Get Mystery Box with random crypto!

'ጨረቃ ድምቡልቃ' የአዲስ አበባ የቤት ችግር የኪራዩ ዋጋ ብቻ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ! ይህን | የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

"ጨረቃ ድምቡልቃ"


የአዲስ አበባ የቤት ችግር የኪራዩ ዋጋ ብቻ የሚመስላቸው ሰዎች አሉ! ይህን አንጀቴን የበላውን ነገር ከራሱ ከአባትየው እስክሰማ እኔም እንደዛ ነበር የሚመስለኝ! ባልና ሚስት ሁለት ልጆች አሏቸው ፣ የሰባትና የአምስት ዓመት ልጆች ! ግለሰብ ቤት ሰርቪስ ተከራይተው ይኖራሉ! ከጎናቸው ደግሞ አንድ ወንደላጤ ይኖራል፤ ፍቅረኛው ሁልጊዜ ቅዳሜ እየመጣች የምታድር ጎልማሳ! እና ቅዳሜ ገና ከምሽቱ አንድ ሰዓት ጀምሮ ... ሌሊቱን ሙሉ "አስቀያሚ" ድምፅ ያንን ከመጋረጃ የሳሳ ግድግዳ እያለፈ ይጎርፋል! ልጅቱ የመጨረሻ ዘግናኝ ዘግናኝ አይነት የማቃሰት ድምፅና የብልግና ቃላት ነው የምታወጣው ፤ፍቅር የሚሰሩ ሳይሆን ከነነፍሷ ቆዳዋን የሚገፈው እስኪመስል!

ታዲያ ባልና ሚስት ተከፋፍለው የልጆቻቸውን ጆሮ ከመያዝ ጀምሮ ቅዳሜ እየተሰደዱ የሚስትየዋ እህት ቤት እስከማደር ደረሱ! የእህት ባል ደግሞ ብዙም ደስተኛ አልነበረም! ቢጨንቃቸው ልጆቹ እስኪተኙ የህፃናት መዝሙር ድብልቅልቅ አድርገው መክፈት ጀመሩ ! ባለቤቶቹ ይሄንኛው አስቆጣቸው "ሰላም ነሳችሁን" ብለው አስጠነቀቋቸው !"ምንድነው በሌሊት ጨረቃ ድምቡልቃ " በመጨረሻ ባል ቀስ ብሎ ጎረቤቱን ስለሁኔታው አናገረው! ወደላጤው ግን ገገማ ነበር! "ጆሯችሁን ለጥፋችሁ የሰው ገመና መስማት አበሻ ሲባል ..." ምናምን ብሎ እንደተበደለ ሰው ዘራፍ አለ "ዲሞክራሲ መብቴ ነው በከፈልኩበት ቤት " አለ ! እስከ 2009 በዚሁ ችግር ውስጥ ይኖሩ እንደነበር አስታውሳለሁ ! ከዛ በኋላ እኔ ጋር ስለተራራቅን የሆነውን አላውቅም ! ጨረቃ ድምቡለቃን በሰማሁ ቁጥር ግን ሁልጊዜ አስታውሳቸዋለአሏቸው

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology