Get Mystery Box with random crypto!

ህልሜን ላስቀድም…! '…እንደ አሁኑ አሜሪካ መጥቼ ይመስለኛል። በዲሲ መንደሮቹ እየተዟዟርኩ በአ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

ህልሜን ላስቀድም…!

"…እንደ አሁኑ አሜሪካ መጥቼ ይመስለኛል። በዲሲ መንደሮቹ እየተዟዟርኩ በአንድ የዶሮ ማነቂያ ሰፈር በሚመስል መንደር ውስጥ እየሄድኩ ሳለሁ ይመስለኛል በሆነ ትንሽዬ መካከለኛ አዳራሽ ውስጥ አማርኛ የሚያወሩ ሰዎች ሰምቼ ጠጋ የምል ይመስለኛል። በሩ ዝግ ነው በቀዳዳ ግን አጮልቄ ሳይ ተሰብሳቢዎቹን አንዳንዶቹን በአካል ሌሎቹን በመልክ ብቻ የማውቃቸው ሰዎች ይመስለኛል። ከፊት ከመድረኩ ጫፍ ላይ አንድ እግሩ በተሰበረ የጅማ በርጩማ ላይ ተቀምጦ ከታች ከመድረኩ ስር ላተኮለኮሉት መግለጫም፣ ሥልጠናም መመሪያም የሚሰጥ ሰው የማይ ይመስለኛል። ሰውየው የሆነ ጊዜ ትግሬ ነበረ። ህወሓትም ሆኖ ያውቃል። ከሆነ ጊዜ በኋላ ደግሞ በቃ ብአዴን ሆኛለሁ ብሎ ዐማራም አግብቶ ብአዴን የሆነ ሰው ነው። ዛዲግ አብርሃ ይመስለኛል።

"…አንተ ኤርሚያስ ለገሰ ከነ ፀጋየ አራርሳ ጋር በጋራ ሆናችሁ አብይ በዐማራና በኤርትራ ላይ ሊከፍት ላሰበው ዘመቻ ትክክለኛነት በቅርቡ የፕሮፓጋንዳ ሥራ ትጀምራላችሁ። ኤርሚያስ ከተቻለ ኢትዮ 360ን ሳታፈራርስ እንዳትለቅ። እናንተ ደግሞ ይላል ወደ እነ ፀጋዬ ዞሮ እናንተ ደግሞ ኤርሚያስን አጀግኑት፣ ከዐማሮችና ከኢትዮጵያኒስቶቹ ጋር መቆየቱ እንደማያዋጣውና በጊዜ ወደ ጎሬው ቢቀላቀል እያላችሁ መለፈፍ ጅምሩ የሚላቸው ይመስለኛል።

"…ዛዲግ አብረሃ ወደ ዮኒ ማኛ ዞር ይልና አንተ በቋሚነት ከስዩም ተሾመ ጋር ለመወጠር ተዘጋጅ። በተለይ በአገው እና በዐማራ በኩል ክፍተቱን ለመፍጠር ተንቀሳቀስ። ቅድስት ብርሃን ትቀላቀልሃለች። በዚህ ጉዳይ ትልቁ ሓላፊነት የወደቀው በአንተ ትከሻ ላይ ነው ይለው ይመስለኛል። የሆነ እንግሊዝኛና ኮስታሪካኛ የመሰለ መልስ ሲሰጠውም አያለሁ።

"…ዛዲግ ጋሽ ደርቤ ናትናኤል፣ ከፋሲል የኔዓለም እና ከሲሳይ አጌ ጋር ሆናችሁ አንዴ ከኤርትራ ሌላ ግዜ ደግሞ ከአብይ ጎን እየሆናችሁ ፒፕሉን የማወዛገቡን ሥራ ሥሩ። ሄኖክ ዘ ሐበሻ፣ አቤል የወይኗ ልጅ፣ አቤ ቶኪቻው እና ሌሎቻችሁ ደግሞ ይላል ሌሎቹ ባይታዩኝም (ወዳጆቼ ስለሆኑ አቤ ቶኪቻው እና ሔኒ ዘሀበሻን ሳይ ድንግጥ የምል ይመስለኛል) ሌሎቻችሁ በጥቃቅንና አነስተኛ ያደራጀናችሁ ዩቲዩበሮች፣ ፌስቡከሮችና ቲክቶከሮች በመሃል በመሃል ወሳኝ ጉዳዮች ላይ ብቻ እየገባችሁ መረጃ ከማዛባት ውጭ ሚዛናዊ በመምሰል ሌላ ተለዋጭ ትእዛዝ እስኪመጣላችሁ ድረስ በተለመደው መልኩ ቀጥሉ ይላቸዋል። እንደምታውቁት ስንዘናጋ መሳይ መኮንን ለሻአቢያ ፈርሞ አምልጦናል። ታዬ ቦጋለ ዓሣ ነው። ሱማሌው ነፍጠኛን አስንቋል። እነ ቶማስ እና ጌትነት አልማው አዋጭ አልሆኑም። እናም ባለው ነው የምንቀጥለው።

"…ሁሉም ትክዝ ብለዋል። የስዬ ትካዜ ግን ከሌላው የተለየ ነው። ስዬ በጥቁር ፌስታል የሽንት ጨርቅ፣ ዳይፐርና የተቀቀለ የጡጦ ጫፍ ይዟል። ድንገት እጁን ያወጣና "እኔ ከምር አሞኛል፣ አሞኛል አቡዬን አሞኛል፣ ትንሽ ልረፍበት ማለት ሲጀምር ዛዲግ አብርሃ ተቆጣ። ብሎ ነገር የለም አንተ ከዮኒ ማኛ ጋር እየተናበብክ አብረህ ትሠራታለህ። ትእዛዝ ነው። መመሪያ ነው። ይሄን ሲሰማ ስዩም ተሾመ በቁሙ ዝልፍልፍ ብሎ የምር ታሞ ሲወድቅ ብንን አልኩ።

•አታምርሩ ህልም ነው ደግሞ…!