Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @yegna_psychology
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.64K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ አስተሳሰባችንን የሚያሳድጉ የሳይኮሎጂ እና የፓለቲካ ፅሁፎች ይቀርቡበታል።
የኛ ሳይኮሎጂ ይተነተናል እንዲሁም ታዋቂ የሥነ-ልቦና ሊሂቃን (theory) ይዳሰሳል።
🌟ማሳሰብያ ለውድ ተከተዮቻችን:➪አባላትን ለማብዛት በምናደርገው #የማስታወቂያ ልውውጦች እንዳትሰላቹብን ለማለት እንወዳለን።

[ ራሳችንን በመቀየር ድርሻችንን እንወጣ! ]

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 31

2022-09-10 20:10:07 የኛ ሳይኮሎጂ|| pinned a photo
17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 20:10:03
የሰላም ይሁንልን!

መልካም አዲስ ዓመት
Happy new year
2 15

ሰላም ለአለማችን
ሰላም ለሀገራችን!

JOIN US
@yegna_pshchology
@yegna_pshchology
@yegna_pshchology
1.8K viewsAbu Ki, 17:10
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-10 19:38:11 #አይዞን !


በዓለም ላይ ካሉ እድለቢስ ዜጎች መሀል እጣችን ወድቆ ዓመቱን ሙሉ የጅምላ እልቂት ፣ ጦርነት፣ ርሀብ፣ ስጋት ሰቆቃ እንስማና በዚህ ውስጥ እናልፍ ዘንድ ተገደናል! ቢሆንም አይዞን!

እጅግ በጣም ፈታኝ በሆነ የኑሮ ውድነት ውስጥ በማይገባን የኑሮ ደረጃ ፣የዓመታት ድካምና ልፋታችንን በማይመጥን አሳዛኝ ኑሮ እየኖርን ነው ቢሆንም አይዞን!

በስደት በመንከራተት ፈፅሞ ባላሰብነው መንገድ ያላሰብነው ቦታ ተገኝተን ይሆናል ...አይዞን!

እንደህዝብ በብዙ ፈተናና በብዙ አጣብቂኝ ውስጥ ያለንም ቢሆን የትኛውም ችግር ፀሐያችንን የጋረደ ደመና እንጂ ጨርሶ ተስፋ የሚያሳጣ የማይነጋ ፅልመት አይደለምና አይዞን!

አጉል ጎረመስኩ ባልኩባቸው አመታት አጓጉል ይመስሉኝ የነበሩ አስተሳሰቦች አሁን ላይ ስሜት ይሰጡኝ ጀምረዋል! በዋናነት "ጊዜ ይዞ የሚመጣው አይታወቅም" ይሉትን ብሂል ወደማመኑ ነኝ ...አይዞን "አዲስ ዓመት" እንዲሁ ልምድ አይደለም ... በሁላችን ልብ ውስጥ አዲስ ተስፋ የሚያስቀምጥ በእርግጥም አዲስ ጊዜ ነው! ተስፋ ሁሉም ነገር ነው ! በጊዜ ተስፋ እናድርግ ፣በተስፋም የጊዜን ተዓምር እንጠብቅ፤ ሁሉም ነገር አዲስ ይሆናል ... እንደሰው የምንከበር፣ እንደሰው የምንወደድ እና እንደሰው በሰው ክብር ልክ የምንኖርበት ጊዜ ይመጣል ! ተስፋችንን ብቻ አንጣል ...አይዞን !! እደግመዋለሁ አይዞን !

መልካም አዲስ ዓመት!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
1.8K viewsAbu Ki, 16:38
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-09 20:44:35 #ደሀ_ለመሆን_አትቸኩሉ!!!


በአውሮፖና አሜሪካ የሚኖሩ ቤተሰቦች ህይዎት ላይ የሚያተኩር ፅሁፍ በአጋጣሚ እያነበብኩ ነበር! በእነዚህ አገራት ሐብታምና ደህና ኑሮ ያላቸው ቤተሰቦች ውስጥ የሚያድጉ ህፃናት ከቤት ውጭ ተፈጥሯዊ የሆኑ ቦታዎች ላይ በመጫዎት ጊዚያቸውን ያሳልፋሉ! ውሃ መራጨት ፣ጭቃ ማቡካት ፣ ፖርኮች ውስጥ በመጨዋት ወዘተ .. የደሀ ቤተሰብ ልጆች ደግሞ በየቀኑ ያደርጓቸዋል ተብለው ከተጠቀሱ አምስት ድርጊቶች አንደኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠውና "አስከፊ" የተባለው
"ህፃናቱ ለረዢም ሰዓት ቴሌቪዢን ፣ ስልክና አይፓድ ላይ ያሳልፋሉ" የሚል ነው! ደሀ ለመሆን አንቸኩል ለማለት ያህል ነው

አሌክስ አብርሃም

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
2.4K viewsAbu Ki, 17:44
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 22:20:47 #ወሎ

የወሎ ሰው ጨዋታ አዋቂና ወግ አሳማሪ እንደሆነ ብዙ ጊዜ ሰምተናል፡፡ ለምስክር እንዲሆን ከሱፊስቶች ጋር የሚመሳሰል ጨዋታቸውን ከብዙ በጥቂቱ እነሆ፡፡ [በዚህ አጋጣሚ ይህንን ጨዋታ የነገሩኝ ወዳጆቼን አመሰግናለሁ]

የቡና ቁርስ

ወሎ ውስጥ ነን፡፡ አንድ እንግዳ ቡና እንዲጠጣ ከጎረቤቶቹ ጥሪ ይደርሰዋል፡፡ ቤታቸው ሄዶ ቁጭ እንዳለ ቡና ከመቅረቡ በፊት ምግብ እንዲቀምስ የእጅ ውኃ አመጡለት፡፡ እንግዳው በቅርብ ስለበላ ቡና ብቻ መጠጣት እንደሚፈልግ ይነግራቸዋል፡፡ ሰዎቹም ፤ እንግዳው ሊያፍር ይችላል በሚል እጁን እንዲታጠብ ገፋፉት፡፡ በቀላሉ እንደማይለቁት ሲያውቅ መብላቱን በመሀላ አስረግጦ ተናገረ፡፡ ይሄን ጊዜ ሴትዮዋ ሳቅ አሉና፤

"ተው?! ወጡን ቀምሶ ነበር ወላሂ ማለት" አሉ፡፡ እነሆ ጨዋታ . . .

[አቦል]

ደሴ ውስጥ የነበረ ምግብ ቤት አሉ፡፡ ሙስሊሙም ክርስቲያኑም በጋራ ይጠቀሙበታል፡፡ ከፈለጋችሁ ስሙን "ቄስ መሐመድ" ልትሉት ትችላላችሁ፡፡ የክርስቲያን እና የእስላም ምግቤት ይላል፡፡ አንድ ከመሀል አገር የሄደ ሰው በከተማው ሲዘዋወር ምግቤቱን ያየዋል፡፡ ከድሮ ጀምሮ ስለ ወሎ ሙስሊምና ክርስቲያን ተስማምቶ መኖር ይሰማ ነበር፡፡ እንዴት እንደሚኖሩ ለማየት ፍላጎት ስላደረበት ጎራ አለ፡፡

ፈራ ተባ እያለ ወደ ምግብ ቤቱ ገቤቶ የቤቱን አንድ ምግብ እንድያመጡለት አዞ ቁጭ አለ፡፡ ብዙ ሳይቆይ የታዘዘው ምግብ ቀረበ፡፡ ማዕዱን ሲያይ ከመደነቁ የተነሳ ከጉርሻው በፊት ሳቁ ቀደመ፡፡ የቀረበለት ሽሮ ነበር! የምግብ ቤቱ ስም ኀብረታቸውን ለማጠናከር ያደረጉት መላ እንጂ ሌላ እንዳልሆነ ገባው፡፡

[ቶና]

አንድ በመንደሩ የታወቀ ጀግና አንድ ቀን ምንሽሩን ታጥቆ ከቤት ወጣ፡፡ ሰው ሁሉ አገር አማን ብሎ በተቀመጠበት ወደ ሰማይ ካልተኮስኩ ብሎ ይገላገል ጀመር፡፡ አንድ ወዳጁ ደርሶ ምን ለማድረግ እንዳሰበ ይጠይቀዋል፡፡

"አላህን ልገለው ነው!" አለ ፈርጠም ብሎ፡፡ ሰውዬውም ቀበል አድርጎ፤

"ካገኘኸው ገላገልከን፡፡ ከሳትከው ግን አስጨረስከን" አለው፡፡

[በረካ]

ይህቺ ደግሞ ባቲ ውስጥ ያለች አነስተኛ ምግብ ቤት ነች፡፡ [ አሉ ናት ] የምግብ ዝርዝር መጻፊያ "ሜኑ" የላትም፡፡ በቤቱ የሚዘጋጀው ሁለት ዓይነት ምግብ ብቻ ስለሆነ የምግቡ ዓይነት እና ዋጋ ግድግዳው ላይ ነው የተጻፈው፡፡

1. ቀይ ወጥ

2 .ስፔሻል ቀይ ወጥ

አንድ እንግዳ ወደ ምግብ ቤቷ ገብቶ አስተናጋጁን ጠራና ምሣ ምን እንደደረሰ ይጠይቀዋል፡፡ አስተናጋጁም ወደ ግድግዳው እየጠቆመ፡፡ "ቀይ ወጥ፣ ስፔሻል ቀይ ወጥ" ይለዋል፡፡ እንግዳው ትንሽ ካሰላሰለ በኋላ ስፔሻሉ ቀርቶ ቀይ ወጥ ብቻ እንዲመጣለት አዘዘ፡፡

ምግቡ ቀርቦ መብላት ሲጀምር በቤት ውስጥ ያሉ ድመቶች፤ ሠላሳ ይሆናሉ፡፡ በሙሉ ወደ እሱ መጡ፡፡ አንዳንዶቹ የሚበላውን ለከፉበት፡፡ ከቁጥጥሩ ውጭ ሲሆን የሚበላውን ትቶ በዛውም ስፔሻል ቀይ ወጡን ለማየት ሌላ ምግብ አዘዘ፡፡

ትንሽ ቆይቶ አስተናጋጁ ያንኑ ቀይ ወጥ ከዱላ ጋር ይዞለት መጣ፡፡

[ምርቃት]

አንድ ደረሳ [ዲያቆን እንደማለት ነው] ብዙ ዓመት አብራው የኖረች ሚስቱ ትሞትበታለች፡፡ ጓደኞቹ የሐዘኑን ክብደት አይተው ሌላ እንዲያገባ አግባቡት፡፡ እርሱ ግን እንደ ሚስቴ የሚሆን አላገኝም በሚል እምቢ አለ፡፡

ከሁለት ዓመት ውትወታ በኋላ አንድ ጓደኛው አንዲት ልጅ ፈልጎ ይድረዋል፡፡ ዐዲስ ሕይወትም ይጀምራል፡፡ ለሱ ሁሉም ነገር እንግዳ ስለሆነበት በጣም ተገረመ፡፡ በተለይ አልጋ ላይ ያለው ቆይታ ከጠበቀው በላይ አስደሳች ሆኖ አገኘው፡፡

አንድ ቀን ይሄ ወዳጁ ትዳር እንዴት ነው ለማለት እሱ ዘንድ ይሄድና፤

"እህ ልጅት እንዴት ናት አንተው?" ብሎ ይጠይቀዋል፡፡

"አጃኢብ ነው ወላሂ፡፡ መቼም አላህ አያልቅበትም፤ ምነው ይቺንም በገደላት"

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.0K viewsAbu Ki, 19:20
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 10:02:40
• BETTING መበላት ላማረራችሁ ምርጥ ቻናል እንሆ

JOIN ብለዉ ይቀላቀሉን
47 views Call King , 07:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-08 09:45:33


✰• የማንን ዘፈን ትፈልጋላችሁ ALBUM ወይም Single እንግድያውስ ከታች የተዘረዘሩትን ተጫኑ ሌሎችም አሉ

✰• JOIN •✰
https://t.me/joinchat/AAAAAFZz4SvSUUi_7-bXwQ
106 views Call King , 06:45
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 21:27:59
ምን የቃና ፊልም ማየት ይፈልጋሉ ?
767 viewsAbu Ki, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-07 21:27:14 በእርግጥ ሞቲቤሽናል ንግግሮች ለጊዜው ጥሩ ናቸው። ስቴቨን ኮቮይ የስኬታማ ሰዎች ሰባቱ ልማዶች የሚል መጽሀፍ አለው። ሰውየው ከመግቢያው character ethic and personality ethic ዙሪያ የሚያጠነጥኑ ራስን የማማሻል መጽሃፍትን በሂስ ይተቻል። ለእነዚህ ጉድለቶች ስቴቨን ሰባቱ ልማዶች በእውቀት፣ በክሎት፣ እና በፍላጎት የተሳሰሩ መሆን አለባቸው የሚል ሃሳብ ያራምዳል።እኔም በእሱ ሃሳብ እስማማለሁ።
በቅርብ ጊዜ እኛ ሀገር ውስጥ የተጀመሩ ሞቲቬሽናል ንግግሮች ትንሽ ከእውነታው የራቁ ናቸው የሚል እምነት አለኝ። እውቀት፣ክህሎት፣ፍላጎት ሳታዳብር፣ እነዚህን ኤለመንቶች የሚደግፍ ማህበራዊ ተቋም መገንባት ሳትችል ላም አለይ በሠማይ ስብከት ይሆናል የሚል እምነት አለኝ። ይልቁንስ ሞቴቬሽናል ንግሮቻችን ያለውን ተጨባጭ እውነታ ነክተው ማለፍ ቢችሉ ብዙ መማር እንችል ነበር።

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
790 viewsAbu Ki, 18:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-06 20:23:01
በአለም ላይ የተከሰቱ እና አሁንም እየተከሰቱ ያሉ አስገራሚ አስደናቂ እንዲሁም አስቂኝ የሆኑ እውነታዎችን እና የሰዎች ገጠመኞችን በተጨማሪም ማታ ማታ ፈታኝ የጭንቅላት ጥያቄዎችን ድንቃድንቅ ሁነቶች ለማግኘት ከፈለጉ join በማለት ፈታ እያሉ ቁም ነገርን ይጨብጡ ከኛ ጋር

https://t.me/joinchat/5k6wNLiEV6k2YmY0
891 viewsAbu Ki, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ