Get Mystery Box with random crypto!

ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekele3
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.50K
የሰርጥ መግለጫ

እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ዩቲቡ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 13

2023-03-24 20:16:03
"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ሰማዕትነት ለአምስት ኪሎው መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት እየቀረበ ነው። ቅር እንኳ ቢባል የሚቀር አይመስልም። ለዚህ ማሳያው ትናንት መጋቢት 14/2015 ዓም በአዲስ አበባ ከተማ ልዩ ስሙ ኃይሌ ጋርመንት በሚባለው አካባቢ ቀሲስ ዐባይ መለሰ በተባሉ አረጋዊ ካህን ላይ የተፈጸመው የግድያ ተግባር ነው።

"…ይህን ዘግናኝ ግፍ የዐይን እማኞችን ጠቅሶ የዘገበው ማኅበረ ቅዱሳን ቴሌቪዥን ሲሆን ሟች በሆርሲሳ ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን የታላቁ ዐብይ ጾምን ሥርዓተ ቅዳሴ ፈጽመው ወደ ቤታቸው በመሄድ ላይ ሳሉ መንግሥት ባለበት ሃገር በጠራራ ፀሐይ በቀን በድንጋይ ተወግረው መገደላቸውን ዘግቧል። ካህኑ በድንጋይ ተደብድበው ሲገደሉ የምስልና ቪዲዮ ማስረጃ ለመያዝ የሞከሩ ሰዎችን በአካባቢው የነበሩ የፀጥታ ኃይሎች መረጃ የያዙትን ሰዎች ሞባይል በመሰብሰብ መሰረዛቸውም ተዘግቧል። አሁን ካህኑ ሕይወታቸው ሲያልፍ ችግሩ ታወቀ እንጂ አስቀድሞ በአካባቢው አገልጋዮች ላይ ዛቻ እና ማስፈራሪያ ይደርስ እንደነበር መረጃ ሰጭዎች መናገራቸውንም የቴሌቭዥን ጣቢያው ዘገባ ያመለክታል።

"…ከሁለት ሳምንት በፊት ለግዳጅ ነው ተብለን ወልዲያ ስታድየም ገብተን ያለ ሥራ ቆመናልና መፍትሄ ይሰጠን በማለት በትናንትናው ዕለት በወልድያ ስታድየም የተከማቹ የከባድ መኪና ባለንብረትና ሹፌሮችና ረዳቶች ያቀረቡት ተማጽኖ ዛሬ ተሰምቶ ከ1ሺ በላይ መኪኖች ወደ ትግራይ እየተመሙ ሲሆን ገሚሶቹም የዐማራ ልዩ ኃይል ዩኒፎርንም የለበሱ ፖሊሶችን በመጫን ሕዝቡም እንዳያያቸው በዋናው አስፓልት መንገድ እያስወጡአቸው መሆኑ ተሰምቷል። የልዩ ኃይሉን ውጣ መባል ተከትሎ ቁጥሩ ቀላል የማይባል የልዩ ኃይል አባላትም ከአባልነት ወጥተው ጫካ መግባታቸውም እየተነገረ ነው። ያለ ሕዝብ ተሳትፎ ሰላም አይታሰብም።

"…እየሰማነ…!
3.8K views17:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-23 21:52:49
አሁናዊ መረጃ፦

መረጃ ፩

"…መዳረሻው የት እንደሆነ ለጊዜው ባይታወቅም ዛሬ መጋቢት 14/2015 ዓም ከትግራይ ክልል አቅጣጫ የተነሡና የመከላከያ ታርጋ በለጠፉ መኪኖች የተጫኑ ታንክን ጨምሮ እንደ BM የሉ ከባድ መሳሪያዎች በብዛት ተጭነው ወደ ወልድያ መስመር ሲጓጓዙ ውለዋል። ሕዝቡ ሁሉ እያየ የተደረገ ነው።

መረጃ ፪

"…አሁንም መነሻቸው ከወደ ትግራይ አቅጣጫ የሆኑ የዐማራ ልዩ ኃይልን የደንብ ልብስ የለበሱ ዛሬ ከሰዓት በኋላ ከቀኑ 10 ሰዓት ጀምሮ በራያ ቆቦ፣ በአራዱም እና በሮቢት አካባቢዎች ብዙ ቁጥር ያለው ሠራዊት  እንዲሰፍሩ ተደርጓል። የአካባቢው የብልጽግና ሹማምንት ስለጉዳዩ ምንም የምናወቀው ነገር የለም ማለታቸውም ተሰምቷል።

መረጃ ፫

"…እኚህ በምሥሉ ላይ የምታዩዋቸው ሼህ ሼህ መሀመድ ጠይብ ይባላሉ። ላለፉት 20 ዓመታት በላፍቶ ቢላል  ትልቁ መስጊድ ሲያሰግዱ የኖሩ ኢማም ናቸው። በዛሬው ዕለት በኖሩበት መስጊድ በግፈኞቹ እና በፅንፈኞቹ የዋሀብይ እስላሞች አማካኝነት ከመስጊድ አያሰግዱም  ተብለው በፆመኛ አንጆታቸው በዚህ ሁኔታ ፖሊስ ጣቢያ ግቢ ውስጥ ይገኛሉ እና ዘመዴ እባክህ ድምፅ ሁንላቸው ብሎ ወንድሜ አቡድልፈታህ አድርሶኛል። እኔም ይኸው አድርሻለሁ።

~ አምሹ…!
.
@Zemedkunbekele3
@Zemedkunbekele3
@Zemedkunbekele3
4.1K views18:52
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:48:07
"…ወይ ጣጣዬ መቼ ነው ደግሞ እንዲህ ያልኩት በማርያም…?

• የልጅትን ፈጠራ ግን አድንቄላታለሁ። … አስተያየቷ ራሱ በሳቅ አፍራሽ ነው። አሁን ስለ ኢህአዴግ ሊግ እንጂ ስለ ዊግ ምንአግብቶኝ ነው የምበጠረቀው?

"…አንዳንዴ እኮ ሲያመኝ ጤና የለኝም። ኧረ ተው ዘመዴ ተው አንዳንዴ ጮጋ በል…! ሃይ አቦ ምንድነው ሳ…?
1.8K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-21 11:48:07
መብረቅ እና ሚስማር ይቀራል…!

"…ባለፈው ሳምንት ብራዚል በክርስቶስ ላይ ተሳለቀች። ዲያብሎስን አንግሣ ክርስቶስን በአደባባይ ተቃወመች። ለሰይጣን ዙፋን ሠርታ፣ ክርስቶስን አስፋልት ለአስፋልት ጎተተች። ተሳቀ፣ ተጨፈረ፣ ማታ ግን ዝናብ ዘነበ። ጎርፍም ጎረፈ ምሷን ሰጣት። የእጇንም አገኘች።

"…ትናንት የወሐቢይ እስላሙ አቢይ አሕመድ። (በነገራችን ላይ አቢይ ጴንጤ የሚመስላቸው አሉ። አቢይ ጴንጤ አይደለም። አሜሪካና ምዕራባውያኑ በኢትዮጵያ መንበር ጴንጤ በዙፋኑ ላይ እንዲፀናላቸው ስለሚፈልጉ የእነሱን ስሜት ለማርካት ጴንጤ መስሎ መንበሩ ላይ የወጣ የወሐቢይ እስላም ነው። ሰው የሚያሳርደውም ለዚያ ነው።)

"…ይሄ አረመኔ ነው ትናንት በአዲስ አበባ የክርስቶስን መስቀል ዘቅዝቆ ፀረ ክርስቶስ መሆኑን ለወዳጆቹ በቅድስት ሃገር ላይ ሆኖ መልእክት ያስተላለፈው። ፓስተር ምህረት ደበበና ዳንኤል ክስረት የሚያዘጋጁለትን መደበር የተሰኘ መጽሐፍ ያስመረቀው የክርስቶስን መስቀል ዘቅዝቆ ነው። እናም ዛሬ ወፋፍራም በረዶ መዝነቡን ሰማን። ሰውየው ከቆየ ገና ሚስማር ነው የሚያስዘንብብን።

"…አቢይ አህመድ፣ ታከለ ኡማና ዮናታን አክሊሉ እስከአሁን መስቀለ ክርስቶን በኢትዮጵያ ምድር ዘቅዝቀው የሳጥናኤል መሆናቸውን አረጋግጠዋል። ይሄ ኮቴ መናና እግረ ደረቅ የሆነ ሰውዬ ከመጣ ጊዜ ጀምሮ በኢትዮጵያ ያልተፈጸመውን ንገሩኝ? ከይሲው ከመጣ ወዲህ ፅንስ በሚጥሚጣ ታርዶ ተበላ፣ የሰው ልጅ እንደ ሽንኩርት ተቀረደደ፣ እንደ ጫጩት ታረደ፣ ተጨፈጨፈ። ሃገሪቷ የደም ኩሬ ሆነች። አብያተ ክርስቲያናት ተቃጠሉ፣ ካህናት ታረዱ፣ ምእመናን ተጨፈጨፉ። በሬሳ ቀለደ። ሰይጣን ራሱ ቀናበት ተደመመበት። ድርቅ በድርቅ ሆንን የዐማራ ሳይቆጠር ትግሬ ብቻ ከሚልዮን በላይ በሰይፍም በራብም ተጨፈጨፈ።

• ሚስማር አለመዝነቡም ራርቶልን ነው።
1.9K views08:48
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-20 10:33:10
“…በአንድም ነገር እንኳ በተቃዋሚዎች አትደንግጡ፤ ይህም ለእነርሱ የጥፋት፥ ለእናንተ ግን የመዳን ምልክት ነው፥ ይህም ከእግዚአብሔር ነው፤” ፊል 1፥28

“…ተናጋሪ ሰው በምድር ውስጥ አይጸናም፤ ዓመፀኛን ሰው ክፋት ለጥፋት ይፈልገዋል።” መዝ 140፥11“…ዓመፀኝነት እንደ ምዋርተኛ ኃጢአት፥ እልከኝነትም ጣዖትንና ተራፊምን እንደ ማምለክ ነው፤ የእግዚአብሔርን ቃል ንቀሃልና እግዚአብሔር ንጉሥ እንዳትሆን ናቀህ…።” 1ኛ ሳሙ 15፥23

“…ልጆች ሆይ፥ መጨረሻው ሰዓት ነው፥ የክርስቶስም ተቃዋሚ ይመጣ ዘንድ እንደ ሰማችሁ አሁን እንኳ ብዙዎች የክርስቶስ ተቃዋሚዎች ተነሥተዋል፤ ስለዚህም መጨረሻው ሰዓት እንደ ሆነ እናውቃለን።” 1ኛ ዮሐ 2፥18

“…እግዚአብሔር ቀናተኛና ተበቃይ አምላክ ነው፤ እግዚአብሔር ተበቃይና መዓትን የተሞላ ነው፤ እግዚአብሔር ተቃዋሚዎቹን ይበቀላል፥ ለጠላቶቹም ቍጣውን ይጠብቃል።” ናሆ 1፥2
https://t.me/Zemedkunbekele3
https://t.me/Zemedkunbekele3
https://t.me/Zemedkunbekele3
861 views07:33
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-19 20:15:30
ዋጡት…!

"…ህወሓት አቢይን በሙሉ ድምፅ ነው የመረጠችው። አከተመ።

"…የወሎ ዐማሮቹ በሰይጣናዊም ይሁን በሳይንሳዊ ጥበብ የአረመኔውንና ኢትዮጵያን በአፍጢሟ ሊደፋት የነበረውን ዋነኛ የዘር ቦለጢቃ ወላጅ አባት የመለስ ዜናዊን ኔትወርክ አፅድተው ጨርሰው አሁን ትግራይን ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥረዋል።

"…አንተም አንቺም የፈለግከውን በል እነዚህ የወሎ ዐማሮች ዐማርነታቸው እንዳይጋለጥ እና ትግሬነታቸውን ለማረጋገጥ ሲሉ ከማይችሉት እና ከማያሸንፉት ከዐለቱ ዐማራ ጋር ዳግመኛ ጦርነት እንዳይገቡ እንጂ አያያዛቸውን ሳየው እንኳ ምርጥ ነው። ይኸው ገና ወደ ሥልጣን እንደመጡ 21 የትግራይ ድምፅ ቴሌቪዥኖች ላይ የሚሠሩ አክራሪና ጽንፈኛ ገዳይ የሆኑ የወያኔ ጋዜጠኛ መሳይ ጉጅሌዎችን አባረዋል። ኪድ ጥፋ ድራሽህ አባህ ይጥፋ ብለው ነው ያባረሩት።

"…የጌታቸው ረዳ እህት እኮ የዐማራ ፎሊስ ናት። ብቻ የዐማራ ጥበብ እኔ ግርም ነው የሚለኝ። ጉድ እኮ ነው።

391 views17:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-18 16:55:16
"ርዕሰ አንቀጽ"

"…በራሴው ስህተት ምክንያት በእንቅልፍ ልቤ የምስጋና መስጫ ሳጥኑን ቆልፌ ውዬ ደግሞ ከፍቼ ከዚያ ተመልሼ ተኝቼ አሁን ገና መነሣቴ ነው። ወይ መዘበራረቅ። ምንዓይነት በየዓይነት የሆነ አጀዛቢ ሃገር ነው ባካቹ…? ሃኣ…? ለማንኛውም አድናቂዬ፣ የቴሌቭዥንም የቴሌግራምም ተከታታዬ ወሎዬው አቶ ጌታቾ ራዳ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ ፕሬዘዳንት ሆኗል። ባለፉት 50 ዓመታት ውስጥ በደም ንፁሕ ዐማራ የሆነ የዐማራ ተወላጅ የትግራይ ብሬዘዳንት ሲሆን ይኼኛው የመጀመሪያው እንደሆነም ተነግሯል።

"…መለስ (ለገሰ) ዜናዊ በእናቱ ኤሪና በአባቱ ወገን የጎጃም ዐማራ፣ ሚስቱ የወልቃይት ዐማራ፣ አቶ ገብሩ አስራት የጎንደር ዐማራ፣ ጌታቸው አሰፋ፣ ሰዓረ እና ጄ ጻድቃን ዐማራ መሆናቸውም ይነገራል። በመጨረሻም የትግራይ ሕዝብ በወንድም የወሎ ዐማራ ይመራ ይተዳደር ዘንድ ግማሽ ወሎ ግማሽ ኤሪ ከሆነው ለጌቾ ታዛዥና ከጠሚው አማካሪ ዳንኤል ክብረት በተገኘ ምክር በወሎዬው አቢይ አሕመድና በወሎዬው ደመቀ መኮንን ውሳኔ ወሎዬው ጌታቸው ረዳ የትግራይን ቁልፍ ጨብጧል።

"…ሲጀመር ጌታቸው ረዳን ትግራይ የላከው ዐቢይ አህመድ ነው። ሁለቱም ኢትዮጵያን ያፈርሱ ዘንድ ከጨለማው ዓለም የተላኩ ልቡሰ ሥጋ አጋንንት ናቸው። እስከ ሲኦል ድረስ ሄደንም ቢሆን ኢትዮጵያን እናፈርሳታለን ያለው ጌቾ አሁን ሚልዮን የትግሬ ወጣቶችን በዐማራ ምድር የአፈር ማዳበሪያ ካስደረጋቸው በኋላ ሲኦል መሄድ ሳያስፈልገው ኢትዮጵያን ለማፍረስ አራት ኪሎ መጥቷል። ወለይ በደስታ መስከሩ ነው።

"…ወፎቼ በራያ በመከላከያ እና በፋኖ መካከል እየተደረገ ያለን የጦፈ ውዝግብ አድርሰውኛል። ዳንኤል ክብረት እና አቢይ አሕመድ ስለ እኔ የሚዶልቱት ዱለታ ደርሶኛል። ወፎቼ ለዐማራው ኃይል የሚጠቅም መረጃም ንገራቸው ብለው አድርሰውኛል።

•ቆይቼ እመለሳለሁ…!
1.4K views13:55
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-16 22:14:25
ሌላዋን ኮተት ስማልኝ…!

"… Dr. Emebet Higher Special Dental Clinic ዶር እመቤት ከፍተኛ የጥርስ ኪሊኒክ ባለቤት ናት። የበሰበሰ ጥርስ ስትነቅል የምትውል እሷም እንደዚያው የበሰበሰ ሃሳብ ይዛ የምትዞር ናት። ያረጀ የገማ የፈረስ ጭራ፣ የሞተች የህንድ ሴት ፀጉር አናቷ ላይ ከምራ በአደባባ እከኳን የምታክ እከካም ሴት እንደ ደኅና ሰው የሕዝብ ወኪል ነኝ ብላ ለዚያች ገልቱ ፀረ ኦርቶዶክስና ፀረ ዐማራ ሴትዮና ምክር ቤት ጥያቄ ታቀርባለች። መጀመሪያ ታጠቢ። ሃይ

•ሦስቱ በዓላት አለች መስቀል፣ ጥምቀትና ዓድዋን ማለቷ ነው። •ሁለቱን አለች ኢድና ረመዳንን መሰለኝ። ባይከበሩ አላለችም? የወከላት ሕዝብ ጠይቂልኝ ብሎ ነው መለቷ እኮ ነው በውስጠ ዝ። አዛኜን የሆነ ክትባትማ ጎድሏታል። ዐቢይ አሕመድ እንዴት እንዴት ያሉ ጀዝባዎችን ነው የሰበሰበብን በእመ አምላክ።

"…ቀጠለችና ጤፍ አለች። ጤፍ ለምንድነው የማይገባልን? ጎጃሜና ጎንደሬዎቹ እሺ አይግቡ ጤፉ ለምንድነው የማይገባልን? ለምን እንዲርበን ተፈለገ? አላለችም ሆዶ። ጎጃሜ ጠልተሽ የምን ጤፍ ነው ኪኒሽን ቃሚ። መራቱ…! ደግሞ እኮ አለች ጤፉ ለአዳነች አቤቤ የምገባ ማዕከል ነው የሚጠቅመው። አራዳዋ ሞኝሽን ብዪ።

"…ቀጠለችና ወደ ሽቀላዋ መጣች። ከሕዝቡ በምታጋብሰው ክሊኒኳ ውስጥ መድኃኒት መጥፋቱ አንገብግቧታል። ምክርቤት የገባችው እንግዲህ የግል ጥቅሟን ልታስከብር እንጂ የሕዝቡ የዳቦ፣ የፍትህ ጥያቄን ልታንፀባርቅ አይደለም ማለት ነው። የውጭ ምንዛሪ ካልተሠራ ከየት ይመጣል ኡሙዬ። ብልጽግናሽ ወሬ እንጂ ሥራ የት አባቱ ያውቅልሻልና ነው ዶላር፣ ዶላር የምትዪው?

• መቼም አሁን ከነገ ጀምሮ እዚቺ ጦር ፊት ጋር ሄዶ ጥርሱን የሚታከም ኢትዮጵያዊ ይኖራል ማለት ነው? ጉድ እኮ ነው።

• ጎጃሜ ግን ጤፉን ከምን አደረስከው…?
1.7K views19:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 18:34:58
"ርዕሰ አንቀጽ"

"…ወይኔ እኔ ዘመዴ የደጃች ውቤ የፒያሳውን አራዳ እሳት የላስኩ ውኃ ቀቅዬ የምበላ እልም ያልኩ ንቁ ነኝ ባዩን የሐረርጌ መራታ፣ የምሥራቁን ሰው አጅሪት አማሪካ እንዲህ ጅዝብ አድርጋ ቀንና ሌሊቱን ትደበላልቅብኝ በማርያም። ጉድ እኮ ነው።

"…ባለቤቴን እንኳ በእኔ ቤት መሸት ብሎላታል ብዬ መደወሌ እኮ ነው። ፍቅሬን መግለጼ፣ ኡኡቴ ወጉ አልቀረብኝም። እዚህ ፀሐይ እያየሁ እዚያ ቢመሽ ነው ብዬ በድቅድቅ ጨለማ እኩለ ሌሊት አልፎ ደውዬባት ጭልጥ እልም ካለ እንቅልፏ አናጥቤ ቀስቅሼአት እንኳን ልታናግረኝ እንድትነጫነጭብኝ አላደረግኳትም። ። የመድኃኔዓለም ያለህ። ምን ጉድ ነው?

"…በዚህ ዓይነት እስከዛሬ በአማሪካ የሚኖሩ ሰዎችን ሰዓታቸውን ባለማቅ ስንቱን ከእንቅልፉ አናጥቤ ጨጓራውን ልጬ ይሆን በማርያም። 12 ሰዓት ቀን፣ 12 ሰዓት ሌሊት የሌለው ሕዝብና ሀገር እኮ ምስኪን ነው። ከጀርመን ወደ አሜሪካ ስመጣ እኮ ከሕይወቴ ላይ 6 ሰዓት እየቀነስኩ፣ ከኢትዮጵያ ወደ ጀትመን ስሄድ ከህይወቴ ላይ 2 ሰዓት እየቀነስኩ እንደምኖር መች ገባኝ። ሙሉ ሕይወት ለመኖር ማን እንደ ኢትዮጵያ። ከ6 ሰዓት ሁለት ሰዓቱ ይሻለኛል።

"…የአሜሪካ እረፍቴን ጨርሻለሁ። የመኝታውን ማለት ነው። በቃ እርፍ አልኩ። ለሽ እንደ እከደከን ማንችሎት። ዳይ አሁን ወደ ሥራ፣ ወደ መጣሁበት ጉዳይ መግባት ነው። እንደ ኢትዮጵያ ማሰቡን ትቼ እንደ አማሪካኖቹ ላስብ። እንዲያ ካልሆነ መቅለጤ ነው።

"…ከአማሪካ መንግሥት ባለ ሥልጣናት ቢሮ ውይይቶች ጎን ለጎን በዋሽንግተን አካባቢ ሁለት፣ በሲያትል ከተማ ደግሞ አንድ ከህዝብ ጋር ነጭነጯን ፊትለፊት የሚያገናኘኝ ስብሰባ በመረጃ ቲቪ እና በኢትዮ ቤተሰብ አማካኝነት ተዘጋጅቷል። ቀናቶቹ በሁሉም ሚዲያዎች ይታወጃሉ። ተዘጋጅታችሁ ጠብቁኝ…!

• ወጥር ዘመዴ…!
1.2K views15:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-03-15 10:15:30 ህልሜን ላስቀድም…!

"…እንደ አሁኑ አሜሪካ መጥቼ ይመስለኛል። በዲሲ መንደሮቹ እየተዟዟርኩ በአንድ የዶሮ ማነቂያ ሰፈር በሚመስል መንደር ውስጥ እየሄድኩ ሳለሁ ይመስለኛል በሆነ ትንሽዬ መካከለኛ አዳራሽ ውስጥ አማርኛ የሚያወሩ ሰዎች ሰምቼ ጠጋ የምል ይመስለኛል። በሩ ዝግ ነው በቀዳዳ ግን አጮልቄ ሳይ ተሰብሳቢዎቹን አንዳንዶቹን በአካል ሌሎቹን በመልክ ብቻ የማውቃቸው ሰዎች ይመስለኛል። ከፊት ከመድረኩ ጫፍ ላይ አንድ እግሩ በተሰበረ የጅማ በርጩማ ላይ ተቀምጦ ከታች ከመድረኩ ስር ላተኮለኮሉት መግለጫም፣ ሥልጠናም መመሪያም የሚሰጥ ሰው የማይ ይመስለኛል። ሰውየው የሆነ ጊዜ ትግሬ ነበረ። ህወሓትም ሆኖ ያውቃል። ከሆነ ጊዜ በኋላ ደግሞ በቃ ብአዴን ሆኛለሁ ብሎ ዐማራም አግብቶ ብአዴን የሆነ ሰው ነው። ዛዲግ አብርሃ ይመስለኛል።

"…አንተ ኤርሚያስ ለገሰ ከነ ፀጋየ አራርሳ ጋር በጋራ ሆናችሁ አብይ በዐማራና በኤርትራ ላይ ሊከፍት ላሰበው ዘመቻ ትክክለኛነት በቅርቡ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ትጀምራላችሁ። ኤርሚያስ ከተቻለ ኢትዮ 360ን ሳታፈራርስ እንዳትለቅ። እናንተ ደግሞ ይላል ወደ እነ ፀጋዬ ዞሮ እናንተ ደግሞ ኤርሚያስን አጀግኑት፣ ከዐማሮችና ከኢትዮጵያኒስቶቹ ጋር መቆየቱ እንደማያዋጣውና በጊዜ ወደ ጎሬው ቢቀላቀል እያላችሁ መለፈፍ ጅምሩ የሚላቸው ይመስለኛል።

"…ዛዲግ አብረሃ ወደ ዮኒ ማኛ ዞር ይልና አንተ በቋሚነት ከስዩም ተሾመ ጋር ለመወጠር ተዘጋጅ። በተለይ በአገው እና በዐማራ በኩል ክፍተቱን ለመፍጠር ተንቀሳቀስ። ቅድስት ብርሃን ትቀላቀልሃለች። በዚህ ጉዳይ ትልቁ ሓላፊነት የወደቀው በአንተ ትከሻ ላይ ነው ይለው ይመስለኛል። የሆነ እንግሊዝኛና ኮስታሪካኛ የመሰለ መልስ ሲሰጠውም አያለሁ።

"…ዛዲግ ጋሽ ደርቤ ናትናኤል፣ ከፋሲል የኔዓለም እና ከሲሳይ አጌ ጋር ሆናችሁ አንዴ ከኤርትራ ሌላ ግዜ ደግሞ ከአብይ ጎን እየሆናችሁ ፒፕሉን የማወዛገቡን ሥራ ሥሩ። ሄኖክ ዘ ሐበሻ፣ አቤል የወይኗ ልጅ፣ አቤ ቶኪቻው እና ሌሎቻችሁ ደግሞ ይላል ሌሎቹ ባይታዩኝም (ወዳጆቼ ስለሆኑ አቤ ቶኪቻው እና ሔኒ ዘሀበሻን ሳይ ድንግጥ የምል ይመስለኛል) ሌሎቻችሁ በጥቃቅንና አነስተኛ ያደራጀናችሁ ዩቲዩበሮች፣ ፌስቡከሮችና ቲክቶከሮች በመሃል በመሃል ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ብቻ እየገባችሁ መረጃ ከማዛባት ውጭ ሚዛናዊ በመምሰል ሌላ ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪመጣላችሁ ድረስ በተለመደው መልኩ ቀጥሉ ይላቸዋል። እንደምታውቁት ስንዘናጋ መሳይ መኮንን ለሻአቢያ ፈርሞ አምልጦናል። ታዬ ቦጋለ ዓሣ ነው። ሱማሌው ነፍጠኛን አስንቋል። እነ ቶማስ እና ጌትነት አልማው አዋጭ አልሆኑም። እናም ባለው ነው የምንቀጥለው።

"…ሁሉም ትክዝ ብለዋል። የስዬ ትካዜ ግን ከሌላው የተለየ ነው። ስዬ በጥቁር ፌስታል የሽንት ጨርቅ፣ ዳይፐርና የተቀቀለ የጡጦ ጫፍ ይዟል። ድንገት እጁን ያወጣና "እኔ ከምር አሞኛል፣ አሞኛል አቡዬን አሞኛል፣ ትንሽ ልረፍበት ማለት ሲጀምር ዛዲግ አብርሃ ተቆጣ። ብሎ ነገር የለም አንተ ከዮኒ ማኛ ጋር እየተናበብክ አብረህ ትሠራታለህ። ትእዛዝ ነው። መመሪያ ነው። ይሄን ሲሰማ ስዩም ተሾመ በቁሙ ዝልፍልፍ ብሎ የምር ታሞ ሲወድቅ ብንን አልኩ።

•አታምርሩ ህልም ነው ደግሞ…!
2.0K views07:15
ክፈት / አስተያየት ይስጡ