2022-09-12 19:21:54
* * * Plagiarism (የሀሳብ ስርቆት ወይም "የመረጃ ምንተፋ" ) * * *
- የድንቁርና ጌቶች - የሚለው መፅሀፍ ከሚዳስሳቸው ነገሮች አንዱ በአአዩ ውስጥ ስለሚከናወን የሀሳብ ስርቆት ነው (ደራሲው Plagiarism ን የመረጃ ምንተፋ ይለዋል)። ደራሲው እንዲህ ይለናል:
~1/ ተማሪው የዶክትሬት መመረቂያ ወረቀቱን ለተቋቁሞ (ለ Defence) አድርሶ ፣ አስተካክል የተባለውን አስተካክሎ ለትምህርት ክፍሉ ይሰጣል። የት/ት ክፍሉ ሊቀመንበር ስላልነበረ ለአስተባባሪው (coordinator) ነበር ያስረከበው። አስተባባሪው ፅሁፉን አየት አየት ገልበጥ ገልበጥ ሲያደርግ ከራሱ ጥናት ጋር የሚመሳሰል እንዲያውም "የተቀዱ" ነገሮችን ያገኛል። ስለዚህ ጉዳዩን ወዲያውኑ ወደ ዲኑ ይወስደዋል።
ሁኔታው ከታወቀ በኋላ ነገሩ በሽምግልና ለመያዝ ይሞከራል። ብዙ ሳብ ጎተት ተደርጎ ነገሩ ሲከር ይመስላል ከተከሳሽ ወገን የሆኑ ሸምጋዮች የከሳሹን የመመረቂያ ፅሁፍ ፈትሸው "አንተም እኮ መመረቂያ ፅሁፍህን ስትሰራ ስራህ ላይ ይሄን ይሄን ቀድተሀል። እርሱ እንዲያውም ገና ስላላጠናቀቀ ቢያንስ አስተካክል ነው የሚባለው አንተ ግን አጠናቅቀህ በማእረጉ ከሁለት አመት በላይ ሰርተሀል ክሱ ባንተ ይብሳል" ቢሉት ሰውየው ደንግጦ ነገሩን ተወው
~2/ ይሄኛው የዚህ ፅሁፍ ፀሀፊ ያጋጠመኝ ሲሆን አአዩ በማስተርስ ደረጃ አንዱ ተማሪ የተመረቀበት የጥናት ወረቀት በተመሳሳይ አመት ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርስቲ ውስጥ በተመሳሳይ ርእስ ካላንዳችም የይዘት ለውጥ ርእሱን ብቻ በመከርከም ሌላው ተማሪ የተመረቀበት ነው። የሚገርመው አአዩ ውስጥ የተሰራው የማስተርስ ዲግሪ የጥናት ወረቀት ላይ አማካሪ የነበረው ዶክተር የሲቪል ሰርቪሱ ላይ External Examiner (የውጭ ገምጋሚ) ሁኖ መከሰቱ ነው።
Deepak Pental የተባለ የዴልሂ ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰር በአንድ biotechnology በሚመለከት ህትመቱ ላይ ፕሮፌሰር Pental የተባሉ የዘርፉ ምሁር ከፃፉት መፅሀፍ ላይ አንድ አንቀፅ ላይ ስማቸውን ሳይጠቅስ በእሱ የጥናት ፅሁፍ ላይ በቀጥታ በመጠቀሙ የህንድ ፍርድ ቤት ለእስራት የዳረገው ከመሆኑም በላይ ዩኒቨርስቲው የፕሮፌሰርነቱን ማእረጉን የቀማው መሆኑን የአንድ ሰሞን የህንድ ሚዲያዎች ትኩስ ዜና ነበር። ህንድን በመሰሉ ሀገሮች ላይ የሀሳብ ሌብነት እስከዚህ ይደርሳል።
O'Conor የተባለው ፀሀፊ The rise of the e-idiots በሚለው መጣጥፉ ከኢንተርኔት ላይ በማናቸውም መልኩ የተፃፉ/የተጫኑ የሰዉ ሀሳቦችን፣ ቃሎችን ፣ የስነ-ጥበብ ስራዎችን ወይም ሌሎች መሰል የሰው ስራዎችን የራሳቸው ኦርጂናል ስራ አድርገው የሚያቀርቡ ሰዎችን electronic idiot (e-idiot) ይላቸዋል።
በፌስ ቡክ ላይ የተፃፉ የሰው ስራዎችን (በተለይ ግጥሞችን) እና ፎቶዎችን ምንጭ ሳንጠቅስ በቀጥታ የራሳችን ገፅ ላይ በመለጠፍ የእኛ ራሳችን ሀሳቦችና ምስሎች(ስእሎች) አድርገን የምናቀርብ e-idiot ስንቶቻችን ነን???
ሌሎች መፅሀፍት ላይ የተፃፉ ፅሁፎችንና አባባሎችን ገልብጠን ካለምንም ማመንታት የራሳችን የአይምሮ ጭማቂ አድርገን በመፓሰት like የምንቆጥር e-idiot ስንቶቻችን ነን?
እናም የእኛ ሀገርን በተመለከተ William Inge - Originality is undetected plagiarism ያለው ከፍ ብሎ እየተውለበለበ ይመስላል።
JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
5.6K viewsAbu Ki, 16:21