Get Mystery Box with random crypto!

የሠላም ሥምምነቱ የአፍሪካ የመሪነት ሚና ጥቅም የታየበት መሆኑን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር | Abrehot Library

የሠላም ሥምምነቱ የአፍሪካ የመሪነት ሚና ጥቅም የታየበት መሆኑን የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ

በኢትዮጵያ በሰሜኑ ክፍል የተከሰተውን ጦርነት ለመቋጨት በደቡብ አፍሪካ ፕሪቶሪያ የተደረሰው የሠላም ሥምምነት የአፍሪካ የመሪነት ሚና ጥቅም የታየበት ነው ሲሉ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ገለጹ።

ለይፋዊ የሥራ ጉብኝት አማምሻውን በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተገኝተው ለጋዜጠኞች ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በመግለጫቸውም በፌዴራል መንግሥትና በሕወሓት መካከል የተደረሰውን የሠላም ሥምምነት የአፍሪካ የመሪነት ጥቅም የታየበት ነው ብለዋል።

ሥምምነቱ የነበረውን ግጭት እንዲቆምና ሰብዓዊ ድጋፉን በአፋር፣ በትግራይና በአማራ ይበልጥ እንዲሳለጥ አስችሏል ነው ያሉት።

ያም ብቻ ሳይሆን በጦርነቱ የተቋረጡ የሕዝብ አገልግሎቶች ዳግም እንዲመለሱና የመልሶ ማቋቋም ሥራ ለመሥራት እንደሚያስችል ተናግረዋል።

ለዚህም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ የፌዴራል መንግሥቱና ሥምምነቱን የፈረሙት የሕወሃት መሪዎች ሊመሰገኑ ይገባል ብለዋል።

በተጓዳኝም፤ የአፍሪካ ኅብረት፣ የኬንያና የደቡብ አፍሪካ መንግሥታት ላበረከቱን አስተዋጽዖም እውቅና ሰጥተዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በሰላም አተገባበሩ ዙሪያ ፍሬያማ ውይይት ማድረጋቸውንም
አሁንም ደግሞ ለሰብዓዊ ድጋፍ የሚውል 331 ሚሊየን ዶላር ተጨማሪ ድጋፍ ማድረጓን ጠቁመው፤ በቀጣይም ድጋፉ ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል።

አሜሪካ በተለይም ደግሞ የኢትዮጵያ ምጣኔ ሃብት እንዲጠናከር እያደረገች ያለው ድጋፍ በተለያዩ መስኮች ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ነው ያረጋገጡት።