው ገለጻ የምታገኙት የካቲት 17 ቀን 2015 ዓ.ም መሆኑን ያሳውቃል፡፡
➢ ከአዲስ አበባ ውጪ ለምትመጡ ተማሪዎች በዩኒቨርስቲው ውስጥ የመኝታ አገልግሎት ለማግኘት የተመደበላችሁን የመኝታ ክፍል 12ኛ ክፍል በተፈተናችሁበት ቁጥር በመጠቀም https://portal.aau.edu.et ማግኘት የምትችሉ መሆኑን ያሳውቃል፡፡
➢ በተለያየ ምክንያት ትምህርት አቋርጣችሁ ለመልሶ ቅበላ ውጤታችሁ የሚያበቃችሁ ተማሪዎች አዲስ ከተመደቡ 1ኛ ዓመት ተማሪዎች ጋር በመቅረብ በ2015 ዓ.ም. የመጀመሪያ ሴሚስተር ለመልሶ ቅበላ ከየካቲት 15 እስከ የካቲት 17 2015 ዓ.ም እንድታመለክቱ እናሳውቃለን፡፡
 
አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ                                                             ሬጅስትራር
3.8K views14:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-16 10:30:35 አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ለ2015ዓ.ም. በማታ መርሃግብር ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል

በዚህም መሰረት አመልካቾች የሚከተሉትን ማሟላት ይጠበቅባቸዋል

1. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ$ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር ማቅረብ
2. በ12ኛ ክፍል ውጤት የምታመለክቱ አመልካቾች ከ2010-2015ዓ.ም. ድረስ ብቻ ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የምታሟሉ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
3. ከተለያዩ ዩኒቨርስቲዎች ከ2010-2014ዓ.ም. በተለያየ ምክንያት አቋርጣችሁ ለምታመለክቱ የወጪ መጋራት ያጠናቀቃችሁበትን የሚገልፅ ደብዳቤ ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ
4. ለዲፕሎማ ወይም ደረጃ 4 አመልካቾች በ2015ዓ.ም. ቅበላ አይኖረንም
ማሳሰቢያ፡-

1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\
portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300 (ሶስት መቶ ብር) በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF) ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራት ያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
4. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
6. በዲግሪያችሁ ለምታመለክቱ የመረጣችሁትን ትምህርት ክፍል የምታገኙት 12ኛ ክፍል ጨርሰው ያመለከቱ ከተመደቡ በኋላ በሚተርፉ ቦታዎች ላይ ብቻ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

የምዝገባ ቀን፡ ከየካቲት 10 እስከ ከየካቲት 16 2015ዓ.ም
የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203

አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር

 
725 views07:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-15 15:16:46 በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሂዩማኒቲስ፣ ቋንቋዎች ጥናት፣ ጋዜጠኛነትና ኮሙኒኬሽን ኮሌጅ፣ ማህበራዊ ሳይንስ ኮሌጅ እና ሥነጥበባት ኮሌጅ ለ2015 የትምህርት ዘመን በመደበኛ መርሃ-ግብር
ከዚህ በታች በተዘረዘሩት የትምህርት መስኮች                                ለመጀመሪያ ዲግሪ ትምህርት አመልካቾችን ይጋብዛል
• Multimedia
• Public Relations and Strategic Communication
• English Language and Literature
• Modern European Languages: Portuguese and Italian, Spanish and German
• Arabic Language and Communication
• French Language and Professional Skills
• Linguistics
• Ethiopian Sign Language and Deaf Culture
• Ethiopian Sign Language and Interpreting
• Folklore (Culture Studies)
• Oromoo Language and Communication)
• Tigrigna Language and Literature
• Archaeology and Heritage Management
• History
• Philosophy
• Social Anthropology
• Sociology
• Music
• Theater
• Fine Arts
 
የቅበላ መስፈርቶች፦
• አመልካቾች በ12ኛ ክፍል ውጤት በ2014ዓ.ም. ትምህርት ሚኒስቴር ባወጣው መስፈርት መሰረት ለከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ነጥብን የሚያሟሉ እና ከትምህርት ማስረጃ ጋር በማያያዝ ማቅረብ የሚችሉ
• ከላይ በተጠቀሱት መስኮች ተምረው ሃገራቸው ለማገልገል ፍላጎትና ዝንባሌ ያላቸው፣
• ማንኛውም የቅድመ-ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪ እንዲያቀርብ የሚጠየቀውን የትምህርት ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
• እንደ አስፈላጊነቱ የትምህርት ክፍሎች የሚያዘጋጁትን ፈተና ለመቀበል ዝግጁ የሆኑ፣
• በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች የሚሰጡ ፍሬሽ ማን ኮርሶችን በሚመደቡበት የትምህርት ክፍል ውስጥ ሆነው ለመማር ፈቃደኛ የሆኑ፣
 
ማሳሰቢያ፡-
1. የማመልከቻ ፎርሙን በዩኒቨርስቲዉ ድረገጽ (https:\\portal.aau.edu.et) መሙላት
2. ከማመልከቻ ፎርም የሚያገኙትን የማመልከቻ ቁጥር (Application Number) በመያዝ ብር 300/ሶስት መቶ ሃምሳ/ በኢትዮጲያ ንግድ ባንክ በሞባይል CBE ብር ወይም በወኪሎች ወይም በቅርንጫፍ አማካኝነት በ242424 አጭር ኮድ ክፍያ መፈጸም
3. ክፍያዎትን ካጠናቀቁ በኋላ ወደ ማመለከቻ ፎርሙ በመመለስ በፒዲኤፍ (PDF)ፎርማት የተለወጠ የትምህርት ማስረጃዎትን የወጪ መጋራትያጠናቀቁበትን ሰነድ መላክ፤
4. ምዝገባዉ ካከናወኑ በኋላ የትምህርት ማስረጃ በአካል ይዞ በመቅረብ ቢሮ ቁጥር 203 ማስገባት ይኖርብዎታል፡፡
5. የተማሪዎች ቁጥር ከመቀበል አቅም በታች (ዝቅተኛ) ከሆነ የትምህርት ፕሮግራሞች የማይከፈቱ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡ 
 
 
           የምዝገባ ቀን፡ ከየካቲት 10 እስከ የካቲት16 2015ዓ.ም       የምዝገባ ቦታ ፡ በሬጅስትራር ህንፃ ቢሮ ቁጥር 203
 
                          አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ሬጅስትራር
1.8K views12:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 06:55:00 https://t.me/aauethiopianuniversty/379
4.1K views03:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-02-04 06:54:48 Addis Ababa University is pleased to announce its bachelor's Degree programs for the eligible applicants as per the NEAEA 12th grade result cutoff points. All applicants will get the necessary dormitory and cafeteria services among others. AAU is proud of the high employability rates of its graduates at all levels and has opened it's doors to its applicants to the path of high competency. Use the link to view the programs.
3.7K views03:54
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-27 14:47:49
መልካም ዜና !

*ከ404 ሆስፒታሎች 7ኛ ደረጃ!

በአዲስአበባ ዮኒቨርስቲ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ህክምና ትምህርት ቤት የሚገኘው የአጥንት ህክምና ትምህርት ክፍል በ2022 አመተ ምህረት (እ.አ.አ) በመላው ዓለም በ60 ሀገራት ከሚገኙ SIGN IMN የሚባለው የረጃጅም አጥንቶች ከፍተኛ ኦፕራሲዮን ከሚሰራባቸው 404 ሆስፒታሎች ከፍተኛ ቁጥር ያለው ኦፕራሲዮን ከተሰራባቸው የመጀመርያ አስር ማዕከላት መካከል(Top Ten) 7ኛው መሆኑን አሜሪካን ሀገር የሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስሪያ ቤት ዛሬ አስታውቋል።

በጥቁር አንበሳ ሆስፒታል የአጥንት ሕክምና ክፍል የሚገኘው ይህ ፕሮግራም በፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ የሚመራ ሲሆን በመላው ኢትዮጲያ ከሚገኙት 40 ፕሮግራሞች የመጀመሪያውና በርካታ ከባባድ የአጥንት ኦፕራሲዮኖች በማድረግም በአንደኝነት የተቀመጠ መሆኑን SIGN FRACTURE CARE INTERNATIONAL አስታዉቋል።

ፕሮፌሰር ብሩክ ላምቢሶ የሚመራው ዲፓርትመንትም ለዚህ ደረጃው ከጤና ሚንስቴር እውቅና ተሰጥቶታል።

የSIGN IMN Fixation System በመኪና አደጋና በጦርነት ለሚከሰቱ የትልልቅ አጥንት ስብራቶች በኦፕራሲዮን ማከሚያ ዋና ፍቱን መሳርያ ሲሆን ዋጋውም ውድ ነው።
5.0K views11:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-01-24 20:08:09
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲን ጨምሮ የ አራት ሀገራት ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የ IPORA (interdisciplinary policy oriented research on Africa ) የሚባል ፕሮጀክት በጋራ ለመስራት በ ኮዲቯር አቢጃን የመግባቢያ ሰነድ ተፈራረሙ።

በዛሬው እለትም ይህንንውፕሮጀችት አስመልክቶ በ ኮትዲቫር ዋና ከተማ አቢጃን የ አራትዮሽ ሰምምነት ውይይት እየተካሃደ ሲሆን በዉይይቱ ላይ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሐናን ጨምሮ የፈረንሳይ ሃገር  ቦርዶ  ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት፣ የ Cote D'Ivoire ሀገር ፌሊክስ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት እና የ ሞሮኮ ራቫት ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ንግግር እና ማብራሪያ ሰተዋል።

የ IPORA ፕሮጀክት በፈረንሳይ ዩኒቨርሲቲ ቦርዶ የሚደገፍ እና ፖሊሲን ያማከለ አለማቀፍ እና ጥናታዊ የምርምር መድረኮችን የሚያዘጋጅ ፕሮግራም ነው።

ለ ፕሮጀችቱም ከ 8 ሚሊዮን ዩሮ በላይ ፈሰስ እንደሚደረግ ተገልጿል።

የአዲስ አበባ ዪንቨርስቲ የፈረንሳይኛ ቋንቋ ተናጋሪ አገራት ዪንቨርሲቲዎች ኔትዎርክ ጋር ሲሰራ ይህ የመጀመሪያው ጊዜ ነው።
6.4K views17:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ