Get Mystery Box with random crypto!

ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የቴሌግራም ቻናል አርማ zemedkunbekele3 — ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)
የሰርጥ አድራሻ: @zemedkunbekele3
ምድቦች: ሃይማኖት
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 25.50K
የሰርጥ መግለጫ

እንደ ፌስቡክ፣ እንደ ዩቲቡ ሁሉ በዚህ መንደርም ለቤተ ክርስቲያኔና ለኢትዮጵያ ሀገሬ የሚጠቅመውን ሁሉ አበረክ ዘንድ አብዝታችሁ ጸልዩልኝ።

Ratings & Reviews

3.00

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

0

1 stars

1


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 5

2023-05-16 13:28:38
የዛሬው "ርዕሰ አንቀጽም" እንደ ሰሞኑ የሚያነጋግር፣ የሚያወያይ ነው። ርዕሰ አንቀጼ ያው እንደምታውቁት ኬክ አይደለም። አይስክሬምም አይደለም። ኮሶ ነው። እንቆቆ፣ መተሬ፣ ሰናፍጭ የበዛበት፣ ለከሃዲና ለአጭበርባሪ፣ ለአፈ ጻድቅ በሙሉ የማይመች፣ የሚያንዘረዝር፣ የሚያስጮህ ነው። የሚያስጓራ አልኳችሁ።

"…ጦማሬን አንብበው ለሚጠቀሙበት ደግሞ ፈውስ ነው። እርጎ፣ መድኃኒት ነው። ባንዳ ሆኖ ለሚያነበኝ ሰው ሊደነግጥ፣ ሊጎረብጠው ይችላል። ለደንታው ነው። በተለይ ዐማራው ግን ከመግደርደር፣ ከማስመሰል፣ ከመሽለጥለጥ፣ ከመቅለስለስ የሚያወጣው፣ ወንድ ወንድ የሚያጫውተው ስለሆነ ይጠቀምበታል።

"…እና ዛሬም ስለ ኦሮሞ ሸኔ ትግልና ስለ ዐማራ ፋኖ ትግል ጽፌላችኋለሁ። የዐማራው ፋኖ ከወንድነት በቀር ከኦነግ ሸኔ መማር፣ መኮረጅ ያለበትን ምክር ለግሻለሁ። የትግሬ ነፃ አውጪና የኦሮሞ ነፃ አውጪዎችን የተቀበለ ጫካ የዐማራ ነጻ አውጪዎችን የማይቀበልበት ምክንያት አለ ወይ ብዬም እጠይቃለሁ። ስለ ዐማራ ሚሊሻ ቁመናም በስሱ ዳስሻለሁ።

"…መጀምርታ ነገር አንብቡት። ከዚያ ቆይቼ የአስተያየት መስጫ ሰንዱቁን እከፍትላችኋለሁ እናንተም የበሰለ አስተያየታችሁን ስጡበት። በረሃ ያሉትም እንደ ግብአት ወስደው እያነበቡ ስለሚወያዩበት እናንተም የተመጠነ፣ ገንቢ አስተያየትም ስጡበት። ተሳዳቢ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ኮማች ሳገኝ ወዲያው ሳይረጋጋ እንዲናፍቀኝ አድርጌ ስለምቀስፈው በእዚያ በኩል አትጨነቁ።

"…ርዕሰ አንቀጹን ለማንበብ ዝግጁ ናችሁ…? ቀውጡት። አስደንብሩት ይሄን ገገማ መቶ ኪሎ ፋራ ሰገጤ የትግሬና የኦሮሞ ነፃ አውጪ ነኝ ባይ ገንገበት።
3.9K views10:28
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:02:38 ከላይኛው የቀጠለ … ይህንን እንደ ግብዓት ይወስዱታል። እናም በመግደል የሚያተርፍ የመሰለው ብልፅግና በዐማራ ክልል የዐማራ ብልፅግና የፓርቲው መፍረስ እውነት እየሆነበት ስለመጣ አጥፍቼ ልጥፋ ከማለቱ በፊት ሕዝቡ በንቃት ራሱንና አካባቢውን ይጠብቅ። ምክንያቱም ይህ ወንጀል ከተፈጸመ የኦሮሞን ህዝብ በዐማራ ህዝብ ላይ ለማነሳሳት እንደ ምክንያት ይጠቀሙበታል። የራሳቸውን ሰው ካስገደሉ በራሳቸው ሰው እና በተለላኪው እንደሚሆን የተረጋገጠ ነው።

"…ሌላው በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ባሉ በሁሉም ወረዳወች ለብልፅግና ድጋፍ፣ ለግርማ የሺጥላን ሞት እና ፋኖን የሚያወግዝ ሰልፍ ተጠርቷል። ከሰልፉ የቀረ ማዳበሪያና ስኳር አያገኝም። ከዚያም አልፎ ይታሰራል በማለት የብልፅግና ፖሊሶች እና የቀበሌ ካድሬዎች በየቤቱ እየዞሩ እየመዘገቡ ነው። ጥሪው ቤተክርስቲያን ጭምር አልቀረም። ለአርሶ አደሩ የወልቃይት ጠገዴ ማንነት ልንጠይቅ ነው የምንሰለፈው ብለው ነው እየቀሰቀሱ ያሉት። በሰቆጣ የቀበሌ ሠራተኞች፣ በከሚሴ ኦሮሞዎቹ መውጣታቸው አላረካቸውም። በላሊበላ ብአዴን አስገድዶ የጠራውን ሰልፍ ወጣቱ በመበተኑም ብአዴን አብዷል። እና በጎንደር ሰልፉ ከተሳካ በጎጃም እና በጎንደር መካከል ክፍተት ለመፍጠር ይመቻል ብለው እየሠሩበት ነው።

"…ከዚህ በተጨማሪ ዐማራ መብራት፣ ውኃ፣ ስኳር፣ ዘይት፣ ኔትወርክ እንዲቆራረጥበት፣ እንዲማረር አስገዳጅ መመሪያ ወርዷል። ለምሳሌ ጠገዴ ቅራቅር ከተማ መብራት እና ውኃን ከሳምንት በላይ ሆን ብለው ዘግተው ከዛ ለህዝቡ የመብራት እና የውኃ ጥያቄ ከአቅማችን በላይ ስለሆነ ሰልፍ ውጡና ለዞን ጥያቄ እናቅርብ በማለት አጭበርብረው ሊያስወጡት እየሰበኩ እንዳሉ መረጃው ደርሶኛል። ሰልፉ ለረቡዕ ነው የተጠራው። በሌሎቹም የዐማራ ክልሎች ሰላማዊ የመብት ጥያቄ አስመስለው። የማዳበሪያ ስርጭትን፣ የመብራትና የውኃ፣ የመልካም አስተዳደር ጥያቄ ለመንግሥት እናቅርብ በመላት ሸውደው ፋኖን ሊያስወግዙ ባነር አሠርተው እየጠበቁ ነው። ከዚያ ያቺን ባነር ፎቶ አንሥተው እነ አሚኮ፣ ኢቲቪ፣ ፋናና ዋልታ ፕሮፓጋንዳ፣ የኦነግና የወያኔ አክቲቪስቶች እሾኮለሌ ሲሉ ሊከርሙ ነው።

"…ዐማራ ልባም ሕዝብ ነው። ኩሩ ሕዝብ ነው። ታሪከኛ ሕዝብ ነው። ለጋስ፣ ቸር፣ ደግ ሕዝብ ነው። ብልሃተኛ፣ ጠቢብ፣ አርቆ አስተዋይ፣ ታጋሽ ሕዝብ ነው። ጀግና የወንድነት ልክ፣ ሃገር ወዳድ፣ ለሃገሩ ሟች ሕዝብ ነው። እያወቀ የሚሞኝልህ፣ የሚታለልልህም ሕዝብ ነው። ለራበው በአፉ አጉራሽ፣ ለጠገበ በግንባሩ ቆጣሪ ነው። ፅዋው እስኪሞላ መሬት ይሆንብህና ፅዋው ሲሞላ ግን ሱናሚ ይሆንብሃል። አሁን ዐማራው ወለም ዘለም፣ ቅልስልስ ሳይል፣ ሳይግደረደርም ኮስተር ብሎ ለ4ኪሎ መታገል አለበት። ለባንክና ታንክ መታገል ነው። መፍትሔው እሱ ብቻ ነው።

"…ዐማራው ሊሄድበት ሊከተለው የሚገባው መንገድ አንድና አንድ ብቻ ነው። ይሄን መንገድ የሚያውቁት ገዢዎቹና ተላላኪው ብአዴን ብቻ ናቸው። ቀደም ሲል ወያኔና ኢህዴን ኋላ ብአዴን፣ አሁን ደግሞ መጀመሪያ ብአዴን፣ ቀጥሎ አዴፓ፣ አሁን ስሙን ቀይሮ የዐማራ ብልፅግና ተብዬ ገረድ ነው። ለዚህም ነው የዐማራን የመዳኛ መንገድ በቶሎ ፍርስርሱን የሚያወጡት። የዛሬው የዐማራ ትንታግ ግን ያንን የመዳኛ መንገድ ጀምሮታል። ጥርሱን ነክሶ፣ አንጀቱን ቋጥሮ፣ እንደ ትግሬና ኦሮሞ በኢትዮጵያ ይከበር ዘንድ የሚታረመውን እያረመ፣ እያስተካከለም መንገዱን ጀምሮታል።  እንኳን ጀመረው እንጂ የዚህ መንገድ መጨረሻ መዳረሻው ለዐማራም ለኢትዮጵያም መዳኛቸው ነው የሚሆነው። መንገዱም

፩. የአባታችሁ የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስ መንገድ
፪.የፊታውራሪ አስማረ ዳኘ መንገድ
፫.የዋዋ ጎቤ መልክ መንገድ
፬.የአርበኛ ዘመነ ካሴ መንገድ
፭.የሻለቃ አስቻለው ደሴ መንገድ
፮፦ የእነ ጄነራል አሳምነውና የእነ ዶ/ር አምባቸው መንገድ ናቸው። ሁለቱ የጊዜ እንጅ የሀሳብ ልዩነት አልነበራቸውም። ይሄ መንገድ ዐማራን ያድናል። አሁን ያለውን የዐማራ መፈናቀል ለማስቀረት፣ ቤት ፈረሳ ለማስቀረት ደግሞ ቤቱ የሚፈርስበት ሕዝብ አፍራሹን ሀይል ማፍረስ፣ መመከት፣ ማነከት ሲጀምር ነው። ይኸው ነው።

"…ለዐማራው ሚሊሻ ግን ደውላችሁም፣ በአካል ቀርባችሁም፣ በቄስም፣ በጓደኛም፣ በሼክም አስመክሩት። እረፍ በሉት። እምቢኝ ካለ ትበላለህ በሉት። ቲማቲም ኪሎው ጨመረ ብለህ የምታማርር አቢይ ገና አንተን ቲማቲም አድርጎ ይበላሃል በሉት። ሁሉም ቤት መከራው ይገባል። ሁሉም ያለቅሳል። የሳቁ፣ አቢይን ብለው የጨፈሩ ሁሉም ደም እንባ ያለቅሳሉ። የኅዘን ድንኳን ከየቤቱ አይነቀልም። ጠረጋው ከቤተ መቅደሱ ይጀምራል። የሚቀር የለም። አሳዳጆች ግን እናታቸው ሆድ ቢመለሱ እንኳ አያመልጡም። በቀለኛ ሕዝብ ተፈጥሯል።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!
5.4K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-15 17:02:38 "ርዕሰ አንቀጽ"

"…የመጨረሻው የሞት ሽረት የአርማጌዶኑ ጦርነት በዐማራ ክልልና በአዲስ አበባ ላይ እየመጣ ነው። አርማጌዶኑ ለሁሉም ክልሎች ይተርፋል። ዐማራን ለመበቀል ሲል በልቡ መርዙን ተሸክሞ ለኦሮሙማው የተገረደው ወያኔም አይቀርለትም። ከወዲሁ ራስን አዘጋጅቶ መጠበቁ ብልህነት ነው። አቢይ አሕመድ በጠበቀው መልኩ በገመተው መንገድ ዐማራው እንደ ትግሬ ሊንበረከክለት እና ሊገረድለት አለመቻሉ ማዲያት እንዲወርሰው፣ እንቅልፍ እንዲያጣ፣ ከንፈሩን ለምፅ እንዲመታው ሆኗል። ትግሬ ላይ ለነበረው ዘመቻ ድጋፍ የሰጡት ክልሎች በሙሉ ወገቤን ብለውታል፣ መከላከያውም አልታዘዝ በማለቱ ክፉኛ ነው እየተበሳጨ የሚገኘው። የዐማራው ሥነልቦና በቀላሉ የማይሰበር መሆኑም አበሳጭቶታል። እናም አለኝ ወደ ሚለው ወደ መጨረሻው የአርማጌዶኑን ካርታ ስቦ ተንደርድሮ ዕድሉን ሊሞክር አኮብኩቧል።

"…ሰሞኑን ከደብረ ዘይት ስብሰባ ቆይተው ወደ አዲስ አበባ በመመለስ ላይ የነበሩትን ጄነራል አለምሸት ደግፌና ጄነራል አበባው ታደሰ በተከፈተባቸው ድንገተኛ ተኩስ ለጊዜው ከሞት ቢተርፉም የሆነ ቀን ግን የአሳምነው ጽጌ እና የሰዓረ መኮንን ዕጣ ፈንታ እንደሚገጥማቸው ምልክት ሆኗል። ወያኔ ያደቀቃትን በአቢይ በኩል ለማድቀቅ ሸኔን አዲስ አበባ አፍንጫ ስር አስፍራለች። ኦነግ ሸኔም እዚያው ደብረ ዘይት ትናንት ማታ 5 ወታደሮችን ገድሎ እስረኞችን ማስፈታቱ ተነግሯል። ልብ በሉ አዲስ አበባ አፍንጫ ስር ነው ይሄ የሚሆነው።

"…ዐቢይ አሁን ሊያደርግ ያሰበው ወደ ዐማራ ክልል የሌላ ክልል ወታደር መላኩ ፋይዳ እንደሌለው ገብቶታል። ደቡቦች በገቡ ማግሥት ከዐማራው ተላምደው እዚህ ሕዝብ ላይማ አንተኩስም ማለታቸው፣ ኦሮሞዎቹ በእልህ ዘለው ገብተው ለወሬ ነጋሪ እንኳ ሳይተርፉ ጭዳ ሆነው ማለቃቸው፣ የዐማራ ተዋጊዎች ለጀትም፣ ለድሮንም የማይመች የውጊያ ስልት መከተላቸው ዐቢይን አበሳጭቶታል። እናም አሁን ሱዳንም እንደጠበቃት፣ ወያኔም አቅም እንደሌላት በመረዳቱ ሌላ የመጨረሻ ዕድል ለመጠቀም መክሮ፣ ዘክሮ ጨርሷል። ምክሩም እንዲህ ነው። ዐማራን በዐማራ ማስወጋት። ከዚያ በፊት ግን በራብ እና በክትባት መቅጣት።

"…ራቡ ዓምና ነው የጀመረው። በብአዴን በኩል እነ ግርማ የሺጥላ ዐማራ ስንዴ ብቻ እንዲተክል፣ ጤፍ የዘሩ፣ ድንች የዘሩ ተነቃቅሎ እንዲጣልባቸው፣ እንዲከስሩ፣ ምርቱም በፎርጅድ ብር ተገዝቶ ኦሮሚያ መጋዘን እንዲከማች፣ በዐማራ ክልል የእህል እጥረት እንዲፈጠር ማድረግ የሚል ነበር። የብአዴን ካድሬ እንደ ጠላት የዐማራ ገበሬን ደደብ ያልተማረ ርጥብ የዋህ የዐማራ ሚሊሻን ይዞ ሲያንገላታ ከረመ። በእኔና በመረጃ ቴሌቭዥን በጥቂት አክቲቪስቶች ጥረት ምርት ከዐማራ ክልል እንዳይወጣ ወተወትን፣ ከበቂ በላይ ተሳካልን። ይሄም መንግሥቱን አንጨርጭሮታል።

"…ዘንድሮ ግን ማዳበሪያ ዐማራው እንዳይደርሰው፣ የምርት ወቅቱ እንዲያልፍ በማድረግ የሚቀጥለው የምርት ዘመን እንዲያልፈውና በራብ ምክንያት አቅሙ እንዲሟጠጥ ለማድረግ እንዲሠራ አቢይ አሕመድ አዟል። የዐማራ ገበሬ ዘንድሮ ማዳበሪያ አያገኝም። ዐመፁ ይቀጥላል። ማዳበሪያ የሚያገኙት መሣሪያ ሲያወርዱ፣ ፋኖንና የዐማራ ልዩ ኃይል ሲዋጉ ብቻ እንደሆነም ወስኗል። አሁን ዐማራው በአውሬው አቢይ አጣብቂኝ ውስጥ ገብቷል። ገበሬው ሰልፍ ይወጣል፣ የብአዴን ወታደር መግደል ይጀምራል። ይሄ ለዐማራ ትግል አሸወይና በር ይከፍታል። ክትባቱ ያለ ከልካይ ገጠር ዐማራው ላይ በስፋት ቀጥሏል።

"…የመጨረሻው የአቢይ አሕመድ፣ የደመቀ መኮንን የዐማራው ማንበርከኪያ፣ ማስገበሪያ ያሉት ዐማራን በዐማራ ማስመታት ነው። አልማዝን ብረት አይቆርጠውም። መጋዝም አይቆርጠውም። አልማዝን የሚቆርጠው ራሱ አልማዝ ነው። ዐማራንም ሌላ አካል አያሸንፈውም። ዐማራን ሊያሸንፈው የሚችለው ራሱ ዐማራው ነው በሚል ስሌት በመከላከያ ለማጥቃት ሞክሮ ያልተሳካለትን ዘመቻ በእነ ዳንኤል ክብረት እና በእነ አቶ ታዬ አፅቀሥላሴ ምክር ዐማራን በዐማራ በሚል አዲስ እስትራቴጅ የዐማራ ሚኒሻዎችን እየላኩ ከፋኖ ጋር ለማጋጠም እየሞከሩ ነው። የዐማራ ነፃ አውጪዎችም በብዙ ትእግስት ገሚሱን እየመከሩ፣ ለገሚሱ ሽማግሌ እየላኩ እረፉ፣ ከእኛ ጋር አትዋጉም እያሏቸው ነው። እንቢ ካላችሁ ግን በትግሬዋ ወያኔ ያልሞትኩትን እንዴት በገዛ ወገኔ እሞታለሁ። ከዚህ በኋላ ግን አልሰማህም። እጠብሰዋለሁ እያሉ ነው። (ፋኖ የማረካቸውን ሚሊሻዎች በቪድዮ አቀርብላችኋለሁ"

"…ይሄ የዐማራ አክቲቪስት ስህተት ነው። የዐማራ አክቲቪስት ስንፍናና ቀሽምነት የፈጠረው ነው። የአማራ አክቲቪስት ከተማ ለከተማ ሲያውደለድል፣ ፌስቡክ፣ ዩቲዩብ እና ቲክቶክ ላይ ሲሞላፈጥ፣ ጋለሞታ ሲያሳድድ፣ ሱሳም ሆኖ ሲጀዝብ፣ በቁማር ተለክፎ፣ አቃጣሪ ሀሞተ ቢስ ሆኖ ሲንከላወስ፣ ገጠር ገብቶ በሚሊሻ ላይ ባለመሥራቱ በአቢይ ተቀደመ። በብአዴን ካድሬ ተነጠቀ። አሁንም አልረፈደም እያንዳንዳን ዐማራ የቻለ በአካል ወደ ገጠር ሄዶ፣ ያልቻለ በስልክ፣ በደብዳቤ ለዐማራ ሚሊሻ ያስረዳ። የብአዴን ሚኒሻዎች ስላልገባቸው አርፈው ቢቀመጡ መልካም እንደሆነ ይነገራቸው። ፋኖዎችም ሬሽን ካነሣቸው የሸኔን መንገድ ይከተሉ የሚሉ መተርጉማንም አሉ። በራብ ቀልድ የለም።

"…ለማንኛውም የፊታችን ረቡዕ አጅሬ ብልፅግና በባህርዳር ግዙፍ ስብሰባ ጠርቷል። የስብሰባው ዓላማም ከታች እስከ ላይ ያሉ የብአዴን አመራሮችን በግምገማ ሰበብ ማሳደድ እና ማሰር፣ እንዲሁም ለአብይ ታማኝ ናቸው የሚባሉትን በሃይማኖት ከእስላም እና ከጴንጤ ናቸው የሚባሉትን ወደ ላይ በማምጣት የዐማራ ብልፅግናን በታማኞች መተካት ነው። ለምሳሌ አሁን በግርማ የሺጥላ ምትክ የጅሌ ጥሙጋውን ኦሮሞ አቶ አህመዲን መሀመድን የዐማራ ክልል የብልፅግና ጽ/ቤት ሓላፊ አድርጎ ሾሟል። ነገ ኦነጉን ለገሰ ቱሉን የዐማራ ክልል ፕሬዘዳን ከማድረግ አይመለስም። ተበቃዩን በራስህ ላይ ይሾማል። ዐማራ ሰው እንደሌለው፣ ተቆርቋሪም እንደሌለው ተረድተዋል። ስለዚህ ጥሬ ካካውን በአናትህ ላይ ይዘፈልለዋል።

"…ሌላው በአሁኑ ስብሰባ እግረመንገዳቸውንም ልክ እንደ ግርማ የሺጥላ ከኦሮሚያ ብልፅግናም አንድ ዕጣ የወደቀበትን የኦሮሞ ባለ ሥልጣን ወይም አክቲቪስት በዐማራ ክልል ውስጥ በማስወገድ የመጨረሻውን ኦፕሬሽን ወደ ዐማራ ክልል ለማካሄድም እየተዘጋጁ እንደሆነ ነው ወፎቼ የሚነግሩኝ። ገዳዮቹ ደግሞ ራሳቸው ሁነው ፅንፈኛ ብለው በዐማራ ክልል ውስጥ እና ከክልሉ ውጭ ባሉ የአማራ ተወላጆች ላይ ሽብር በመፍጠር ወደ ክልሉ የመጨረሻውን አርማጌዶን ለማካሄድ ጦር ለማዝመት መወሰናቸው ነው። ይህንኑ ዕቅድ ያወጣውና እስከዛሬ አንዴም ሳይቀር በሁሉም የዐማራ ክልል የዐማራ ብልፅግና ስብሰባ ላይ እየተገኘ ካባ ሲሸለም የቆየው ኦቦ ሽመልስ አብዲሳ በአሁኑ ይለፈኝ አልሄድም እያለ ይገኛል። ስብሰባው የሚደረገው ለ10ቀን ነው። ይህ የወፎቼ መረጃ ነው። ብተሰሙ ስሙኝ። ቀድማችሁም አስቡበት። የብአዴን ሰዎች ሆይ ይህ ከሕዝብ ጋር የመቂሚያ የመጨረሻ ዕድላችሁ ነውና ወደ ቀልባችሁ ተመለሱ። በዕድላችሁም ተጠቀሙበት። ባትሰሙኝ ግን እኔ ከደሙ ንፁሕ ነኝ። እስከዛሬ እኔ ተናግሬ የቀረ የምትሉት ከሌለ ይሄንንም እመኑኝ። ስሙኝ። አስቀድማችሁ ሴራውን አፍርሱ።

"…የዐማራ ሕዝብም ይጠንቀቅ። ከአሁኑ በብአዴን አክቲቪስቶች በኩል ለስብሰባ የመጣው እንዳይወጣ የሚል ሥራ እያሠሩ ነው። በባህርዳር ስብሰባ ካልተሳካላቸው አዲስ አበባ ውስጥም ሊሞክሩት እንደሚችሉ የመረጃ ወፎቼ ይናገራሉ። ይህንን እንደ ግብዓት… ከታች ይቀጥላል።
5.5K views14:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-13 20:14:42
"…ትንሽ ጴንጤ ቢኖርበትም መንግሥቱ ከዐማራና ትግሬ የፀዳ የእስላም መንግሥት ነው፣ በአመራሩም ላይ የእስላም ስም ያላቸው፣ የጠመጠሙም ስለሚበዙ አገዛዙ የሚያጠፋውን ጥፋት ብንቃወም የመሪነት ዕድላችን ሊነጠቅ ይችላል። ስለዚህ የሆነው ሁሉ ቢሆንብን እንደ ዘመነ ወያኔ የአገዛዙን ገመና ከመግለጥ እንቆጠብ ብለው ተማምለው አገዛዙ በመቀመጫ በታፋቸው የሰቀሰቀባቸውን ሳንጃ ሳይነቅሉ ህመሙን ችለው ተቀምጠዋል።

"…ዛሬም አንድ ዘግናኝ ዜና ሰማሁና ዜናው እስላም ነክ ስለሆነ እስቲ ከእነ ሙጂብ አሚኖ፣ ከእነ አህመዲን ጀበል ገፅ ልየው፣ ልረዳው ብዬ በፔጃቸው ስቀላውጥ ዋልኩ። ወፍ የለም። ብዙ ክርስቲያኖች ግን በጉዳዩ አዝነው ሲላቀሱ እያየሁ ተደመምኩ። የእስላሞቹ ዝምታም እንደገረመኝ እስከአሁን አለሁ።

"…ሰበታ ከተማ ኬንተሪ ደረቶ በሚባል ቦታ አቶ መሀመድ አብደላ የሚባል ኢትዮጵያዊ የጉራጌ እስላም እንደሌላው ኢትዮጵያዊ ሁሉ ቤቱ በኦሮሞዎቹ ይፈርስበታል። ትላንት ከሰዓት በኋላ ታዲያ ከውድመት የተረፈውን ዕቃ ወደ ገጠር ይጭንና መሄጃ ሲያጣ አንድ ፊኒሽንጉ ያላለቀ የሪልስቴት ፎቅ ግራውንዱን የፎቆ ባለቤት "ቤት እስክታገኙ እረፉበት" ብሎ ያስጠጋዋል። ማታ ላይ ታዲያ የኦሮሞ ፖሊሶች ይመጡና እነ መሀመድ የተኙበትን የህንፃ በር መጀመሪያ ደበደቡ ከዚያ በርግደው ገቡ። ከዚያ ያፈረስነው ዕቃ እኮ የራሳችን ነው የት አባክ አደረስከው ብለው ባልና ሚስቱን በጥይት ደፏቸው። ጩኸቱን ሰምተው ከመጡት ጎረቤቶች መሀል ደግሞ አንዲት ሉባባ ብላቱ የተባለችን ሴት በጥይት ግንባሯን ብለው ከነ ጽንሷ ደፏት። የነፍሰጡሯ ባል ከተመታ በኋላ ቆስሎ በደመነፍስ ሮጦ አመለጠ። ሕዝቡም አስከሬን ተቀብሎ ጭጭ።

"…ኦሮሞዎቹ በወለጋ የወሎ፣ በለገጣፎ የጉራጌ እስላም አረዱ፣ መስጊድም አፈረሱ። እስላሙ ግን ዝም ጭጭ።

• እንኳንም ሞጣ አልሆነ።
1.7K views17:14
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 19:49:11
የዐማራ እናት…!

"…የዐማራ እናት ባለ ሥልጣን ልጇ ከሃዲ ነው። ሆዱ ከሞላ ደረቱ ከቀላ እናት ማለት ምኑም ናት። የዐማ ራ አንቂ፣ አክቲቪስት ሩጫው ከተማ ላይ ነው። ራሱም አልነቃ። ገና ቁማር ላይ ነው። ቤቲንግ፣ ጫት፣ ሲጋራ ሀሺሽ ላይ ነው። የዐማራ አክቲቪስት ሥልጣኔው አስቂኝ ነው።

"…የዐማራ አክቲቪስት ገጠር ገብቶ ሚልሻውን አላነቃም። በዚህ ምክንያት የዐማራ እናት እስከ አሁን መለስ ዜናዊ የሚገዛ ሁላ ነው የሚመስላት። መረጃ የላትም። ዐማራ በመንግሥት እንደሚገደል አታውቅም። የተፈናቀለ፣ የተሰደደ ዐማራ እንዳለ አታውቅም። መረጃ የላትም። ማን ይስጣት መረጃ። ልጇ ራሱ አልነቃ። በጎጥ ተወሽቆ ዳያስጶራ ሲቀፍል የሚውል የጎፈንድሚ ጥገኛ ነው።

"…የዐማራ አክቲቪስት ሞጣ ቀራንዮ ነው። ቡሃቃ አቦሬ አፍ። የዐማራ አክቲቪስት ስድአደግ ነው። ነቃ ያሉ፣ ቀለም የገባቸው፣ የተማሩ፣ የተመራመሩ ብቅ ሲሉ አሸማቀቃቂ ወደል መሃይም ይበዛዋል። የዐማራ አክቲቪስት ልጅ ተድላ መላኩን ትቶ ዮኒ ማኛ ቤት ስድብ ሲጠጣ፣ ሲለማመድ የሚውል ነው። ድንባዣም ቀረርቷም ነው። ጫካ ተገቡትን የማይረዳ፣ ህልም የሌለው። ራዕይ የሌለው። እውር ድንብር ያለ ይበዛዋል።

"…የዐማራ እናት ከዚህ የተነሣ መረጃው ስለሌላት በዓለም ላይ የጠፋ፣ የምን ይሁን የምን የማይታወቅ የተበላሸ፣ የተጣለ የኮሮና ክትባት ተብላ በማንም መንገደኛ የጠንቋይ ካዳሚ በመሰለች ሴት ምንነቱ የማይታወቅ መርፌ ትጠቀጠቃለች። የዐማራ እናት ታሳዝናለች። ገዳዩዋን መከላከያ አደግድጋ ትመግባለች።

"…የዐማራ እናት ቶማስ ጃጀውን፣ ጌትነት አልማውን፣ ጥላሁን አበጀን፣ መንግሥቱ ዘገየን ወልዳ ትሰቃያለች። ማርያምን የዐማራ እናት ታሳዝነኛለች።

"…ያጎደልኩት ካለ ጨምሩበት። ዐማሮች በደንብ ጭራ ታበቅሉ ዘንድ እኔ አሸበርቲው ዘመዴ ይሄን ጻፍኩላችሁ።

•ጧ በል…!
3.9K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-12 19:49:11
• አሁን ደግሞ በሕገ መንግሥቱ መሠረት ወደ ኦሮሞ ዐማራ ጭዌ እንምጣ። በቅድሚያ የኦሮሞ እናት።

የኦሮሞ እናት…!

"…በደንብ እንዲገፋላት፣ ጠላቴ የምትለውን ነፍጠኛ ወገኗን አናፍጦ ነፃ እንዲያወጣት፣ "ታጋይ ልጇ" በፀሐይ የነደደ አናቱን ቅቤ፣ ለአንጀቱ ደግሞ እርጎ እና ወተት እየሰጠች እንዲህ ትንከባከበዋለች።

"…የኦሮሞ አክቲቪስት እና ባለ ሥልጣን ለኦሮሞነቱ ከኢትዮጵያም ነፃ ለመውጣት እንዲህ ወጥሮ ይታገላል። አክቲቪስቱ አይገፋፋም፣ አይሰዳደብምም፣ ባሌ አሩሲ እያለም አይከፋፈልም። በስተመጨረሻ እንዲህ በግፍ የሚያርዱት እና የሚያፈሱት የዐማራ ደም ነቀርሳ ሆኖ ከትንሽ እስከ ትልቅ ከምድረ ገጽ እንደሚያጠፋቸው፣ የንፁሐን አምላክም በሃላል እንደሚበቀላቸው ቢያውቁም ለጊዜው ዐማራውን ለማጥፋት አይደለም ርስበእርሳቸው ከወያኔም ጋር እንኳ ቢሆን ስምም ሆነው ወጥረው ይሠራሉ። በሰሊጥ ብርም አይጣሉም።

"…ሌላው የኦሮሞ አክቲቪስትና አንቂዎች የሚያስደምሙት ባህርዳር እና ጎንደር፣ ፌስቡክ እና ዩቲዩብ ብቻ ላይ ተዘፍዝፈው አይውሉም። እታች ገጠር ድረስ ገብተው አረጎት የኦሮሞ እናቶችን ጭምር አሳምነው ከትግላቸው ጎን ያሰልፋሉ።

"…የዐማራውን ልቀጥል…? 
4.0K views16:49
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 21:06:52
ደግሜ መጣሁባት…!

"…ከሃዲ ይሁዳዋን፣ የዐማራን ትግል ቀርጥፋ በሊታዋን፣ ትግሉ ሳይጀመር ጨርሳ፣ የትግሉን ገንዘብ ከተማ ሆና ግጣ፣ ግጣ በልታ፣ ፋኖም፣ የዐማራ ልዩኃይልም ሳይቀር ለለውጥ መራር ትግል በጀመሩበት ወቅት ሁሉን ጥላ ኮማሪት፣ ጋለሞታ፣ የሴት ጭን ቸርቻሪ የሆነችውን፣ ከወያኔ ዘመን ይልቅ የዐማራ መጨፍጨፍ በበረታበት በዚህ ዘመን፣ ጎንደርን ትታ ሸሽታ አዲስ አበባ የብአዴን ባለሥልጣናትን የዝሙት ስሜት ለማብረድ አዲስ አበባ 22 የከተመችውን ይሁዲት ንግሥት ይርጋን ይሄን ጥያቄ ጠይቁልኝ። የአሁን ስልኳ ያላችሁ ጎደኞቼ ከላካችሁልኝ እኔው ራሴ ደውዬ እነግራት ነበር።

"…ወደ ጥያቄዬ ልግባ…። በታጋይነት፣ በጀግና ስም ቀፍለሽው፣ በብአዴኖች ምክር ከተከበረበት ከሀገረ አሜሪካ ድረስ የሞቀ ትዳሩን አፋተሽ፣ ልጆቹን በትነሽ፣ በድብቅ አግብተሽው ስታበቂ፣ 15 ቀን ሙሉ እስካይ ላይት ሆቴል ከሹገር ዳዲው ጋር ስትቀብጪ ከርመሽ፣ ቀጥለሽ የአማሪካ ፕሮሰስ መጀመሪያ፣ አንዳንድ ነገር ማስተካከያ ብለሽ 700 ሺ ብር ተቀብለሽው ስታበቂ ሹገር ዳዲው አሜሪካ ከገባ በኋላ እግርህን ብላ ያልሽውን... ልቀጥል ወይ…?

"…ብሏል አሸበርቲው ዘመዴ በሉልኝ…! ቀጥሎ ከናትናኤል መኮንን ጋር ያለውን እቀጥላለሁ። ናትናኤል መኮንን ጎንደርን አቅርቦ ለምን ወሎ፣ ጎጃም ሸዋን እንደሚሰድብም አሳያችኋለሁ።

"…ከነከስኩማ ሳላደማ መች በቀላሉ እፋታሃለሁ አባቴ…! ቅር የሚልህ ካለህ የመንጫጫት መብቱ የአንተው ነው? የዐማራን ትግል ቆርጥሞ በል ቡዶችንና ሾተላዮችን ከትግሉ ሜዳ ገገል እንዲሉ ማጽዳት፣ ማራገፍ ለነገ የማይተው የዛሬ ቀዳሚ አጀንዳ ነው መሆን ያለበት። በበረሃ የሚንከራተቱት እውነተኞቹ ፍዳቸውን እየበሉ የብአዴን ፋኖ በዳያስጶራ ዶላር ኢንቬስተር የሚሆንበት ምንም ምክንያት የለም።

• ክላልኝ ወዲያ…!
4.7K views18:06
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-11 13:10:16
"ርዕሰ አንቀጽ"

"…አቅም ሲኖርህ ትከበራለህ። ሀብት ሲኖርህ ወዳጀ ብዙ ትሆናለህ። ውበት ሲኖርሽ ውበት እንደ ተመልካቹ ነውና ውብ ከመስልሻቸው ሁሉ አድናቆት ይጎርፍልሻል። ፈላጊሽም ይበዛል። ጀግና ስትሆን ግን ትለያለህ። ለጀግና የማይንበረከክ፣ የማይገዛ፣ ጀግና የማያደንቅ፣ የማይደመምበት የለም። ወዳጄ ምንግዜም ጀግና ሁን። ከጀግና ጋር ዋል። የጀግና ወኔ ይጋባል እና ከጀግና እግር ስር አትጥፋ።

"…ህወሓት ከአቢይ አሕመድ ጋር እንደታረቀች መጀመሪያ በአማሪካ በኩል ያስደረገችው ነገር ቢኖር፣ የዐማራን ልዩ ኃይልና የዐማራን ፋኖ ትጥቅ አስፈታልኝ፣ ከወሎ እነ ምሬ ወዳጆን፣ ሙሉ ሸዋን፣ ከጎንደር "ሻለቃ መሳፍንትን" በተለይ መሳፍንትን ሞቶ ማየት ሁላ እንፈልጋለን ብላ ነበር እዬዬ ያለችበት። አዲስ አበባ እንዳትገባ ወጥሮ የያዛትን ሸዋንም እንዲሁ ለትበቀል ፈልጋ ነበር።

"…ኦሮሙማው አቢይ ሸዋን ለራሱ ለመጠቅለል ሲል፣ የጎንደሩን መሣፍንት ደግሞ ለወያኔ የበቀል ፍላጎት ሲል ገጠመ። በጎንደር መሣፍንት፣ በሸዋ የሸዋ ፋኖ አቢይ የላካቸውን የብራኑ ጁላን መከላከያ ተብዬ እንደአመጣጡ መክተው አንክተውም መለሱት። ለመሣፍንት የጎንደር ሕዝብ መንገድ ዘግቶ ድጋፍ ሰጠው። ለምሥራቅ ዐማራም የራያ ሕዝብ፣ ለሸዋም እንዲሁ ሕዝቡ ከነፃነት ታጋዩ ጎን ቆመ። መንግሥትም በሚፈልገው መጠን አልሳካ አለው። በመጨረሻም የሸዋውን አቆይቶ የጎንደሩን በድርድር ፈታው።

"…በድርድሩም መሠረት በሀርብ በር ኬላ የነበረው የቀሽሙ ብራኑ ጁላ የመከላከያ ሠራዊት በትናንትናው ዕለት ከበባውን ለቆ ፈርጥጦ ወጥቷል። እነ ሻለቃ መሳፍንት ተስፉም ወያኔን ጠብጥበው የታጠቁትን የቡድን መሳሪያቸውን እንደያዙ ተከበረው ይኖሩ ዘንድ ራሳቸውን አስከበሩ። ዓለም እንዲህ ናት። ዓለም የጉልበተኞች መሆኗን ዕወቅ።

• ድርጅቱ ዘመዴ ነኝ አሸበርቲው…!
5.0K views10:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 22:39:29
"የልደቷ ቀን ልደታችን ነው"
"ዮም ፍስሀ ኮነ በእንተ ልደታ ለማርያም"

"…ዛሬ አምላክን የወለደች በድንጋሌ ሥጋ በድንጋሌ ነፍስ የጸናች የእናታችን የእመቤታችን የቅድስት ድንግል ማርያም የልደቷ መታሰቢያ ዓመታዊ በዓል ነው። በጀርመን ባለሁበት ከተማ በአንድ ወዳጆቼ ቤት ሰብሰብ ብለን የእመቤታችንን የልደቷን በዓል እያከበርን ነው። ለዚያ ነው የጠፋሁት።

"…የቃልኪዳኗ እመቤት እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ለዛሬዋ በዓለ ልደትትሽ ያደረሰን ልጅሽ ጽንእት በድንግልና ሥርጉት በቅድስና እመቤታችን በዘመናችን ሁሉ ጸጋውን ክብሩን እንዳይነሳን ለምኝልን። አእምሮውን ጥበቡን በልቡናችን ሳይብን አሳድሪብን።

"…የእመቤታችንን ፍቅሯን በልቦናችን ጣዕሟን በአንደበታችን ያሳድርብን ምልጃና ጸሎቷ ረድኤት በረከቷ ከሁላችን ጋር ይሁን። የአሥራት ሃገሯን ኢትዮጵያን በምልጃዋ ትጠብቅልን።

• እንኳን አደረሳችሁ…!
5.6K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2023-05-09 22:39:29
እኔ ዘመዴ…

"…በሰው ሰውኛው በሥጋ ዓይን ሲታይ የአሁኑ የግንቦቱ ፍልሚያ ከባለፈው ፍልሚያ ትንሽ ከበድ የሚል ይመስላል። የእነሱ አሰልጣኝ ጥልሚያኮስ እንደተናገረው ከሆነ በአሁኑ ግጥሚያ ሞት ሽረት ነው የሚጠብቀን ሲል መሰማቱን ለቅዱሳን ቅርብ የሆነ ንፁህ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ሲናገሩ ተደምጧል።

"…ተጋጣሚ ቡድኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። በተለይ ከትግራይ አካባቢ የመጡት የተቃራኒ ቡድን አዲስ ፈራሚዎች ቡድናችን ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ ብለው በሰው ሰውኛው አሁንም የሚሰጉ አሉ። ከዐረቡ ዓለም ለተቃራኒው ቡድን የፈረሙ እንዳሉም ተሰምቷል። ምዕራባውያንም በበጀትም በጀትም ከተቃራኒው ቡድን ጎን በሙሉ ኃይላቸው እንደሚቆሙም ይጠበቃል።

"…ዳኛው እውነተኛ ዳኛ ስለሆነ በዳኛው በኩል ስጋት የለብንም። ቡድናችን የመሸነፍ ሪከርድ በሌለበት በአሸናፊው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚሰለጥን፣ የሚመራም ስለሆነ የመሸነፍ ስጋት፣ ከቅዱሳን ጸሎት በቀር ለጊዜው ከምድር እንደተቃራኒው ቡድን ድጋፍ የለንም።

"…በባለፈው ጫዋታ የተጎዱ፣ የደከሙ፣ የዛሉ የተሳሰሩ፣ ዱዳም ዲዳም የመሰሉ፣ የተሰበሩ ከዚያም አልፈው እስከሞት ድረስ የተፋለሙ ስለነበሩ በአሁኑ ጨዋታ እስከአሁን ባለው እንቅስቃሴ የቡድናችን ወቅታዊ አቋም ለሕዝብ ይፋ የሚሆን አይደለም። ተቃራኒው ቡድን ግብፅና ሱዳንን ይዞ እስከ ግንቦት ሲኖዶስ ድረስ ዐማራውን ማንበርከክ የሚል ዕቅድ ይዞ ቢንቀሳቀስም ሁለቱ አጋዦቹ በደረሰባቸው ድንገቴ የመብረቅ ጥቃት ስለተወገዱ እቅዱ ሊሳካለት አልቻለም።

"…ስለሆነም እኔ ዘመዴ አሁንም በቀደመ አቋሜ እንደጸናሁ ነኝ። ከመጪው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባና ከዐማራው የሞት ሽረት ትግል ላይ ዓይኔን ለአፍታም አላነሣም። ፍልሚያው ከባድ ነው። አሸናፊዎቹ ግን እኛው ነን። እኔ ግን ወይ ፍንክች፣ ወይ ንቅንቅ ብያለሁ። እናንተስ?
5.4K views19:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ