Get Mystery Box with random crypto!

ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekele3
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.50K
የሰርጥ መግለጫ

እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ዩቲቡ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 6

2023-05-08 20:50:18
አማርኛ…!

"…በፈረንሳይ ግዙፍ የጦር አካዳሚ ውስጥ የሚሠሩ ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች አማርኛን በዚህ መልኩ እየተማሯት ነው። ህወሓትና ኦህዴድኦነግ ደግሞ ለፈረንሳይ መንግሥት የተቃውሞ ደብዳቤ ጻፉ አሏችሁ።

• ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ
• ለ ሉ ሊ ላ ሌ ል ሎ

"…አማርኛ መንፈስ ነው። ድምፂ ወያኔ፣ ቲኤምኤች፣ ዛራ፣ ኦኤምኤን፣ ኦቢኤን፣ ኩሻንኩሽ ሚዲያ፣ ፀጋዬ እሬሳ፣ ህዝቅኤል ጋቢሳ፣ ስታሊንና አሉላም እንጀራ የሚበሉት በአማርኛ ቀባጥረው ነው።

"…ትግሬም ኦሮሞም ባይማሩት የሚጎዱት ራሳቸው ናቸው። ግራ የሚገባቸው ራሳቸው ናቸው። ጀዋር መሃመድ አማርኛ ማወቁ ጠቀመው እንጂ አልጎዳውም። በቀለ ገርባ መጽሐፍ ተርጉሞ የጻፈው በአማርኛ ነው። ነጋሶ ጊዳዳ፣ መራራ ጉዲናም መጽሐፍ የጻፉት በአማርኛ ነው። አቢይ አህመድ ያውም የጎንደር ዐማራ ሴት አግብቶ ነው ፏ ብሎ የሚኖረው። አማርኛም ነፍስ እኮ ነው።

"…ብራቮ አማርኛ…! አንደዜ ለአማርኛ ሞራል።
6.0K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 20:50:18
የኦሮግሬ ነገር…!

"…ደግነቱ በአማርኛ ነው የሚፈራረሙት። አዛኜን ያ መለስ ዜናዊ ግን ሲበዛ ክፉ ነው። እሱ የወልቃይት ዐማራ አግብቶ በአማርኛ እየተግባባ ለኦሮሞ ግን እርስ በእርሱም ከሌካውም እንዳይግባ ከጀርመን ኑረምበርግ የላቲን ፊደል አምጥቶ ኦሮሞን ዱዳ በምልክት ቋንቋ ከጉራጌ ከሲዳማው እንዲነታረክ ካደረገው በኋላ አሁን ደግሞ ምን አምጥቶ አዘጋጅቶለት ይሆን ቀን በቀን የሚያፈራርማቸው። አይ ወያነ መችም መቸም ነፍሱ አይማርም። አቡነ አረጋዊን እውነቴን እኮ ነው።

"…አይ አማርኛ እ…ም…ጷ ኑሪልኝ አቦ። አንቺ እኮ ለአያያዝ ቀላል፣ ለተጠቃሚ ብርሃን፣ ሊያጠፉሽ ኪሊማንጃሮ ቢደፉብሽ፣ አርታኢሌን ቢያነዱብሽ፣ የአማሪካ ሱናሚ ቢያጥለቀልቅሽ አንቺ እንደሁ አትጠፊ። የትግሬም፣ የዐማራም፣ የኦሮሞም ለማኝ እንኳ ቢርበው ለምኖ የሚበላብሽ፣ ቦለጢቀኞቹ፣ ካድሬዎቹ ሰብከው የሚኖሩብሽ። ለፓስተሮች እንጀራቸው፣ ለኡስታዞች መቀፈያቸው የሆንሽ አንቺ ሞገሳም አማርኛ ሆይ ዘላለም ኑሪልኝ።

"…ቅድስት አማርኛ ሆይ የተለጣለጡትን ትግሬና ኦሮሞንም እንዲህ አቀራርበሽ አፈራርሚያቸው። መቼም ዘንደሮ የዐማራው መንቃት ገና የማያሳየን ጉድ የለም።

• ወጥር ዐማራ…! እኔ በሳቅ…
5.5K views17:50
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 14:51:56 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…የዐማራ ክልልን በተመለከተ ተደጋግሞ የሚነሣ ነገር አለ። ያም ምንድነው ያልን እንደሆነ "የዐማራ ክልል መሪዎች ለምንድነው በሚመሩት ሕዝብ ላይ ጨካኝ፣ አረመኔ የሆኑት? ለምንድነው እንደ ኦሮሞ፣ እንደ ትግሬና ደቡብ ወንድሞቻቸው ቢያንስ ከሌላ ነገድ ተወልደውም እንኳ ቢሆን መሪ ሆነው ለተሾሙበት ለዐማራ ነገድ ጥብቅና የማይቆሙት? ለሰላሙ፣ ዲሞክራሲና ለልማቱ የማይተጉት? ለምንድነው ሌሎቹ ለሚመሩት ሕዝብ ሽንጣቸውን ገትረው እንደሚሟሟቱት፣ እንደሚሟገቱት የዐማራዎቹም የማይሟገቱት ብለው ሲጠይቁ ይደመጣል። ለዚህ ጉዳይ መልስ ለመስጠት የበኩሌን ሚጢጢ ሃሳብ ለመሸጥ ነው በርዕሰ አንቀጽ የመጣሁት።

"…እውነት ነው ለምሳሌ አቢይ አህመድ የወሎ ዐማራ ነው ኦሮሞነትን በኦሮሞ ምድር ላይ በመወለዱ እና ኦሮሚኛ ቋንቋ በመናገሩ ብቻ ኦሮሞነትን የተቀበለ የዐማራ ሰው ነው። መለስ ዜናዊ ኤርትግ፣ ስብሐት ነጋ ኤርትግ፣ ቴዎድሮስ አድሓኖም፣ ኬሪያ ኢብራሂም ወዘተ ኤርትግ ናቸው። ገብሩ አሥራት፣ ጌታቸው ረዳ ወዘተ ዐማትግ ናቸው። ነገር ግን እነዚህ ግለሰቦች በተሾሙበት ክልል ለተሾሙበት ሕዝብ እጅግ ሲበዛ ታማኝ ደማቸውን የሚሰጡ፣ የሰጡም እስከሞትም የታመኑ ናቸው።

"…ወደ ዐማራ ክልል ስንመጣ ግን የተለየ ጠባይ፣ የተለየ ማንነት፣ የተለየ ስብዕና ነው የምናገኘው። ክልሉ በራሱ እንዲቆም አይፈለግም። ክልሉ ውስጥ የሚኖረው የዐማራ ነገድ በክልሉ የሥልጣን እርከን ስፍራም የለው። የክልሉ የዐማራ አመራሮች ቀደም ሲል በሕወሓት በጥንቃቄ ተመርጠው የተፈጠሩ፣ የተሠሩ ናቸው። ብልፅግናም ያንኑ የህወሓትን ፖሊሲ ነው ያስቀጠለው። ሕዝባቸውን የሚፀየፉ፣ በመረረ ጣላቻም የተሞሉ፣ ሊበቀሉት የሚፈልጉትን ሕዝብ የሚመሩ ናቸው በወረንጦ ተለቅመው እንዲመሩት የሚደረጉት። ምሳሌም እናንሳ ብዙዎች እንደሚሉት፦

"…አገኘሁ ተሻገር (የቅማንት ዐማራ ማንነት ያለው) ሰካራም በትግሬ የተመረጠ፣ በመለስዜናዊ በበረከት ስምኦን የተመለመለ ነው ይሉታል። ተመስገን ጥሩነህ፣ ሰማ ጥሩነህ፣ ኢንጂነር ሀብታሙ፣ ይልቃል ከፍአለ የጎጃም አገው ሸንጎ አባላት ሲሆኑ ጄነራል አበባው ታደሰ ደግሞ በአባቱ የሀውዜን ትግሬና በእናቱ የዋግኽምራ አገው ሸንጎ አባል ነው ይሉታል። ደመቀ መኮንን ምንጩ የባሌ ኦሮሞ ሲሆን ወሎ ተወልዶ በ77 ድርቅ ቤተሰቡ ቻግኒ ጎጃም ያደገ ነው ይባላል። መለስ ዜናዊና በረከት ስምኦን እጅግ የደከሙበት የእንግሊዝ የስለላ ድርጅት ከቦታው ንቅንቅ እንዲል የማይፈልገው ሰው ነው ይሉታል። እስላም ሆኖ ያውም ፅንፈኛ ዐማራ ጠል እስላም። እነዚህ ሰዎች ሙሉ ዐማራ ያለመሆናቸው ችግር የለውም ምክንያቱም ሌሎቹም እንዲሁ ናቸውና። በኢትዮጵያ ሙሉ በሙሉ ንፁሕ ሌላ ዘር ያልተቀላቀለብኝ ነኝ የሚል የለም። ሆኖም ግን ሌሎቹ ለተሾሙበት ክልል ሕዝብ ሟች ሲሆኑ እነዚህ ለምን ገዳይ ሆኑ? ነው ጥያቄው።

"…እነዚህ የዐማራ ሕዝብ ገዢዎች የራሳቸውን የሆነ ወሳኝ ኔትወርክ ፈጥረውም ነው ዐማራውን ቀፍድደው የያዙት። ከባዱ ነገር ይሄን ኔትወርክ ማፈራረሱ ላይ ነው። የዞን፣ የወረዳ፣ በቀበሌ ስምሪት፣ በፖሊስ ተቋማት፣ በተለይ ደግሞ በዞንና በወረዳ ወሳኙ ስፍራ ከዚያም ወረድ ሲል በቀበሌ በሚገኙ ማዘዣ ጣቢያዎች፣ ከፍ ሲል በልዩ ኃይል እና በአድማ ብተና፣ በዞን፣ በወረዳና በቀበሌ ካቢኔ ውስጥ በቀጥታ የመሳተፍ እና የማዘዙን ሥልጣን የተቆጣጠሩት እነዚህ ኃይሎች ናቸው። አሁን ከቀበሌ እስከ ክልል ወሳኙን የዐማራ የሥልጣን እርከን በብዛት እንዲቆጣጠሩ የተደረጉት እነዚህ በዐማራ ጥላቻ ያበዱ፣ ዐማራ ማንነት እንዲጠፋ፣ ክልሉም ፍርስርሱ እንዲወጣ በሚተጉ በደም ማንነታቸው የቅማንት፣ የአገው ሸንጎ፣ የከሚሴ ኦሮሞ እና የአርጎባ ተወላጅ የሆኑ ግለሰቦች ናቸው። እነዚህ አካላት በአሁኑ ጊዜ በክልሉ የፀጥታና የፖሊስ ተቋማት ውስጥ ወሳኞቹ አካላት ናቸው።

"…እንደ ድንገት በእነዚህ ተቋማት ውስጥ የገቡ ዐማሮች ከተገኙ በፍጥነት ነው እርምጃ የሚወሰድባቸው። ሳይታወቁ፣ የደም ማንነታቸው ሳይጣራ ተሽሎክሉከው አልፈው ሥልጣን የሚይዙ ካሉም በዲሞክራትነታቸው፣ በእኩልነት፣ በፍትሕ አቀንቃኝነታቸው ወዲያው ይታወቃሉ። ዐማራ ክልል ላይ ሆኖ ስለክልሉ መበደል፣ መጨቆን፣ ስለ ሕዝቡ መፈናቀል፣ መሰደድ፣ መገረፍ፣ መታረድ መናገር የጀምር ሰው ያኔ ዐማራ መሆኑ ይታወቃል። ዶር አምባቸው፣ ምግባሩ ከበደ፣ አቶ እዘዝ ዋሴ፣ ጄነራል አሳምነው ጽጌ ሰለባ የሆኑት በእነዚሁ የዐማራ ማንነት በሌላቸው ቀድሞ በህወሓትና ኋላ በአዲሱ ባርያ አሳዳሪያቸው በኦህዴድ ኦነግ አማካኝነት በተሾሙ ፀረ ዐማራ ኃይሎች ነው።

"…ለዚህ ነው አገኘሁ ተሻገር እንደፈለገ ሰክሮ፣ ሰርቆ፣ ቀባጥሮ የማይነካው። ገና ክልሉ ያለቅጥ ሰፍቷል ተብሎ 8 ቦታ ሊሸነሽኑት መሆኑን ስትሰሙ ደግሞ ጉድ ትላላችሁ። ሲጠቃለል ዐማራ ትግሉን ከባድ የሚያደርግበት ይሄ ነው። ዐማራን የሚያሸንፈውም፣ የሚፈታተነውም ለዘመናት በተሠራበት መዋቅራዊ አስተዳደራዊ ሴራ ምክንያት ነው። ዐማራ ትግሉን ፈታኝ የሚያደርግበት ይሄን የሴራ መስመር በጸሎትም፣ በዱአም፣ በጉልበትም ቢሆን በጥበብ በጣጥሶ የራሱን የጸጥታ መዋቅር መዘርጋት ሲችል ብቻ ነው። ሌላው ቢቀር ፓርላማ ተመርጠው የሚገቡት እንኳ ለምሳሌ እንደ ዶር ሂሩት ካሰው አይነቷ በግልፅ "ዐማራ ጨቋኝ ነበረ" ብላ ዐማራውን ምረጠኝ ብላ የምረጡኝ ቅስቀሳም አድርጋ ጨቋኙ ዐማራም በደቡብ ጎንደር መርጧት የአበባ ምንጣፍ ተነጥፎላት ጨቋኙን ዐማራ ወክላ ፓርላማ የገባች ሴት ናት። ፓርላማ ገብተው ስለ ዐማራ መጨቆን የሚተነፍስ ሰው ካገኛችሁ እሱ በደም ማንነቱ ዐማራ ነው። ዝም፣ ጭጭ፣ የሚሉት በሙሉ ግን በጥንቃቄ ተመርጠው የዐማራን መጥፋት፣ የክልሉን መፍረስ፣ መድቀቅ፣ መበተን የሚፈልጉ አማርኛ ተናጋሪ ኃይላት ናቸው የሚሉ መተርጉማን አሉ።

"…እንግዲህ ይሄን ዐማሮች ሲያዩት ከባድ ነገር ግን ደግሞ ወስኖ ካመረረ፣ ጥርሱንም ነክሶ ቆርጦ ከታገለ ኢምንት የሆነ ሴራ ለመበጣጠስ ቀናትም አይፈጅበትም። በአንድ ጎን እያመረተ፣ ሌላውንም እየመከተ በሌላ ጎን ደግሞ ውስጡን እያጠራ መታገል ከጀመረ ድል አፍንጫው ስር ነው የምትንከላወሰው። ቢያንስ እነዚህ ፀረ ዐማራ የዐማራ ሹመኞች እንደ ትግሬና ኦሮሞ ሹመኞች ከነገዱ ባይወለዱ እንኳ እንደእነሱ ለሚመሩት ሕዝብ እንዲጨነቁ ማድረግ ተገቢ ነው። ሙፈሪያት ካሚል እንኳ ግማሽ የጅማ ኦሮሞ ሆና ለስልጤ ደሟን የምትሰጥ መሆኗን እነ ሂሩት ካሰው ቢረዱ መልካም ነው እላለሁ። እኔ የምጽፈው ጦማር ይመራል ነገር ግን ምንም ማድረግ አልችልም። ፈርዶብኝ ነው። እኔ አይስክሬም ብቻ አይደለም የምሸጠው። ኮሶ፣ እንቆቆ፣ ግራዋም፣ እሬትም እሸጣለው። ለወያኔና ለኦነግ ሰዎች ደግሞ በረኪናና የአይጥ መርዝ በስፋት አቀርባለሁ። 1 ሜትር ገመድም በተመጣጣኝ ዋጋ አቀርብላቸዋለሁ። ታነቅ…

"…ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ… አሸበርቲው።
5.8K views11:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-08 10:18:23
የሄኖክ ዘሐበሻ ይቅርታ…!

"…ብዙ ሰው ዳንኤል ክብረትና የዘሐበሻው ሔኖክ አለማየሁ ላይ አትጨክንም። እጅህ ቄጤማ ዓይንህ ጨለማ ይሆናል ይለኝ ነበር። እኔም ሁሉም የሚሆነው ጊዜው ሲደርስ ነው። ይዋል ይደር ጊዜም እንስጣቸው ባይ በመሆኔ በሁለቱ ላይ የሚነሣ የብዕር ሰይፍ ሳይኖረኝ ቆይቷል።

"…ዳንኤል በኦሮሞ የጨረቃ ጳጳሳት ምክንያት እህል ውኃው ተቋርጧል። እስከአሁንም እንዳይተነፍስ ተደርጎ በ12 ቁጥር ሚስማር ተጠርቅሟል። ይሄን ጦማር አይቶ ወብርቶ ብቅ ካለም እኔም የሰሰትኩትን ጨምሬ ብቅ እላለሁ።

"…ሄኖክም ወዳጄ ነው። ከትንሽነት ወራቱ ጀምሮ ነው የማውቀው። እናቱም ወዳጄ ናቸው። ራሱን ለመለወጥ እንደ ሄኖክ የለፋ ሰው በህይወቴ ገጥሞኝ አያውቅም። በመዲና መጽሔት ዝግጅት ወቅት አግዤዋለሁ። ምስክር ከካታኮምብ በሚለው የብዕር ስሜም ጥቂት ጦማሮችን ጽፌለታለሁ። ይሄ ጸሐፊ ማነው? አጋልጥ ተብሎ ማዕከላዊ ከአንዴም ሁለት ሦስቴ በእኔ ምክንያት ተንገላቷል። አሳልፎ ግን አልሰጠኝም። ሄኖክ ወዳጄም ወንድሜም ነው። እዚህ ቦታ መግለጽ የሌለብኝን ሁሉ ማውራት አይጠበቅብኝም። ባለፈው ጊዜ ለሻሸመኔው የዘር ፍጅት 1ሺ ዶላር እሰጣለሁ ሲል በፍጹም ጨምር ብዬው በሕዝብ ፊት ያስጨመርኩት ስለምቀርበው ነው።

"…ሔኖክ ምርጫ 97 ትን ተከትሎ በጋዜጠኞች ላይ በተከፈተው ወከባ መጀመሪያ ወደሰሜን አፍሪካ፣ ከዚያ ቱርክ፣ ከዚያ ወደ አማሪካ የተሰደደ በተሰደደበትም ሃገር በራሱ ጥረት ሚዲያ ከፍቶ የታገለ ደፋር ልጅ ነው። ሄኖክ ለማደግ ካለው ጉጉት የተነሣ ኋላ ላይ የቢዝነስ ጓደኛ ሆነው የቀረቡት እንደ ክፍሉ ታደሰ ያሉት ከዐማራ ባለሃብቶች ጋር ተጣግተው ሊያሳስቱት እንደሚችሉ እጠረጥራለሁ። ለማንኛውም ሄኖክ እኔ የድምጽ ቅጂው እንደወጣ ፌክ ነው ባልኩት መሠረት ዛሬ ደርሶበት ይቅርታ ጠይቋል።

•ዐማራ ግን ያሸንፋል!
5.8K views07:18
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-29 10:45:48
"…እንግዲህ ክርስቶስ በአብ ክብር ከሙታን እንደ ተነሣ እንዲሁ እኛም በአዲስ ሕይወት እንድንመላለስ፥ ከሞቱ ጋር አንድ እንሆን ዘንድ በጥምቀት ከእርሱ ጋር ተቀበርን። ሞቱንም በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ከተባበርን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ደግሞ ከእርሱ ጋር እንተባበራለን" ሮሜ 6፥ 4-5

• ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
~በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
• አሰሮ ለሰይጣን
~ አግአዞ ለአዳም
• ሰላም
~ እምይእዜሰ
• ኮነ
~ ፍሥሐ ወሰላም።
487 views07:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 10:29:42
"ርዕሰ አንቀጽ"
•የጥያቄ ቀን

"…የግርማ የሺጥላ ገዳይ ማነው? ለግርማ የሺጥላ ከቤተሰቦቹ ይልቅ የፅንፈኛው ሰውበላ በላኤሰቡ የኦነግ ሚዲያዎችና አክቲቪስቶቻቸው ከፍየሏ በላይ እየጮሁ ነጠላ ዘቅዝቀን ደረት እየደቃን እናልቅስ፣ ለቅሶም ድረሱንም ለምን አሉ? …ኦነግ ከመቼ ወዲህ ነው ለዐማራ ሟች አዛኝ፣ ተቆርቋሪ፣ አልቃሽ፣ ተንሰፍሳፊ፣ እንስፍስፍ የሆነው? ምድረ ገተት ጠንቋሊ አለ እስታሊን።

"…እነ ዶር አምባቸው ሲገደሉ በዋዜማው ገዱ አንዳርጋቸውን ጀርመን ፍራንክፈርት፣ ደመቀ መኮንንን አሜሪካ መላቸው ይታወሳል። አሁንም ግርማ የሺጥላን ሲገድለው ይልቃል ከፍአለን መቀሌ፣ ደመቀ መኮንንን ታንዛኒያ የላከው ለምን ይሆን? በመቀሌው የክልል ርዕሳነ መስተዳድር ጉዞ ላይ ከዐማራ ክልል ይልቃል ብቻውን እንዴት ሰደዱት? ከኦሮሚያ የካቢኔ አባላት ሽመልስን አጅበው ሲሄዱ ከዐማራ ምነው ግርማ የሺጥላ ቀረ? ልጆቹን ይዞ፣ ሚስቱን ይዞ ለስብሰባ ነው የሄደው ከተባለ በኋላ መንዜ የምን ስብሰባ ነው ሲል፣ አይ ቤተሰብ ጥየቃ ነው ለምን ተባለ?

"…አቢይ ግርማ የሺጥን ራሱ በሚያዘው የሪፐብሊካን ጋርድ ለምን አስጠበቀው? ከሁሉ ፈጥኖ ሂሊኮፕተር እንዴት ላከለት? የሚያጣጥረውን ግርማ የሺጥላ ሂሊኮፍተሩ ውስጥ ማን ጨረሰው? ሂሊኮፍተሩ ገና ሰማይ ላይ እያለ አቢይ አሕመድ ግርማ ሞቷል ብሎ የኅዘን መግለጫ እንዴት ተጣድፎ አወጣ? ናትናኤል መኮንን የተባለ ሉጢ ፖሊስ ራሱ ሳይሰማ የገዳዮቹን ስም በየትኛው ምርመራ አረጋግጦ ነው ያወጀው? አቢይ በቀጣይ የሚበላቸው ተረኞች እነማን ናቸው ብላችሁ ትገመትላችሁ…?,

"…እሳደባለሁ የምትል የኦሮሞ ጽንፈኛ የወሃቢይ እስላም፣ የወለጋ ኦሮሞና የደቡብ ተጎታች ፅንፈኛ ቤንጤ፣ የዐማራ ሆድአደር ፅንፈኛ ብአዴን፣ የህወሓት አምላኪ ቆርቆሮ ፓጋን… እንዳል ቀስፋችሁ ጮጋ በሉ።

• ድርጅቱ ነኝ…!
3.6K views07:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 04:12:26
ያልታወቁ ሀይሎች…!

"…በኦሮሚያ ሲሆን ያውም በወለጋ ገዳዮች "ስማቸው ያልታወቁ ሀይሎች" የሚል ነው። በቀን በጠራራ ፀሐይ እየደፉ፣ ሺዎችን እየጨፈጨፉ ስማቸው ያልታወቁ ኃይሎች ነው።

"…ዐማራ ክልል ሲሆን ገዳዮቹ ከመግደላቸው በፊት ሁላ ስም ወጥቶላቸው ሊነገረን ይችላል። ነውጠኛ ጽንፈኞች አላለም አቢይ አህመድ።

"…ፖሊስ ምርመራ ማድረግ እንኳ አይችልም። ገዳዩ አቢይ ቸኮለ። ቸኮለና ተበጠረቀ። ዳይሬክተሩና ደራሲው ፊልሙን አስበላው።

"…አሁን ያልታወቁት ሀይሎች ታንዛኒያ ከአቢይ ጋር በመደራደር ላይ ናቸው። ነውጠኞቹ ጽንፈኞች ደግሞ ድሮን እየተዘጋጀላቸው፣ ታንክ እያሟቀላቸው፣ የኦነግ ሠራዊት በመከላከያ ካባ ሊርመሰመስባቸው ነው።

"…ሞክራት… ! ለወሬ ነጋሪ አይተርፈውም ዐማራ። ብአዴናውያን ተጠንቀቁ። ከአቢይ አሕመድ ጋር እንዳትጨረገዱ።

"…ያልታወቁ ሀይሎች ምደረ ጠንቋሊ ሁላ ደኅና አያሳድራችሁ…!
3.9K views01:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 04:12:26
ነፍሰ ገዳዩ ቀጣፊ ደራሲ…!

•ግርማ የሺጥላን ከመግደሉ በፊት ኔትወርክ አጠፋ።
•ግርማ የሺጥላን ከገደለ በኋላ ከፖሊስ ቀድሞ፣ የግርማ ቤተሰቦች ሳይሰሙ እሱ መርዶ አረዳ።
•ገዳዮቹ በምርመራ ሳይታወቁ አስቀድሞ ፈረጀ።
•የግድያው ዜና ሳይሰማ ክልሎች ተመሳሳይ መግለጫ እንዲያወጡ አስደረገ። ዳራሲው ሃጫሉን ከገደለበት፣ እነ ዶር አምባቸውን ካስወገደበት ቀሽም ድራማ ሳይማር በግርማ የሺጥላ ደገመው።

"…ደስስ ያለኝ ነገር ሁሉም ሕዝብ መንቃቱ ነው። ፌስቡክ ገጹ ላይ ሄጄ ሳይ ሕዝቡ ገዳይ አንተ ነህ ሲለው አያሁ። በመንግሥት ሚዲያዎች ዜና፣ በኮሚኒኬሽን መሥሪያ ቤቱ መግለጫም ሥር የሕዝብ አስተያየት የአቢይን ገዳይነት ጮሆ የሚመሰክር መሆኑን ሳይ አምላኬን አመሰገንኩት።

"…ይሄ ደም ጠጪ የማይጠረቃ በላኤሰብ ልቡሰ ሥጋ አጋንንታም የሆነ ክፉ ገና ሰሞኑን ብዙ ሰው ይበላል። ተብታባው የሲጋራ ኩሽናው ብራኑ ጁላም ጦሩን ወደ ዐማራ ምድር ያዘምታል። ግን ቀምሶ ይወጣታል። የአቢይም ፍጻሜው ይሆናል።

"…ዐማራን በድሮን፣ በኦነግ ሠራዊት ሊያስወርር ይሞክር ይሆናል። ትግሬን ሸዋ አላስገባ ያለው ዐማራ ከዚያ የሚያደርገው አይመከርም። ከዚያ በፊት በአዲስ አበባ ዙሪያ የሰፈረው የአራጁ የኦነግ ሠራዊት አዲስ አበባ ላይ ጭፍጨፋ ሊሞክር ይችላል። ኋላ ግን ከአሩሲ፣ ከባሌና ከጅማ የመጣው የአክራሪው የኦሮሞ ወሃቢያ እስላምና ከወለጋ የመጣው ጽንፈኛው የኦሮሞ ጴንጤ እስላም ሞጆን አያልፍም፣ ሆለታን አይሻገርም። ይኸው ነው።

• አቢይ አሕመድ ነፍሰ ገዳይ ነው!
• ዐቢይ አሕመድ ጨፍጫፊ ነው!
• አቢይ አሕመድ ቀጣፊ ነው!
• አቢይ አሕመድ ዋሾ ነው!
• አቢይ አሕመድ ከሃዲ ነው!
• አቢይ አሕመድ ልቡሰ ሥጋ አጋንንት ነው!
• አቢይ አሕመድ ውሸታም ሳይሆን ራሱ ውሸት የውሸትም ፈጣሪዋ ነው።

• ማኔቴቄልፋሬስ…!
3.7K views01:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 04:12:26
ተቀበል…!

"…የፓርላማ አባሉ ዶር ሃንጋሳ ኢብራሂም ይናገራል። "ቀድመው ካልገደሉኝ ገዳዩን እኔው እነግርሃለሁ እያለ ነው።" አለቀ።

"…በዚህ ሰበብ ሰኔ ላይ የአዲስ አበባን ዲሞግራፊ ለመቀየር በአዲስ አበባ ያሉ የዐማራ ባለሃብቶችን፣ አርቲስቶችን፣ ምሑራንን፣ የሃገር ሽማግሌዎችን ለመጨፍጨፍ የተዘጋጀው የኦሮሙማው ጨፍጫፊ ቡድን ጭፍጨፋዬን ደርሶ ያስጥለኛል ብሎ ወደ ሚሰጋው የሸዋ ሕዝብ ለመዝመት የፈጠረው ፈጠራ ነው። አባቴ ሕዝቡ ሺ ኪሎሜትር ፈጥኖ ቀድሞሃል። የበሻሻው ጌጃ አራዳ ተባኖብሃል። ይደባለቃል፣ እድለኛ ከሆንክ ለፍርድ ትቀርባለህ አሊያም ትደመሰሳለህ። የንጹሐን ደም ዘር ማንዘርህን ፍዳ ያባላል።

"…ዐማሮች ዳይ ወደ ሥራ። ገዳዩ ይታወቃል። ኧረ ለመሆኑ። ሟቹ ገና መመታቱ ሳይታወቅ። ለሞቱ ኃላፊነት የወሰደ ቡድን ሳይኖር። ፖሊስ ምርመራ ሳይጀምር ሳይሆን ገና ወንጀል መፈጸሙን ሳይሰማ። እንዴት አቢይ አሕመድ ቀድሞ ሰማ…? እንዴትስ ገዳዮቹን ዐወቀ? ናትናኤል መኮንንስ ገዳይ የፋኖ ያላቸውን ሰዎች ስም ለመጻፍ እንዴት ፈጠነ? ጠንቋሊ ሁላ።

"…በዚህ ሰበብ ወደ ዐማራ ክልል ሕግ ለማስከበር በሚል ትግሬን ዐመድ ባደረግክበት መንገድ ወደ ዐማራ እሄዳለሁ የሚል የአረመኔው አቢይ ነፍሰ በላ አረመኔ ሠራዊት ከወዲሁ ቤተሰቡን ተሰናብቶ ይሂድ። አከተመ።

"…ገዳዩ አቢይ አህመድ ነው።
3.3K views01:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-28 04:12:25
"…እኔን የሚያስለቅሰኝ ይሄ ነው…!

"…ከፊታችን በሚመጡት ሳምንታት "ሕግ የማስከበር ዘመቻ" ብለው በዐማራ ክልል እንጀምረዋለን ብለው አፕሬሽን እንደ መግቢያ ያገለግላቸው ዘንድ አረመኔው አቢይ አሕመድ እና እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነብርሃኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰና በተመስገን ጥሩነህ የሚመራ የደኅንነት ኃይል በዛሬው ዕለት በዐማራ ሕዝብ ዘንድ የሚጠላውን ግርማ የሺጥላን በመግደል የጦስ ዶሮ ፍለጋውን ጀምሯል።

"…እነ አቢይ አሕመድ የግርማ የሺጥላ ብቻ በቂ ስላልሆነ ገና አጠገባቸው ካለው በሕዝብ ዘንድ የተጠላ ባርያ ገረዱ ጨምሮ ሌሎችንም የአማራ ባለሥልጣናት ለመብላት እቅዳቸውን አውጥተው መጨረሳቸው ነው የሚነገረው።

"…ወደ በቀል ሥራዋ የተመለሰችው ህወሓት ከኦነግ ኃይሎች ጋር በመሆን በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ኤርትራውያንን፣ የኢሳት፣ የግንቦት ሰባት ሰዎችን ጨምሮ፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ አክቲቪስቶችን፣ በተለይ ጁንታ ብሎ ባወጀው ጦርነት ላይ ህወሓትን በመቃወም በንቃት የተሳተፉ የዐማራና የትግሬ አክቲቪስቶችን ይበላቸዋል። ልክ ሰኔ 15 እነ ዶር አምባቸውን እና እነ አሳምነው ጽጌን ገድሎ የዐማራ ልዩ ኃይልን እንደጨፈጨፈው ሁሉ አሁንም የተወሰኑ የዐማራ ብአዴን ሰዎችን ደፍቶ ሲያበቃ ፋኖ ላይ ለመዝመት ዐማራን ለመጨፍጨፍ ይሞክራል።

"…የሰሜን ዕዝን ጨፈጨፉት አቢይ እና ወያኔ ናቸው። የቤንሻንጉል ጉምዝ ባለሥልጣናትን ወለጋ ላይ ጠብቆ የገደለው የኦሮሞ ኃይል ነው። ሙስጠፌን ለማስፈራራት ሲባል የፓርላማ አባሏን ሱማሌያዊት በአየር መንገዱ ውስጥ ያስረሸነው አቢይ ነው። ዛሬም ግርማን የገደለው አቢይ አሕመድ ራሱ ነው። ከዚያ ብርሃኑ ጁላ መጀመሪያ ሰሜን ሸዋ ላይ ይዘምታል። ሞክራት።

"…እኔ ግን የሚያስለቅሰኝ ይሄ ጭፍጨፋ ነው። አቢይ አህመድን ከነፓርቲው የሚበቀል ትውልድ እየመጣ ነው። አከተመ።
3.4K views01:12
ክፈት / አስተያየት ይስጡ