Get Mystery Box with random crypto!

እኔ ዘመዴ… '…በሰው ሰውኛው በሥጋ ዓይን ሲታይ የአሁኑ የግንቦቱ ፍልሚያ ከባለፈው ፍልሚያ ትን | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

እኔ ዘመዴ…

"…በሰው ሰውኛው በሥጋ ዓይን ሲታይ የአሁኑ የግንቦቱ ፍልሚያ ከባለፈው ፍልሚያ ትንሽ ከበድ የሚል ይመስላል። የእነሱ አሰልጣኝ ጥልሚያኮስ እንደተናገረው ከሆነ በአሁኑ ግጥሚያ ሞት ሽረት ነው የሚጠብቀን ሲል መሰማቱን ለቅዱሳን ቅርብ የሆነ ንፁህ ልብ ያላቸው ክርስቲያኖች ሲናገሩ ተደምጧል።

"…ተጋጣሚ ቡድኑ አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል። በተለይ ከትግራይ አካባቢ የመጡት የተቃራኒ ቡድን አዲስ ፈራሚዎች ቡድናችን ላይ ጫና ሊፈጥሩ ይችላሉ ብለው በሰው ሰውኛው አሁንም የሚሰጉ አሉ። ከዐረቡ ዓለም ለተቃራኒው ቡድን የፈረሙ እንዳሉም ተሰምቷል። ምዕራባውያንም በበጀትም በጀትም ከተቃራኒው ቡድን ጎን በሙሉ ኃይላቸው እንደሚቆሙም ይጠበቃል።

"…ዳኛው እውነተኛ ዳኛ ስለሆነ በዳኛው በኩል ስጋት የለብንም። ቡድናችን የመሸነፍ ሪከርድ በሌለበት በአሸናፊው እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ የሚሰለጥን፣ የሚመራም ስለሆነ የመሸነፍ ስጋት፣ ከቅዱሳን ጸሎት በቀር ለጊዜው ከምድር እንደተቃራኒው ቡድን ድጋፍ የለንም።

"…በባለፈው ጫዋታ የተጎዱ፣ የደከሙ፣ የዛሉ የተሳሰሩ፣ ዱዳም ዲዳም የመሰሉ፣ የተሰበሩ ከዚያም አልፈው እስከሞት ድረስ የተፋለሙ ስለነበሩ በአሁኑ ጨዋታ እስከአሁን ባለው እንቅስቃሴ የቡድናችን ወቅታዊ አቋም ለሕዝብ ይፋ የሚሆን አይደለም። ተቃራኒው ቡድን ግብፅና ሱዳንን ይዞ እስከ ግንቦት ሲኖዶስ ድረስ ዐማራውን ማንበርከክ የሚል ዕቅድ ይዞ ቢንቀሳቀስም ሁለቱ አጋዦቹ በደረሰባቸው ድንገቴ የመብረቅ ጥቃት ስለተወገዱ እቅዱ ሊሳካለት አልቻለም።

"…ስለሆነም እኔ ዘመዴ አሁንም በቀደመ አቋሜ እንደጸናሁ ነኝ። ከመጪው የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባና ከዐማራው የሞት ሽረት ትግል ላይ ዓይኔን ለአፍታም አላነሣም። ፍልሚያው ከባድ ነው። አሸናፊዎቹ ግን እኛው ነን። እኔ ግን ወይ ፍንክች፣ ወይ ንቅንቅ ብያለሁ። እናንተስ?