2023-03-02 21:06:08
በአዲስ አበባ እየተፈፀመ ያለውን የጥቁር ጣልያኖች የውንብድና ተግባር እያየንም ቢሆን እንኳ ምስጋናም ቃለ መሃላም ማቋረጥ ነውር ነውና ስለ አረመኔዎቹ ነውርም ለማውራት ቢሆን ሰፊ ጊዜ ስላለን በቅድሚያ ቃላችንን አክብረን ያው 3 ሺ ሰው ሁሉ በትእግስት፣ በጥብአት፣ በሥነ ሥርዓት ጨክኖ አመስግኖ እስኪጨርስ ብንጠብቅም ጭራሽ ይሄን ጦማር እስካዘጋጅ 1ሺ ሰው ተጨምሮ 4ሺ ሰው አምላኬን አመስግኗል። እግዚአብሔር ይመስገን።
"…የዓድዋ ድል ዝግጅታችን በተያዘለት መርሀ ግብር መሠረት ሰዓቱን ጠበወቆ ይቀጥላል። በጩኸት፣ በሁከት፣ በግርግር፣ በእርግማን፣ በስድብ፣ በሆያ ሆዬ መርሀ ግብራችንን ማወክ ግን ክልክል ነው። እንደዚያ ማድረግን አልፈቅድም። እኔ ዘመዴ ዘመድኩን በቀለ፣ አክሊለ ገብርኤል እንደ ተራ አክቲቪስት ነገርየውን ማጯጯህም አልፈልግም። ከዚያ ይልቅ የአገዛዙን ነውር ለመልካም ነገር እንዴት እንጠቀምበት? እያልን የምንወያይበት እንጂ የምናለቃቅስበትም አይደለም። መሆንም የለበትም። በአንድ በኩል ለለውጥ የሚዘጋጅ ማኅበረሰብ መፍጠሪያ፣ በሌላ በኩል ደግሞ በብልፅግና ፍቅር ወድቆ ከብልፅግና ጋር እለት በእለት ያለ ድካም ተራክቦ ለመፈጸም አንሶላ የሚጋፈፍ ጋለሞታ ሁሉ ብልፅግና ማለት ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ መሆኑን በተግባር ያየንበት ዕለት መሆኑን እያወጅን በዚህ አራጅ መናፍቅ መንግሥት ዙሪያ የተሰባሰበውን መንጋ ሁሉ አንገት እያስደፋን አዲስ የመወያያ አጀንዳ የምንከፍትበት አዲስ የትግል ምእራፍ የምንጀምርበት በዚህም ዙሪያ የምንወያይበት እንጂ የምንቆዝም መሆን አይገባም።
"…ብልፅግናንና የአቢይ አሕመድ ማንነትን ለማወቅ ረፍዷል? አዎ ረፍዷል። ነገር ግን ቢረፍድም ይሄን ነውረኛ አቅመቢስ አራጅ ልኩን ለማሳየት ከበቂ በላይ አቅምና ደቂቃ አለ። ለእኔና እኔን ለመሰሉ የዚህን አፈ ቅቤ ልበ ጩቤ አረመኔ አራጅ አሳራጅ አፓርታይዳዊ የአቢይ አሕመድ አገዛዝ ዛሬ የፈፀመው ነውር አያስደነግጠንም። ይልቁኑ እርሱን የማያውቁት በይበልጥ እንዲያውቁት የሚያደርግ ተግባር ፈጽሞ በእኛ በአቢይ አካሄድ ዙሪያ የተቃውሞ ጥያቄ ላለን ሰዎች ተጨማሪ አዲስ የሚሰባሰብ ጨርቁን የጣለ እብድ ቢያመጣልን እንጂ እኛ ቀደም ብለን በአገዛዙ ያበድን አይሞቀን፣ አይበርደን። ይብላኝ በአቢይ አሕመድ ዛሬ ማበድ ለጀመራችሁ እንጂ እኛማ እየበረደልን አብደን አብደን ወጥቶልን ድነን በየፊናችን መፍትሄ ፍለጋ እየባዘንን እንገኛለን። እንኳን ደኅና መጣችሁ አዳዲስ እብዶች።
"…ዛሬም ምንድነው የምናደርገው ያልን እንደሆነ በጨዋ፣ በሥነ ሥርዓት የታነፁ ኢትዮጵያውያን በሚርመሰመሱበት በቴሌግራም ፔጃችን ላይ ታላቁን የዓድዋ የድል በዓላችንን የሆነውን ሁሉ ለመማሪያ እያደረግን በተረጋጋ መልኩ ደስስ እያለን የድል በዓላችንን እናከብረዋለን። እናጣጥመዋለንም። እነሱ የፈለጉትም እኛን መረበሽ፣ ማበሳጨት እና ማወክ ነበር። እኛ ግን ታላቅነታችንን ማስመስከር የምንችለው የአናሳና የበታችኝነት ስሜት ለሚያሰቃያቸው ጥቁር ጣሊያኖች አጀንዳ ሰጥተን፣ እኛ ቪቫ ምኒልክ፣ ቪቫ ዓድዋ ስንል መዋል ነው።
"…ወራዳነታቸው፣ ፀረ ኢትዮጵያ፣ ፀረ ምኒልክ፣ ፀረ ኦርቶዶክስ፣ ፀረ ዐማራ፣ ፀረ ሰሜን፣ ፀረ ዓድዋ፣ ፀረ ጣይቱ፣ ፀረ አርበኞች መሆናቸውን፣ ጨፍጫፊ፣ ገዳይ፣ አረመኔ መሆናቸውን እያሳየን፣ በአቢይ አሕመድ አገዛዝ ተስፋ ያልቆረጡት ሴፍቲኔተሮችን ተስፋ እንዲቆርጡ፣ እርማቸውን እንዲያወጡም እያደረግን ነገር ግን የድል በዓላችንን በአሸናፊነት ስሜት በደስታ፣ በፍቅር፣ በአርበኝነት መንፈስ ስናከብርና ስናጣጥም እንውላለን። አንዳችሁም አትረበሹ፣ አትጨነቁም፣ አትብከንከኑ።
"…አሁን በኦሮሚያ ይፈጽሙ የነበረውን መከራውን ሁሉ የወለጋውን እርድ ጭምር ስበው ወደ መሃል ሃገር እያመጡት ነው። ይሄ ምልክት ነው። ሙከራም ነው። ሙቀት መለኪያም ነው። ምዕራብ፣ ምሥራቅ፣ ሰሜንና ደቡብ ሸዋ ከአዲስ አበባ በቅርብ ርቀት ላይ ዐማራን አርደው፣ አፈናቅለው ሞክረው አይተውታል። ሰሞኑን በአዲስ አበባ ዙሪያ በሺዎች የሚቆጠሩ፣ ከኦሮሞ ውጪ የዐማራ፣ የትግሬ፣ የጉራጌ፣ የወላይታ፣ የከምባታ ወዘተ ቤቶችን በግሬደር አፍርሰው፣ በጥይት ነፍሰጡር ገድለው፣ ሕጻናት በጅብ አስበልተው አይተውታል። የሕዝቡን ዝምታ እንደፍርሃት፣ እንደ ሽንታምነት፣ እንደ ቅዘናምነት ቆጥረውታል። በእርግጥ እነሱ መሬት ላይ በሚገባ ሠርተውታል። ይሄ ታዲያ ለአዲስ አበባ የሙቀት መለኪያ ቴርሞ ሜትር ነው። ምልክትም ነው።
"…እኔ ትናንትም፣ ዛሬም ነገም የምለው ለዚህ በኦሮሞ ስም ይህን ታይቶ የማይታወቅ ዘግናኝ ግፍ ለሚፈጽም መንግሥት ተብዬ ማስገጃ መፍትሄ የምለው ወሬ ትቶ መሬት ላይ ሥራ በመሥራት ኮምጨጭ ብሎ ለመጋፈጥ መወሰን ነው። ሌላ ምንም አማራጭ የለም። ብትተወው የማይተውህ፣ ብትሸሸው የማይለቅህ፣ ብትለምነው፣ ብትማፀነው የማይምርህ አረመኔ ርህራሄ ያልፈጠረበትን ጉድ እንዴት አድርገን እንገላገለዋለን ለሚለው መልሴ "እንጃባክ እኔ ምን ዐውቅልሃለሁ" ነው የሚሆነው። መልሱ በኪስህ ነው። መልሱ የጨነቀው፣ የቸገረው፣ በፊት በችርቻሮ፣ አሁን በጅምላ ዘሩ እየጠፋ ያለው ሕዝብ ጋር ነው ያለው። የራበው ሆዱን ለመሙላት፣ የጠማው ጥሙን ለማርካት፣ የበረደው እርቃኑን ለመሸፈን ሃሳብ አመንጭቶ መፍትሄ ለራሱ እንደሚያመጣውና የጎደለውን እንደሚያሟላው ሁሉ ነፃነቱን ተገፍፎ በባርነት ውስጥ የወደቀውም ሕዝብ በባርነት ውስጥ መውደቁን ካመነና እኔ ብሞትም መጪው ትውልድ በነፃነት ይኑር ብሎ የቆረጠ፣ የወሰነም እንደዚያ እንደሆን፣ ይሄንንም ውሳኔ ካመነ እና ነፃ ለመውጣት መንገዱን ከጀመረ ያን ጊዜ መፍትሄውን ያገኛል። ነፃነት ደግሞ በነፃ በብላሽ አይገኝም።
"…መርሀ ግብራችን ይቀጥላል። ሰከን፣ ረገብ፣ ባለ መልኩ በተረጋጋ፣ በጨዋ ደንብ ይቀጥላል። ደግሞ ኦነግ ፊት አይለቀስም። ኦነግ ፊት መበሳጨት አያስፈልግም። ለአራጅ ኦነግ የሚያስፈልገው ምኒልክ፣ ጣይቱ፣ ዓድዋ ሲሉ መዋል ብቻ ነው። ለሰይጣን መስቀል፣ ለወያኔና ለበለፀገው ኦነግ ደግሞ ምኒልክ፣ ዓድዋና ጣይቱ አስለፍላፊ ጠበል ናቸው። አዲስ አበቤ ብቻ ሳይሆን አጠቃላይ ኢትዮጵያውያን ግን ለመፍትሄው ከወዲሁ ተዘጋጁ። ይሄ ፈሪ፣ ቦቅቧቃ፣ ሴትና ሕጻን ሽማግሌ አራጅ መንግሥት ከዚህ በላይ ውድመትና ጥፋት ሳያመጣ በጊዜ ምሱን ለመስጠት ዐውቀን መዘጋጀት እንጂ መንበጫበጭ ማንን ይድላው ብላችሁ ነው?
"…በህወሓት ጥጋብ ትግሬንና የትግሬን ምድር በር ዘግቶ፣ መውጫ መግቢያ ከርችሞ፣ እግዚአብሔር ለኃጥአን በላከው መቅሰፍትና ቁጣ ንፁሐን ትግሬዎችን ጭምር እንደቀጣ ሁሉ በቀጣይ ተረኛዋ የኦሮሚያ ምድርም ያው የትግሬ ምድር ዕጣ ፈንታም ይደርሳታል። አዎ አዛኜን የሚሊዮን ኢትዮጵያውያን እንባ የፈሰሰባት ኦሮሚያ ዓይናችን እያየ፣ ጆሮአችን እየሰማ ትቀጣለች። ሺዎች በግፍ የታረዱባት ኦሮሚያ፣ ደማቸው እንደ ዥረት እንደወንዝ የፈሰሰባት ኦሮሚያ ትቀጣለች። ግድ ነው። ሰማይ ዝናብ ይከለክላል፣ ምድርም ፍሬ አትሰጥም። የኦሮሞ ግንዱ ይቆረጣል። ቅርንጫፉም ይረግፋል። ከብትም እህልም ያልቃል።
4.3K viewsedited 18:06