Get Mystery Box with random crypto!

ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekele3
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.50K
የሰርጥ መግለጫ

እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ዩቲቡ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 8

2023-04-22 12:20:36
استغفر الله العظيم.

"…ሙ - jibu እስኪጨርስ አላናጥበው ልጠብቀው ብዬ ነው እንጂ እኔማ ውይይታችንን እኮ አልረሳሁትም። አሁን ልጀምር ነኝ። ኢንቅርታ… ለዛ ኖ የዘገየሁት። ጠብቁኝ ልመጣ ነኝ።
3.4K views09:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-22 08:40:53
ቅዳሜ፦ ቅዱሳት አንስት ይባላል፦

"…እኔ ይህን በእጅ የተሠራውን ቤተ መቅደስ አፈርሰዋለሁ በሦስት ቀንም ሌላውን በእጅ ያልተሠራውን እሠራለሁ ሲል ሰማነው ብለው በሐሰት ሲመሰክሩበት።” ማር 14፥57-58 የተሰማው ከትንሣኤው በፊት ጌታ ተከሶ በጲላጦስ ፊት በቀረበ ጊዜ ነበር። ጌታ መያዙና መሞቱ እርግጥ ከሆነ በኋላ ትንሣኤውን ለማየት የጓጉትም ሴቶቹ ናቸው።

"…በዚህ ዕለት ሴቶቹ የአይሁድን ማስፈራሪያ ንቀው፣ የክርስቶስን አካል ሽቱ ለመቀባት ፍርሃታቸውን በክርስቶስ ፍቅር ለውጠው፣ ጨለማ ሳያግዳቸው በጋለ ፍቅር አካሉን መፈለጋቸው፣ ወደ መቃብሩም ሲመላለሱ ማደራቸው፣ ማርያምም ትንሣኤውን ቀድማ ስለማየቷ፣ ሴቶችም የመላእክትን ራእይ ስለ ማየታቸው፥ ቤተክርስቲያን የምታስተምርበት ዕለት ነው። ማቴ 28 ፥ 1-15፣ ማር 16፥1-8 ሉቃ 24፥1-12 ዮሐ 20፥1-18

"…በሐዲስ ኪዳን የሴቶች ተሳትፎ እጅግ ሰፊ ነው። ጌታ ከመረጣቸው 120 ቤተሰቦች መካከል 36ቱ ቅዱሳት አንስት ናቸው። ጌታ በዋለበት ውለው በአደረበት አድረው ያገለገሉትም ሴቶችም ናቸው። ባለሽቱዋ ማርያምና የይሁዳ እናትን ጨምሮ ብዙዎቹ ጌታ በንስሐ ጠርቶ ያቀረባቸው ናቸው። ሴቶች ቃሉን ለመማርም ትጉሃን ነበሩ። ማርያምም መልካም ዕድልን መርጣለች ከእርስዋም አይወሰድባትም። ሉቃ 10፥42 የሚል ምስክርነት የተሰጠውም ለሐዲስ ኪዳን ሴቶች ነው። ከልብ ስለሰሙት ሞቱ ላይ ቆመው ትንሣኤውን ናፈቁ።

“…መግደላዊት ማርያምና ሁለተኛይቱ ማርያም መቃብሩን ሊያዩ መጡ።…እንደ ተናገረ ተነሥቶአልና በዚህ የለም።…ፈጥናችሁም ሂዱና፦ ከሙታን ተነሣ…ብላችሁ ለደቀ መዛሙርቱ ንገሩአቸው። ማቴ 28፥1-7 ተብለው ትንሣኤውን ያበሰሩን ሴቶች ናቸው።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።
925 views05:40
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-21 21:24:21 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…በሱዳን የርስ በእርስ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው። ዜጎች ከካርቱም ወጥተው ወደ አጎራባች ከተሞች እየሸሹ ነው። የከተማ ውስጥ ጦርነቱም እንደቀጠለ ነው። በ3 ቀን ብቻ 45 የጦር ጀቶች ካሉበት ሳይነሱ ወድመዋል። የታንኩና የተሽከርካሪዎቹ አይወራም። አይነገርምም። ሆስፒታሎችም ወድመዋል። በብዙ ቁጥር ዜጎች እየሞቱም እየቆሰሉም ነው። እንዲያም ሆኖ አሜሪካ ዜጎቿን ለማውጣት አላሰበችም። በእሱ ፈንታ በሱዳኑ ጦርነት ሰበብ ተጨማሪ ወታደሮች ምሥራቅ አፍሪካ ጅቡቲ ለማስፈር መወሰኗን ነው ያሳወቀችን።

"…የበረኸኞቹ 2 ኃያላንና 7 የአረብ ሃገራት ወደ ኢትዮጵያ ይገባሉ የሚለው ትንቢት ብቻ የሚጠበቅ ይመስለኛል። በየመንና በሶሪያ ላይ የተራገፈው የምዕራባውያኑ የጦር መሣሪያ ከአሰብና ምጽዋ መጋዘን ወጥቶ በኢትዮጵያ ምድር ሊራገፍ ይችላል። ጅቡቲና ሱማሊያም የሠፈረው መንጋ ተፍተፍ ማለቱም አይቀርም። ነገርየው መቼ እንደሚጀመር አይታወቅምና ተዘጋጅቶ መጠበቁ ግን መልካም ነው የሚሉም አሉ። ከወር በፊት ካርቱም እንዲህ የጦር ቀጠና እሆናለሁ ብላ ለአፍታም አስባ እንዳልነበር ልብ ይሏል። አዲስ አበባም ሰምተሻል።

"…ሶሪያ ላይ የተፋጩት አማሪካ መሩ የምዕራቡ ዓለም ኃይልና ሩሲያ ናቸው። ሶሪያ ብትፈራርስም ፑቲን አላሳድንና መንግሥታቸውን ግን ታድጓል። የመን ስትወድም ሱዳን ሳኡዲን አግዛ በየመን ጦርነት ተሳታፊ ነበረች። የመን ፈራረሰች ሱዳን የየመን ርግማን በቶሎ የደረሰባት ይመስላል። የኦሮሞ ቦለጢቀኞች ዐማራን ካላንበረከኩ እረፍት የሚያገኙ ስለማይመስላቸው ከዐማራ ጋር ጦር መግጠማቸው የግድ መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው። ዐማራም ለመመከት፣ መልሶ ለማንከትም ተዘጋጅቷል። ሱዳን እርስ በእርስ መፋጀቷ፣ ግብፅም በሱዳን መዋረዷ አቢይን ወደ ዐማራ በቶሎ እንዳይገባ ቢያደርገውም ይቀራል ማለት ግን አይደለም። ምንአልባት ኮሌራ፣ ራብና አመፅ ካላዘገየው በቀር አብይ አህመድ መሞከሩ እንደሆን አይቀርም። ግባ ትቀምሳታለህ።

"…የዓለም ጦርነቶች ሁሉ ማሳረጊያ ግን ኢትዮጵያ ናት። እስልምናን የፈጠረችው የሮም ካቶሊክ እንደሆነች የሚተረጉሙ መተርጉማንም አሉ። ሮም ኃጢአት በይፋ ትሠራለች። እስልምና የሮምን ኃጢአት በይፋ ይቃወማል። ሕዝብም እስልምናን አድንቆ ትክክል ብሎም እንዲቀበል ጥቅሴ መሆኑ ነው። ኢትዮጵያ የሃይማኖቶች ሁሉ መነሃሪያ እንድትሆን ተበጅቶ ወደ ሥራ ከተገባ ቆየ። እስልምናና ፕሮቴስታንቲዝም በአንድ ፖፖ ካልተጠቀምን ካሉም ቆዩ። ተዋሕዶን የጋራ ጠላት ያደረጉት በዶግማና በቀኖና አንድ ሆነው እኮ አይደለም። ጥላቻው ነው ያገናኛቸው። ያስተሳሰራቸውም።

"…አስመራ ተወላጁ ትግሬ ቴዎድሮስ አድሃኖም፣ መሠረቱ የወሎ ዐማራ የጴንጤ እስላሙ የኦሮሞ ወኪል አቢይ አህመድ ለዓለም አቀፍ ከፍተኛ ሹመትና ሽልማት የታጩት በዕቅድ ነው። ደመቀ መኮንን የእንግሊዝ፣ ዐቢይ የአማሪካና የዓረብ ቋሚ ተቀጣሪ ናቸው እኮ የሚሉ አሉ። ሬድዋን ሁሴን፣ ሙፈሪያት ካሚል፣ አደም ፋራህ፣ የሰላም ሚንስትሩ ብናልፍ አንዷለም፣ ሽመልስ፣ አዳነች እና ጁላም በፀረ ዐማራነት ተጠምቀው ጉዳይ ለማስፈጸም የተሾሙ ናቸው።

"…በኦሮሞ ጴንጤና እስላሞች በኩል ክርስቶስ መሠረቷ የሆነችውን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶን የማፍረሱ ተግባር የሰይጣኑ ዓለም ዕቅድ መሆኑን የሚናገሩም አሉ። ሶሪያ፣ ህንድ፣ ግብጽ፣ አርመን በኦርቶዶክሳዊነታቸው ዋጋ ከፍለዋል። ዐማራና ትግሬም በኦርቶዶክስነታቸው በአረመኔዋ ኮሚኒስት በህወሓት ፈቃድ በጴንጤና በእስላሞቹ የብልፅግና መሪዎች ሴራ ተፈሳፍሰዋል። ገዳማትም ፈርሰዋል። ቅዱሳት መጻሕፍት ተዘርፈዋል። ካህናት መነኮሳት ታረደዋል። በዐማራም በኦሮሚያም እንደዚሁ ኦርቶዶክስ በመናፍቃንና በአህዛቦቹ ገዢዎች ፍዳቸውን ዓይተዋል። እያዩም ነው። ዩክሬንና ሩሲያም ኦርቶዶክስ መሆናቸውን ልብ ይሏል። ዐቢይ ለቡራኬ ሮም የሚመላለሰው ወዶ መስሎሃል።

"…በኢትዮጵያ የተሸነፈው የአውሬው መንፈስ ኢትዮጵያን በማፈራረስ ድልን ለመጎናጸፍ የቋመጠ ይመስሏል። በሶዳማዊነት ጉዳይ ሚጢጢየዋን እስላማዊት ሃገር ኳታርን የሚያከብረውና አንዳች ነገር በተቃውሞ የማይተነፍሰው ዓለም በዚሁ ጉዳይ ሩሲያን ግን ሚሳኤል ተኩሼ ካላንበረከኩ ይላል። በኢትዮጵያ ሕግ ሰዶማዊነት ፀያፍ ቢሆንም ዛሬ ሥልጣን ላይ ለመውጣት፣ በንግድ ሃብት ለማፍራት የዚህ ነውር ተጠቂ መሆን ግድ ይላል። ይሄ ኢትዮጵያን የማንበርከኪያው አንደኛው መንገድ ነው።

"…አርቴፍሻል ራብ፣ የኢኮኖሚ ድቀት፣ ሕዝብን አስጨንቆ መግዛት። ነውረኛው የተደላደለ ኑሮ ሲኖር፣ አማኙና ሃቀኛው እንዲቆረቁዝ በማድረግ ነውረኛው የብልጭልጩ የብልፅግና መንገድ ትክክለኛ ነው በማለት ሰው ሁሉ የሞራል፣ የግብረገብ እና የሃይማኖት አሴቱን አሽቀንጥሮ ወደ ነውሩ ዓለም እንዲቀላቀል ማድረግም የዚሁ ዓለም አቀፍ ተልእኮ አንዱ አካል ነው። ለመዘነጥ እንኳ መጰንጠጥ የግድ እንደሚልህ ብዙ ሰው እንዲያምን እየተደረገ ነው። ባንኮች ለብድር ገንዘብ የሚያፈሱልህ ከጰነጠጥክ ወይ ከሰለምክ መሆኑን ሠርተውበት ተግባራዊ አድርገውታል። ጴንጤም እስልምና ባለባንክ ናቸው።

"…እስላሙ የዓረቡን፣ ጴንጤው የምእራቡን ዓለም ባሕል በነፃነት እንዲያስፋፉ ነገሮች ተመቻችተውላቸዋል። ብሔራዊ ቋንቋ፣ ፊደል ወዘተረፈ እንዳይኖረን በብርቱ ተሠርቶ ተግባራዊ ተደርጓል። ሱሉልታና ቃሊቲ አማርኛ ከትምህርትም ከሥራም ቋንቋነት ተወግዷል። አማርኛ የዐማራ ነው ተብሎ ስለተከሰሰ ዜጎች እስላሙ ዓረብኛን፣ ጴንጤው እንግሊዝኛን ብሔራዊ ቋንቋው እንዲያደርግ ተወስኖ ወደ ሥራ ተገብቷል። ነውር በሃገሪቱ ተንሠራፍቷል።

"…ሕዝብ ከመጠን በላይ በዝቷል። የሃገር ኢኮኖሚ ተንኮታኩቷል። ኢትዮጵያን የሚመሩት ጎረምሶች ከዚህ ድቀት የሚወጡበት ዕውቀት የላቸውም። ሕዝብ መቀነሥ አለበት ብለው በመወሰናቸው ሕዝብን በራብና በጦርነት፣ በጭንቀት፣ በማሳበድ፣ በማሰደድ፣ በማሰር፣ በበሽታም በመጨፍጨፍ ላይ ተጠምደዋል። የዐማራና የአፋር፣ የኢትዮጵያ መከላከያ ሳይጨመር ከትግሬ ብቻ አንድ ነጥብ 2 ሚልዮን ወጣት ህጻን ሽማግሌ በጦርነቱ እና በጥይት ተጨፍጭፎ አልቋል። ይሄ ዘግናኝ ነው። አሁን ደግሞ የዐማራው ቁጥር ይቀንስ ዘንድ ቢለዋው እየተሳለለት ነው።

•…ከኤርትራ በረሃ እና ከዐማራ ገጠሮች በሚነሱ ጥቂት የመስቀሉ ጦረኞች አማካኝነት ኢትዮጵያም ምሥራቅ አፍሪካም ነፃ ይወጣሉ። እስከዚያው ግን የተማረ ይግደለኝ፣ ምላስ ያለው ያግባኝ ባልነው መሠረት በአፈ ቅቤ ሆደ ጩቤው በአቢይ አሕመድ አርጩሜ ምዕራባውያኑ እነሱ ወዳዘጋጁልህ ወጥመድ የግድህን እስክትገባ ድረስ ተራ በተራ ትዠለጣታለህ። ዳዊትህን ያነሣህ፣ ማዕተብክን ያልበጠስክ ግን እልል እያልክ ትሻገራታለህ። ፈሳሙን አትፍራው። አባቴ ይሙት እውነቴን ነው። ስቃዥ የምጽፈው መሆኑ ይታወቅልኝ ብሏል።

• ድርጅቱ…!
2.1K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-20 09:17:05
ሐሙስ፦ አዳም ሐሙስ ይባላል፦

"…ከጌታ ትንሣኤ በኋላ በአምስተኛው ቀን ቅድስት ቤተ ክርስቲያን አባታችን አዳም እና እናታችን ሔዋን ከትንሣኤው ጋር ተያይዞ ታስበው ይውሉ ዘንድ አዳም ወር በገባ በ6 ከኢየሱስ እና ከእነ ቅድስት አርሴማ ጋር አብሮ የሚከበር የወርሀዊ በዓል ሥርዓት የተሠራለት ቢሆንም የዛሬው ግን አባታችን አዳም ከልጅ ልጅህ ተወልጄ፣ በሜዳህ ድኼ፣ በእንጨት ላይ ተሰቅዬ ከ5 ቀን ተኩል በኋላ አድንህሃለሁ ተብሎ የተሰጠው ተስፋና የተገባለት ቃል ኪዳን ተፈጽሞ አዳምና ልጆቹ ነጻ የወጣበትን አስበን የምንውልበት ዕለት ነው።

"…አባታችን አዳም በሦስት ነገር ወደቀ። በተዋሕዶ፣ በመብልና በእጽ ምክንያት ወደቀ። ሰይጣን ከቆንጆዋ እባብ ተዋሕዶ፣ እባብን መስሎ፣ እባብንም አሕሎ አዳምና ሔዋንን ሰብኮ፣ ጌታ እግዚአብሔር እንዳትበሉት፣ የበላችሁ ቀን የሞት ሞትን ትሞታላችሁ ብሎ የከለከላቸውን ዕጽ በልተው ሞቱ። በዚህ ምክንያት የሞቱትን አዳምና ሔዋንን ለማዳን እግዚአብሔር ወልድ ወደዚህ ምድር መጣ።

"…ሰይጣን በእባብ ገላ ተዋሕዶ እንዳዋረደው፣ ጌታም ከአዳም የልጅ ልጅ ከእመቤታችን ከሥጋዋ ሥጋ ከነፍሷ ነፍስ ነስቶ ሰው ሆኖ በተዋሕዶ ተገልጦ አዳነው። አዳም በዕፅ ምክንያት እንደ ሞተ የሚያውቅ ጌታም በዕለተ አርብ በ17 ክንድ ዕፀ መስቀል ላይ ተሰቅሎ አዳነው። በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳም "ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ የዘላለም ሕይወት አለው፥ እኔም በመጨረሻው ቀን አስነሣዋለሁ… ሥጋዬን የሚበላ ደሜንም የሚጠጣ በእኔ ይኖራል እኔም በእርሱ እኖራለሁ። ዮሐ፥ 6፥ 54-56 በማለት በመብል ምክንያት የጠፋውን አዳምን የራሱን ሥጋና ደም መብልና መጠት አድርጎ አደነው።

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኀይል ወሥልጣን
አሰሮ ለሰይጣን
አግአዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም።
2.2K views06:17
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 21:24:01 የተበላ ዕቁብ…!

"…ዘመዴ ትላለች ከወደ ኦህዴድ ኦነግ ቢሮ የመጣችው ወፌ። ዘመዴ… ባለፈው ሳምንት አብይ አህመድ የኦሮሞ ታዋቂ ሰዎችንና የሀገር ሽማግሌዎችን በድብቅ ሰብስቦ ነበር። የስብሰባው ዋና ዓላማም "በዐማራ ክልል ላይ የተጋረጠብን ችግር እጅግ ልንገነባ ላቀድነው ሥርዓት እጅግ አደገኛ ነው። የትግሬ አስጊ አይደለም። የሚፈልጉት ነገር ስላለ እንደ ፈረስ ልንጋልባቸው እንችላለን። የዐማራውን ደንቃራ ተረባርበን በጊዜ ካላስወገድነው አደጋው ከባድ ነው።

"…ስለዚህ ከአሁኑ ተዋቂ የሃገር ሽማግሌዎችን መርጠን ለጊዜው እግራቸው ላይ በመውደቅ በሽምግልና ስም ማቀዝቀዝ፣ ከዚያ የቡድን መሳሪያዎችን እንዲያስረክቡ ማድረግ፣ ከዚያ የኃይለኞቹን ማንነት በደንብ መለየት በመጨረሻም ላይመለሱ ድራሻቸውን የማጥፋት ሥራዎችን መሥራት ይኖርብናል በማለት በመመካከር ከኦሮሞ ልሂቃን ጋር ከስምምነት ደርሰው ወደ ሥራ ለመግባት ተማምለው ተለያይተዋል።

"…በዚሁ ውሳኔ መሰረት ከነገ ሚያዝያ 12/2015 ዓም ጀምራቹሁ በክልሉ ውስጥ ለሚንቀሳቀሱ የፋኖ አመራሮች የሚታመን ሰው በመላክ አነጋግሩ በማለት አብይ አህመድ ለአማራ ክልል አመራሮች ትዕዛዝ አስተላልፋል። እናም ይህን መመሪያ የተቀበሉት እነ ግርማ የሺጥላ ነገ ሚያዝያ 12/2015 ዓም በባህርዳር ስብሰባ ጠርተዋል። 

"…ሌላው በቁጥር 4 የሚሆኑ የመከላከያ ጀኔራሎች በሰሜን ሽዋ ዞን ታዋቂ የሆኑ የኢፋት ተወላጅ ሽማግሌዎችን ዛሬ ሚያዝያ 11/2015 ዓም ወደ መከላከያ ሚኒስትር መሥሪያ ቤት በመጥራት "የኢፋት ፋኖዎችን አስታግሱልን፣ አርፈው ይቀመጡ፣ የያዙትን የቡድን መሳሪያዎች ያስረክቡ፣ የነፍስ ወከፍ መሳሪያዎችን መያዝ ይችላሉ፣ በአካባቢው የሚደረገውን የፀጥታ ኃይሎች እንቅስቃሴ አይግቱ፣ ይህን መፈፀም አለባቸው ለዚህም። ለዚህም የ 4 ቀን ጊዜ ሰጥተናል ከ 4 ቀን በኋላ ምላሹን አሳውቁን በማለት ዛሬ ለሽማግሌዎች ትዕዛዝ ሰጥተዋል።

"…ሽማግሌዎችም መልሰው "እናንተ እንዴት አውቃቹሁ ጠራቹሁን? በምን መስፈርት ነው የሽምግልና ምርጫው የተደረገው? በማለት የጠየቋቸው ሲሆን ጄነራሎቹም መልሰው ይሄን የእናንተን መረጃ ከነ ስም ዝርዝራችሁ የሰጡን የሰሜን ሸዋ የክልሉ የብልፅግና አመራሮች ናቸው። እናም በአስቸኳይ መልስ አምጡ ብለዋቸዋል። ብላኛለች ርግቤ። በቀጣይ የሚሆነውን እንዲሁ ይዤልህ እመጣለሁም ብላኛለች ርግቤ።

"…የጎንደሩን የፋሲል ግንብ ዱላ ቀረሽ ስብሰባ ነገ እመለስበታለሁ። አይ ሽምግልና። ተባነነበት እኮ። አባ ገዳ ኦነግን መርቆ እየሸኘ፣ የዐማራ ጳጳስ፣ ቄስ፣ ሼክ መስቀል፣ ታቦትና ቁርአን አስይዞ የሚዘበዝበው ነገር የተበላ እቁብ ሆኗል። በእኔ በኩል ፋኖ ጋር ሽማግሌ ሆኖ የሚመጣውን ማንኛውንም አካል "እግሩን ሰብሮ" የዶሮ ጠባቂ ማድረግ ነው በል በል ይለኝና ሳስበው ደግሞ ክፉ ተናገርክ እባላለሁ ብዬ ዝም በል በል ያሰኘኛል። እናንተስ በሽምግልናው ጉዳይ ምን ታስባላችሁ…?

• ወፎቼና ድርጅቱ ነኝ…!
1.3K views18:24
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 19:30:41
"…ባለፈው ዓመት ወያኔ ደሴ ሳትደርስ፣ ወልዲያም ሳትገባ፣ ገና ወደ ቆቦ ስትንደረደር አሜሪካ ባሏት ሚዲያዎች ሁሉ ተጠቅማ የአሜሪካ ዜግነት ያላቸውን ዜጎቿን በሙሉ ከአዲስ አበባ አስወጥታ ናይሮቢ እንዲከትሙ አድርጋ ነበር። ወያኔ አዲስ አበባን ልትይዝ ነው ብላም ለያዥ ለገናዥም አስቸግራ ነበር። ኧረ ተይ አሙካ፣ ወያኔ አዲስ አበባ የሚያስገባ አቅም የላትም። ዐማራን ለማድቀቅ አንቺ፣ ኦሮሞዎቹ የጦር ጀነራሎች እና የትግሬ የሂዊ ተላላኪዎች የፈጠሩት ነገር ነው ብትባል እምቢኝ አለች።

"…ዘንድሮ በሱዳን…!

"…ሩሲያና ኤርትራ የሚደግፉት የሱዳን ልዩ ኃይል አዛዥ ኤሚቲ፣ አሜሪካ፣ አቢይ እና ግብፅ የሚደግፉትን አልቡርሃንን ቀጥቅጦ፣ ቤተ መንግሥቱን፣ የደኅንነት እና የመገናኛ ብዙሃንንን ተቆጣጥሮ፣ አየር መንገዱን እና ሆስፒታሎች ወድመው፣ ከዚህም አልፎ በጦርነቱ ካርቱም ላይ የአሜሪካን ኤምባሲን ብረት ለባሽ መኪና በ100 ጥይት ተበሳስቶ፣ የአውሮጳ ኅብረት አምባሳደር ከሞት አምልጦ፣ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ተዘርፎ፣ ነውር ተሠርቶበት እያየች ምን ብትል ጥሩ ነው…? "ዜጎቼን ከሱዳን የማስወጣት እቅድ የለኝም።"

"…ወያኔ ገና ከመቀሌ ስትነሣ ዜጎቻችንን ከአዲስ አበባ እናውጣ ያሉት አማሪካ እና የአውሮጳ ኅብረት በዋግነር ግሩፕ ድጋፍ ካርቱምን ቺቺኒያ ካስመሰላት ጦርነት ውስጥ ግን ከጃፓን በቀር ሌሎቹ ዜጎቻችንን ንቅንቅ አናደርግም ማለታቸውን ሳይ "ወያኔ በቃ ጭራቅ፣ ቡልጉ ነበረች እንዴ ብዬ ለማሰብ ተገደድኩ።

"…የእግዚአብሔር ሥራ ግሩም ነው። ለዐማራ የታሰበው ለግብጽ፣ ለወያኔና ለብልጽግና ሆኗል። ጎንደር ሊገባ የነበረው የሳምሪ ጦር አልቡርሃንን ሊረዳ ወደ ኋላ ተመልሷል። ጦርነቱ ከሱዳን ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ ይችላል። ተዘጋጅቶ መጠበቅ ነው።

•ለማንኛውም ግን ማርያምን ዐማራና ኢትዮጵያ ያሸንፋሉ…!
2.0K views16:30
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 17:19:08
ሸኔ በሶደሬ…!

"…አንተ የዐማራ ልዩ ኃይል ይፍረስ፣ የዐማራ ፋኖ ይደምሰስ የሚለውን የብርሃኑ ጁላ፣ የከሃዲው አበባው ታደሰ፣ እና የገልቱ ብአዴን መሪዎችን ዲስኩር ትቀባበላለህ እዚህ አዲስ አበባ ጫፍ፣ ከአፍንጫዋ ስር የሽመልስ አብዲሳና የአብይ አሕመድ ፕላን ቢ ጦር በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ገዳም ላይ በቦንብ የታገዘ ጥቃት ይፈጽማል።

"…ትናንት ከምሽቱ 3:00 እስከ 4:00 ሰዓት ሲሆን በምሥራቅ ሸዋ ሀገረ ስብከት ከናዝሬት በቅርብ ርቀት የሚገኘው የሶደሬ ፈለገ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተክርስቲያን ላይ ከ50 በላይ በሚሆኑ የታጠቁ ኃይሎች ከፍተኛ ጉዳት እንደደረሰበት ተነግሯል። ታጣቂዎቹ አልከፈት ያላቸውን የቤተ መቅደሱን በር ቦንብ አፈንድተው ሰብረው በመግባት ንዋያተ ቅድሳቱን አውድመዋል። የቤተ ክርስቲያኑን አስተዳዳሪ ቤትም ሰብረው በመግባት በወቅቱ አስተዳዳሪው ባይኖሩም በቤት ዕቃዎች ላይ ጉዳት፣ በካህናቱም ላይ ከፍተኛ ማዋከብ ፈጽመዋል፣ የደብሩንም ገንዘብ አፍነው በመውሰድ እስከአሁን እንዳልለቀቋቸው ተሰምቷል።

"…ዘመኑ የኦሮሞ ነው። መሪዎቹ ፅንፈኛ የወሐቢ እስላሞች እና ፅንፈኛ የጴንጤ እምነት ተከታዮች ናቸው። ሁለቱም በኦርቶዶክስ መጥፋት ስምም ናቸው። ኦነግ ሸኔ የአገዛዙ የበኩር ልጅ ነው። የተፈጠረውም ዐማራና ኦርቶዶክስን እንዲያጸዳ ነው። ዘመኑ ዘመነ መከራ ነው። መከራውም በተዋሕዶ ላይ ነው። እንዲህ እንደሆነ ግን አይቀርም። አኬሩም መገልበጡ አይቀርም። እስከዚያው ይጨማለቁብን። አይ ብርሃኑ ጁላ። ይሄንንስ ፋኖ ነው የፈጸመው አይደል…? እስቲ ናና ዘብዝብ።

"…ለማንኛውም ሶደሬ፣ ዝቋላ ዙሪያ፣ ሞጆ መስመር፣ ዝዋይ፣ ሰበታ አለ የሚባለው ሸኔ ሸኔ ሳይሆን ራሱ መከላከያው ሸኔ ሆኖ እንደሚገድል ይታወቅ።

"…ይሄም ተመዝግቦ ይቀመጥ።
2.5K views14:19
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-19 11:43:11
ለዐማራ ልዩ ኃይል አድርሱልኝ…!

"…ወደ መከላከያ የምትጠቃለል የዐማራ ልዩ ኃይል በኦሮሚያ የሚጥብቅ እንዲህ በወጠጤ መደፋት ነው። እነ ብርሃኑ ጁላ፣ እነ አቢይ አሕመድ፣ እነ ደመቀ መኮንን፣ እነ ጄነራል አበባው ታደሰ እንዲህ ቂጡን ባልጠረገ የኦሮሞ ወጠጤ ሊያስፈጁህ ነው። ደመ ከልብ ሊያደርጉህ ነው። ደጋግመህ አስብበት።

"…በዚህ መልኩ እየተነገረው ርቦት፣ ፈርቶ፣ በእምቢተኝነት፣ በጥጋብ፣ በድንቁርና እና በመሃይምነት እልም ብሎ የሚገባ ካለ ይበለው። ያነጥፈው፣ እንዲህ በአስከሬኑ ላይ ቆሞ የኦሮሞ ወጠጤ ይፈንጭበት። ምከረው፣ ምከረው፣ እምቢ ካለ መከራ ይምከረው።

"…የነቃችሁ ዐማሮች ግን ሽምግልና የሚባል የዐማራ አምካኝ፣ ጀግና ቆርጣሚ ሥርዓት ላይ አረመኔ አህዛቡ መንግሥት ታቦት እና መስቀል አስይዞ የሚልካቸውን ጳጳሳት፣ ካህናት፣ መነኮሳት፣ ሽማግሌዎችና ባለ ሃብቶችን ለጊዜው መስማት ካላቆምክ ትበላለህ። ተናግረናል። ጳጳሱ አያድንህም፣ መነኩሴው አያስጥልህም። ተናግረናል። እምቢ ብለህ በዥልነትም፣ በየዋሕነትም እጅ ከሰጠሕ በኋላ ለሚደርስብህ ኪሳራ ከጠላትህ ይልቅ እኔ ወዳጅህ ነኝ ያማላግጥብህ፣ ይበልህ፣ ደግ አደረገ የምልህ።

"…ዐማራ የጨነቀው፣ የቸገረው እንደ ኦነግ፣ እንደ ህወሓት ጨካኝ መሆን ብቻ ነው። ጨካኝ ስትሆን ትከበራለህ፣ ሊወጋህ የመጣን ጠላት እንደ ከብት ዐሞሌ እያላስክ አትንከባከበው። ሊገልህ የመጣውን፣ የተኮሰብህን ቀድመህ ቀንድሸህ ጣለው። ስብከቱን ሌላ ጊዜ ትደርስበታለህ።

"…ያልነቃ ዐማራ የትም ይሁን የት ይበላል። ይዋጣል። የነቃ ዐማራ እግዚአብሔርን ይዞ ያሸንፋል። የኦሮሞ እና የትግሬ ወጠጤ መጫወቻ ከመሆን ራስህን ጠብቅ።

• በዚህ ምክር ቅር የሚልህ ካለህ በአናትህ ተተከል። ኬሬዳሽ።
3.4K views08:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 22:26:33
ዐማራ…!!

እግዚአብሔር ነውና ከአንተ ጋራ
በምድር ማንንም ሳትፈራ
ለጠላት አንጀትህ በፍፁም ሳይራራ
ወጥርና መክት ጀግናዬ ዐማራ።


• ወይ ፍንክች…! ወይ ንቅንቅ…!  ወጥር አልኩህ አንተው… !
836 views19:26
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-04-18 13:47:54
ለዐማራ ልዩ ኃይል አድርሱልኝ…!

"…ብርሃኑ ጁላ፣ አቢይ አሕመድ እና ሽመልስ አብዲሳ ከእነ ደመቀ መኮንን ጋር ሆነው የዐማራ ልዩ ኃይልን አፍርሰው መከላከያ ግባ የሚሉት ለዚህ ነው። አሟሟቱን ሕጋዊ ለማድረግ። ለዚያ ነው የሚወተውቱት።

"…ይሄ የምታዩት መከላከያ ዳርፉር ሄዶ ሰላም የሚያስከብር፣ በስሙ ብቻ ጠንካራ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ከመንደር የማይወጣው የኦነግ መፈንጫ፣ ማላገጫ፣ መሳቂያ፣ መሳለቂያ ሆኗል። ኦሮሞዎቹ የኢትዮጵያ መሪዎች፣ ኢትዮጵያዊውን ተቋም እንደ ህወሓት ከመበተን ይልቅ፣ በዚያው እያለ ማዋረድ፣ መስጨፍጨፍን መርጠዋል።

"…ኦሮሞው የፌደራል ፖሊስ ደመላሽ ገብረ ሚካኤል ወለጋ ወስዶ 20 ሺ በላይ የዐማራና የኦርቶዶክስ፣ የደቡብ ልጆችንም አስፈጅተው፣ መሣሪያውንም ሸኔ የሚሉት ኦነግ እንዲታጠቀው አድርገዋል። አሁን ደግሞ የዐማራ ፋኖ፣ የዐማራ ልዩ ኃይልን እና የደቡብ ልጆችን በመከላከያ አስገብተው ሊፈጇቸው ወስነው ጨርሰዋል ነው የሚባለው። በኦነግ ተገደለ ሊባልልህ ነው።

"…መከላከያውን ግን ወያኔ እንደ ከፍት የነዳቸው ሳያንስ አሁን ደግሞ ኦነግ እንደከፍት ነዳው መባልን መስማት በጣም አድርጎ ያበሳጫል። ዐማሮች እና ቤርቤረሰቦችዬ በአረመኔው አቢይ አሕመድ እና በምርኮኛው ብራኑ ጁላ ከመበላታችሁ በፊት ደጋግማችሁ አስቡበት። ተጠንቀቁበለማለት ነው። በብላሽ አትሙቱ።

"…ማርያምን አዛኜን ዐማራና ኢትዮጵያ ግን ያሸንፋሉ…!
3.0K views10:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ