Get Mystery Box with random crypto!

'…እኔን የሚያስለቅሰኝ ይሄ ነው…! '…ከፊታችን በሚመጡት ሳምንታት 'ሕግ የማስከበር ዘመቻ' ብለ | ዘመድኩን በቀለ(ነጭነጯን)

"…እኔን የሚያስለቅሰኝ ይሄ ነው…!

"…ከፊታችን በሚመጡት ሳምንታት "ሕግ የማስከበር ዘመቻ" ብለው በዐማራ ክልል እንጀምረዋለን ብለው አፕሬሽን እንደ መግቢያ ያገለግላቸው ዘንድ አረመኔው አቢይ አሕመድ እና እነ ሽመልስ አብዲሳ፣ እነብርሃኑ ጁላ፣ አበባው ታደሰና በተመስገን ጥሩነህ የሚመራ የደኅንነት ኃይል በዛሬው ዕለት በዐማራ ሕዝብ ዘንድ የሚጠላውን ግርማ የሺጥላን በመግደል የጦስ ዶሮ ፍለጋውን ጀምሯል።

"…እነ አቢይ አሕመድ የግርማ የሺጥላ ብቻ በቂ ስላልሆነ ገና አጠገባቸው ካለው በሕዝብ ዘንድ የተጠላ ባርያ ገረዱ ጨምሮ ሌሎችንም የአማራ ባለሥልጣናት ለመብላት እቅዳቸውን አውጥተው መጨረሳቸው ነው የሚነገረው።

"…ወደ በቀል ሥራዋ የተመለሰችው ህወሓት ከኦነግ ኃይሎች ጋር በመሆን በቅርቡ በአዲስ አበባ የሚኖሩ ኤርትራውያንን፣ የኢሳት፣ የግንቦት ሰባት ሰዎችን ጨምሮ፣ የሃይማኖት አባቶችን፣ አክቲቪስቶችን፣ በተለይ ጁንታ ብሎ ባወጀው ጦርነት ላይ ህወሓትን በመቃወም በንቃት የተሳተፉ የዐማራና የትግሬ አክቲቪስቶችን ይበላቸዋል። ልክ ሰኔ 15 እነ ዶር አምባቸውን እና እነ አሳምነው ጽጌን ገድሎ የዐማራ ልዩ ኃይልን እንደጨፈጨፈው ሁሉ አሁንም የተወሰኑ የዐማራ ብአዴን ሰዎችን ደፍቶ ሲያበቃ ፋኖ ላይ ለመዝመት ዐማራን ለመጨፍጨፍ ይሞክራል።

"…የሰሜን ዕዝን ጨፈጨፉት አቢይ እና ወያኔ ናቸው። የቤንሻንጉል ጉምዝ ባለሥልጣናትን ወለጋ ላይ ጠብቆ የገደለው የኦሮሞ ኃይል ነው። ሙስጠፌን ለማስፈራራት ሲባል የፓርላማ አባሏን ሱማሌያዊት በአየር መንገዱ ውስጥ ያስረሸነው አቢይ ነው። ዛሬም ግርማን የገደለው አቢይ አሕመድ ራሱ ነው። ከዚያ ብርሃኑ ጁላ መጀመሪያ ሰሜን ሸዋ ላይ ይዘምታል። ሞክራት።

"…እኔ ግን የሚያስለቅሰኝ ይሄ ጭፍጨፋ ነው። አቢይ አህመድን ከነፓርቲው የሚበቀል ትውልድ እየመጣ ነው። አከተመ።