Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @yegna_psychology
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.64K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ አስተሳሰባችንን የሚያሳድጉ የሳይኮሎጂ እና የፓለቲካ ፅሁፎች ይቀርቡበታል።
የኛ ሳይኮሎጂ ይተነተናል እንዲሁም ታዋቂ የሥነ-ልቦና ሊሂቃን (theory) ይዳሰሳል።
🌟ማሳሰብያ ለውድ ተከተዮቻችን:➪አባላትን ለማብዛት በምናደርገው #የማስታወቂያ ልውውጦች እንዳትሰላቹብን ለማለት እንወዳለን።

[ ራሳችንን በመቀየር ድርሻችንን እንወጣ! ]

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 33

2022-09-03 21:35:43
#ውድቀትን

ርግማን ወይንም ስኬት ልታደርገው የምትችለው አንድም እንደ መሠናክል እንድም እንደ መረማመጃ ልትጠቀመው ትችላለህ። ለስኬት ወይም ለውድቀት የምትሰጠው ምላሽ በራስህ ብቸኛ ቁጥጥር ውስጥ ነው!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
1.7K viewsAbu Ki, edited  18:35
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-03 21:32:46 #ስንኞች

በብዙ ጭንቅና በብዙ መከራ አቁሜ ሲጃራ እጠነቀቅ ብየ፤ ለሳምባ ለልቤ በትምባሆ ምትክ ፤ንፉግ አየር ስቤ ከሱስ ጸዳሁ ልበል? መኖርን የሚያክል፤ ሱስ ተከናንቤ ከገነት ጋር ጠፍቶ ፤የጤና ትርጉሙ የተሻለው ሕመም፤ ጤንነት ነው ስሙ፡፡

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
1.7K viewsAbu Ki, edited  18:32
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-31 21:47:28 ግብህን ካላወክ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል ።

“ቁም ነገሩ ከየት እንደመጣህ አይደለም፣ ዋናው ቁም ነገር ወደ የት እንደምትሄድ ማወቅህ ነው” /Brian Tracy/
አንድ መንገደኛ ሰው ረጅምና አድካሚ የሆነ ጎዳናን ካለፈ በኋላ መንትያ መንገዶች ላይ ደረሰ፡፡ በዚያ የቆመን አንድ ሌላ የሀሃገሩን ሰው አየና፣
“ከእነዚህ ሁለት መንገዶች ትክክለኛው መንገድ የቱ ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡
ይህ የሃገሩ ሰው፣ “መሄድ የምትፈልገው ወደ የት ነው?” ብሎ ለመንገደኛው ጥያቄውን በጥያቄ መለሰለት፡፡
መንገደኛውም፣ “ወደ የት መሄድ እንደፈለኩ ገና አላወኩም” አለው፡፡ የቆመውም ሰው፣ “እንግዲያውስ፣ ሁለቱም ትክክለኛ መንገዶች ናቸው”
በማለት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ መለሰለት፡፡ መንገደኛው፣ “የምትሄድበትን ካላወቅህ የትኛውም መንገድ ይወስድሃል” የሚልን መልእክት ተቀብሎ፣
“መልእክቱ ገብቶኛል” በሚል ዝምታ ተዋጠ፡፡

ብዙዎቻችን በደመ-ነፍስ ነው የምንኖረው ፡፡ ከየት ተነስተን ወደ የት መሄድ እንዳለብን በቅጡ አናውቅም ፡፡ የጉዞአችንን ማረፊያ አለማወቅ በሕይወታችን ላይ ምን ያክል ተፅዕኖ እንዳለው አስበነው አናውቅም ፡፡
የግብ ጉዞ የምርጫ ጉዞ ነው - “የትኛውን ጎዳና ብመርጥ ወደ ዋናው የሕይወቴ አላማና ራእይ ያደርሰኛል” የሚል ምርጫ!
ግቡን በቅጡ ያላወቀ ሰው፦
የመጣውን ያስተናግዳል፣
ወደተከፈተለት ይገባል፣
ጊዜአዊ ደስታን በሰጠው ነገር ላይ ጊዜውን ያባክናል፡፡
ሕይወት በምርጫ የተሞላች ነች ፡፡ ጠዋት በስንት ሰአት ከመኝታዬ መነሳት እንዳለብኝ ከምወስነው ውሳኔ አንስቶ ማታ በስንት ሰአት ወደመኝታዬ መሄድ አለብኝ እስከሚለው ድረስ የምንመርጠው ምርጫና የምንወስነው ውሳኔ በአላማችን ላይ ጣልቃ ይገባል፡፡
“ብዙ ሰዎች የሚያስፈልጋቸው አሳ እንዳልሆነ ሳይገባቸው እድሜ ልካቸውን አሳ ሲያጠምዱ ይኖራሉ” /Henry David Thoreau/
“የምትፈልገውን ነገር ካልተከታተልከው አትጨብጠውም፡፡ ካልጠየክ መልሱ
ሁልጊዜ የእምቢታ ነው፡፡ ወደፊት ካልተራመድክ ዘወትር ራስህን ባለህበት ታገኘዋለህ” /Nora Roberts/
ግቡ አልደረስ ያለ ሲመስልህ መቀየር ያለብህ ግቡን አይደለም አካሄድህን እንጂ !!!


JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
1.1K viewsAbu Ki, 18:47
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-30 19:29:58 ጭንቀት የነገን ችግር ላይፈታ የዛሬን ደስታ ያደፈርሳል ።

ሁልጊዜ የተሻለና የተረጋጋ ሰላማችንን የምናገኘው ትናንት ከሰራነው ጥፋት ስንማርበት ዛሬ ለምናደርገው ተግባር ማስተዋል ሲኖረንና ነገን የተሻለ ብሩህ ህይወት
እንዲኖረን ዛሬ ላይ ጥሩ ስብዕና ተላብሰን ትልቅ የሆነ ተስፋን ሰንቀን ለአላማችን መኖር ስንጀምር ነው ።
ጭንቀት:- የራስን ኑሮ ትቶ በሰዎች ህይወት ውስጥ ጣልቃ ገብቶ መዘባረቅ፣ በራሳችን ጊዜ ወደራሳችን የምንስበው የህሊና በሽታ ነው ።
ሁልጊዜም በማይመለከትን ጉዳይ ጣልቃ ከመግባት እንቆጠብ ያኔ የጠፋውን ደስታችንን እንመልሳለን ።

ጭራሽ ከመውደቅ ተንጠልጥሎ መዳን ለህይወትህ ትልቁን ትምህርት ይሰጥሀል ምናልባት ተደናቅፈህ ብትወድቅ እንኳን እንዳትሰበር የምታርፍበትን አስበህ ተጓዝ።

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
77 viewsAbu Ki, 16:29
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:27:06 ...በሕይወት ትልቁ ቁም ነገር ትምህርት መውሰድ ነው፡፡
መቼም በስለንም አውቀንም አንጨርስም። ባወቅን ቊጥር ብዙ ቀዳሚ አላዋቂነታችን ይታወሰናል፡፡
ሁሌም እንማር፣
ሁሌም ለመለወጥ ዝግጁ እንኹን፣
ሁሌም ብሩሕ ተስፋ ይኑረን፡፡
ብልህ ሰው ዛሬ ላይ ፡
ዐዋቂ ነኝ፣
ትክክል ነኝ፣
እኔ ብቻ የሚል ሳይኾን ዛሬ ላይ የሕይወትን ትምህርት ከሕፃናት ሳይቀር ለመማር የተዘጋጀ ነው፡፡
ስለ ዛሬ ማንነቱ ሲያስብ ሙሉነት የሚሰማው ብቻ ሳይኾን፣ ነገ ላይ ለመሙላት የሚሰናዳ ነው፡፡
ብልህ ሰው ትናንትናንና ነገን አስታርቆ ዛሬን በእረፍት በርጋታና በደስታ የሚኖር ሲኾን፣ በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይኾን ሰውን ሁሉ ለመውደድ የሚጥር ነው፡፡

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
2.1K viewsAbu Ki, 17:27
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-27 20:02:26 #ፀሐይ_ላይ_ተሰጥተው_ከበረዶ_አገር_ስንዴ_ልመና!


ኢትዮጵያ ብቻዋን በመጠን ከዮክሬን ሁለት እጥፍ የምትበልጥ አገር ናት! በህዝብ ብዛትም እንደዛው! በወጣት ቁጥርማ ኢትዮጵያ አጠገብ አትደርስም! ዪክሬን ከዓመት እስከአመት በከፍተኛ በረዶ የቀላቀለ ቅዝቃዜና በከፍተኛ ሙቀት የምትጨነቅ አገር ስትሆን ኢትዮጵያ ከዓመት እስከዓመት ለኑሮም ይሁን ለእርሻ እጅግ ምቹ የአየር ንብረት አላት! ይሁንና ዩክሬን ከዓለማችን ከፍተኛ የእህልና ወዘተ ምርት አምራች አገራት አንዷ ዋናዋም ናት!

እንግዲህ ኢትዮጵያ ብቻ ሳትሆን ድፍን የአፍሪካ ባለስልጣን አንገቱን በከረቫት አንቆ እንደዝንጀሮ ፀሐይ ሲሞቅ ስለኒዩክሌርና ምናምን ሲዘባርቅ ይከርምና ከዚች ከአፍሪካ ጋር ስትነፃፀር በአጉሊ መነፅር እንኳ ከማትታይ አገር ስንዴና ዘይት ይማፀናል! ሰሞኑን ከሩሲያ ጋር በተፈጠረው ጦርነት አፍሪካ ከዳር እዳር በኑሮ ውድነት የሚናጥበት አንዱ ምክንያትም ይሄ ነው! ወጉን ሲያሳምሩት ታዲያ "ምዕራባዊያኑ ራሳችንን እንዳንችል የሸረቡብን ሴራ" ይሉሀል! ድህነት ምርጫ ነው! መሰልጠን ወይም ሞት ብሎ የተነሳ አገር በማንም ሴራ ተገቶ አያውቅም! የአስራ ሶስት ወር ፀሀይ ላይ ተሰጥተን በድህነት ሙቀጫ የምንወቀጥ ስጦች ነን?ምንድነን?


JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
2.1K viewsAbu Ki, edited  17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:21:32 ...አየህ_ልጄ!!!!

የፈለከውን ነገር ብታገኝም የሚቀር ነገር መኖሩ እሙን ነው።
ምስጢራትን ሁሉ ያወቅክ ቢመስልህም በዚህ አለም ከአንተ ህሊና የተደበቀ ብዙ ነገር ይኖራል። እናም የሚሻለው፦
የምትጠቀምበት ያክል ብቻ እወቅ፣
የሚያጠግብህን ያክል ብቻ ብላ፣
የሚያረካህን ያክል ብቻ ጠጣ።
ሁሉንም ነገር ማጣት ሰቀቀን ቢሆንም
ሁሉንም ነገር ማግኘትም እዳ ይሆናል፤
ምንም አለማወቅ ባዶነት ቢሆንም
ሁሉንም ማወቅ ደግሞ ሸክም ይሆናል።

#ሁሉ_በልክ_ሁሉ_በመጠን_ሲሆን_ይሆናል_መልካሙን_የሚሰጠን።

ሰናይ ምሽት ተመኘው!!!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.0K viewsAbu Ki, 17:21
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-25 20:02:08 በፍቅራችሁ ልጆቻችሁን አትግደሉ!


አሁን አሁን በየሚዲያው የሚቀርቡ ህፃናት ልጆች፣በአሳዛኝ ሁኔታ የህፃንነት ለዛና ነፃነታቸው ተሟጦ እንደፓሮት ወላጆቻቸው የጫኑባቸውን የትልቅ ሰው ዲያሎግ ደጋሚ አነብናቢ እየሆኑ ነው! መጀመሪያ ነገር የምትጭኑባቸው ነገር የልጆቹን አዕምሮ የሽምደዳ እስረኛ የሚያደርግ፣የማሰብ የመመራመር የመጠየቅ አቅማቸውን የሚያቀጭጭ ነው! ሲቀጥል የብዙዎቹ የምናያቸው ወላጆች አቅም ደካማ ፣በንባብም ይሁን በትምህርት ያልተቃኘ በመሆኑ ባለማወቅ ልጆቻቸው የእነሱን ድክመት እንዲወርሱ በፍቅር ስም ይፈርዱባቸዋል!

ዓለማዊ ነገርም ይሁን መንፈሳዊ ልጆቻችሁን ስታስተምሩ ውጤቱን እንዲሸመድዱ አታድርጓቸው! በአቅማቸው ልክ ምክንያቱንና ወደውጤቱ የሚወስደውን መንገድ ብቻ እንዲያውቁ አሳይዋቸው! ልጆቻችሁ እናተ የምታነበንቡትን ሳይገባቸው ስለደገሙ ለእናተ መዝናኛ ከመሆን ባለፈ ምንም እውቀት አይጨምሩም! እንደውም ለልጆቹ ውድቀት እየሰነቃችሁ ነው! ልጆች እንደእድሚያቸው ይኖሩ ይማሩና ይናገሩ ዘንድ ተዋቸው! እባካችሁ ፈጣሪ በአደራ የሰጣችሁን "ሰው" በወላጅነት አጉል መብት "ፓሮት" አታድርጓቸው! ልጆቻችሁን አትግደሉ!

አሌክስ አብርሃም

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
2.9K viewsAbu Ki, 17:02
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-24 20:23:56 ደራሲ
" ቀኑ ደመናማ ነበር "

ሀያሲ
" ፅልመት የታፈነ ብርሃን ነው እንዲል ብራዚላዊው ደራሲና ሃያሲ .....ደግሞም ራሽያዊው የፖስት ሞደርኒዝም ስነፅሁፍ አባት የሚሉት ...ደመና ወደሰማይ የዘነበ ዝናብ ነው እንዲል ...ፀሊም ቀናት እንደ ቁራ መርገምት በአክናፋቸው ህላዌን ከመገለጥ ሲሸብቡት ...ከምድር የተነነች እንባ በጠቆረ ቆፈን ህዋውን ታጠይመው ዘንድ በሰማየት አኮፈኮፈች ...ቀናችንን እንደኮሶ ተጣባችው ሊለን ሲሻ ደራሲው ቀኑ ደመናማ ነበር አለን ..."

ሰፊው ህዝብ ...
አርፌ ዩ ቲዮብ እና ቲክቶክ ላይ ብመሰጥስ!

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
3.3K viewsAbu Ki, 17:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-08-23 22:23:49 ከመሞታችሁ በፊት ማድረግ ያለባችሁ 20 ነገሮች


1.ትላንትናን እና ነገን እያሰባችሁ አትጨነቁ፡፡ ትናንት አልፏል ነገ አልመጣም ስለዚህ ዛሬን ቀን በሙላት ፣ በደስታ ፣በሰላም ለመኖር ጥረት አድርጉ፡፡

2.የበደሏችሁን ሰዎች ይቅርታ አድርጉላቸው ፡፡

3.ሁሉንም ሰው በእኩል ዓይን እዩ፡፡

4.ወደዚህ ምድር ያመጧችሁን እናትና አባታችሁን ውደዱ ፣ አክብሩ ፣ ታዘዙ ። *

5.የምትጠሉትን ስራ አትስሩ፡፡

6.የሕይወት ግባችሁን በመለየት በቅጡ ኑሩ፡፡

7.መስታወት ውስጥ ራሳችሁን ተመልክታችሁ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ ራሳችሁን ውደዱ፡፡
8.እዚህ ምድር የመጣችሁት በፈጣሪ አላማና እጅግ በጣም ጠቃሚ ሰዎች እንደሆናችሁ አስቡ ፡፡
9.ዘወትር መሄድ እፈልጋለሁ ወደምትሉት ስፍራ ሂዱ፡፡
10.በየቀኑ ለሌሎች ቢያንስ አንድ መልካም ነገር አድርጉ፡፡*
11.ለውጥን በፀጋ ለመቀበል ዝግጁ ሁኑ፡፡
12.ሁሉንም ዓይነት የሕይወት ትምህርት በፀጋ ተቀበሉ፡፡
13.የሕይወት ፈተና ውስጥ ያለውን መልካም አጋጣሚ አስተውሉ እንጂ ተስፋ አትቁረጡ፡፡
14.በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ውስጥ አዎንታዊ እና በጎ አሳቢ ሆናችሁ ዝለቁ፡፡
15.በሰው ሁሉ ለመወደድ ሳይሆን ሰውን ሁሉ ለመውደድ ጣሩ ፡፡*
16.ከቁሳ ቁስ ጋር ያላችሁን ትስስር አላሉ፡፡
17.ልባችሁን ተከተሉ፡፡
18.ሁልጊዜም ትልቅ በመሆን ሌሎችን አነቃቁ፡፡
29.ከሰዎች ሁሉ ጋር ተጫወቱ በሰላም በመግባባት ኑሩ 20.የተቸገሩትን ደግፉ ፡፡ ደግሞም ይህን ጽሑፍ #Share አርጉ ፡፡*

የዘለልኩት እስቲ እኔ ያልጠቀስኩት መደረግ ያለበት ነገር #Comment እንድታረጉልኝ ነው?
#Comment

JOIN US
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychology
@Yegna_Psychologyነ
3.6K viewsAbu Ki, 19:23
ክፈት / አስተያየት ይስጡ