Get Mystery Box with random crypto!

የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹

የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የቴሌግራም ቻናል አርማ yegna_psychology — የኛ ሳይኮሎጂ||🇪🇹
የሰርጥ አድራሻ: @yegna_psychology
ምድቦች: የልጅ እንክብካቤ
ቋንቋ: አማርኛ
ተመዝጋቢዎች: 14.64K
የሰርጥ መግለጫ

የተለያዩ አስተማሪ እና አዝናኝ አስተሳሰባችንን የሚያሳድጉ የሳይኮሎጂ እና የፓለቲካ ፅሁፎች ይቀርቡበታል።
የኛ ሳይኮሎጂ ይተነተናል እንዲሁም ታዋቂ የሥነ-ልቦና ሊሂቃን (theory) ይዳሰሳል።
🌟ማሳሰብያ ለውድ ተከተዮቻችን:➪አባላትን ለማብዛት በምናደርገው #የማስታወቂያ ልውውጦች እንዳትሰላቹብን ለማለት እንወዳለን።

[ ራሳችንን በመቀየር ድርሻችንን እንወጣ! ]

Ratings & Reviews

3.50

2 reviews

Reviews can be left only by registered users. All reviews are moderated by admins.

5 stars

1

4 stars

0

3 stars

0

2 stars

1

1 stars

0


የቅርብ ጊዜ መልዕክቶች 29

2022-10-03 21:51:43 የተሻለ ማንነት ለመገንባት፣
ህልምን ለመኖር፣
የመፍትሔ ሰው ለመሆን፣
አመርቂ ለውጥ ለማምጣት ከፈለጉ በእርግጥም የሚጠቅሞትን ቻናል እንጠቆሞ!
ይቀላቀሉ ያተርፉበታል!
643 views€£phâ (SânTos), 18:51
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 21:39:56 የስነ-ልቦና አቅሞን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦

እይታን የሚያሰፉ፤
ማንነትን የሚያንፁ፣
መልካምነትን የሚዘክሩ፣
ስብዕናን ከፍ የሚያደርጉ ውብ ምክረ ሀሳቦች በየእለቱ የሚነገርበት የምንጊዜም ግሩም ቻናል ተጋብዘዋል
597 viewsAbu Ki, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 21:39:15 የስነ-ልቦና አቅሞን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦

እይታን የሚያሰፉ፤
ማንነትን የሚያንፁ፣
መልካምነትን የሚዘክሩ፣
ስብዕናን ከፍ የሚያደርጉ ውብ ምክረ ሀሳቦች በየእለቱ የሚነገርበት የምንጊዜም ግሩም ቻናል ተጋብዘዋል
606 viewsAbu Ki, 18:39
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 20:36:58 ምዕራባውያን በነፃነት የመጠየቅ ጠንካራ ባህል አላቸው።
የሰዎችን ንግግር እንድያው በድፍን ቅል ይሆናል በሚል አይተረጒሙም። የተባለው ነገር ምን ማለት እንደ ሆነ ማብራሪያ ይጠይቃሉ ።

እኛ ኢትዮጵያውያን ግን በዝህ መጠን የመጠየቅ ባህሉ ያለን አይመስልም። እንዲያውም በአብዛኛው ለንግግሮቹ አሉታዊ ትርጓሜ በመስጠት ጉዳዩን በጥሬው (በራሳችን ግምት) የምንወስደው ይመስላል። አንድ ወዳጄ ይህ ችግር አትመርምር አትጠይቅ ከሚለው ጨቋኝ ባህላችን እንደሚነሳ ይናገራል፡፡ እንዲያውም አሁን የምናየው የአገሪቱ ዝርክርክ ፖለቲካ ከዝህ ፈላጭ ቁራጭ አኗኗር እንደሚመነጭ ያስረዳል፡፡

ምዕራባውያኑ ግን ጥያቄንና ምርምርን የእውነት ማንሸራሸሪያ ሠረገላ አድርገው ይጠቀሙበታል፡፡ ብንጠይቅ ብንመራመር ሰዎች ይቀየሙናል የሚል አስተሳሰብ የላቸውም። ለምን ተጠየቅሁ ለምን ተመረመርሁ በሚል አምባጓሮ የሚያነሳ ጦር የሚሰብቅ ፍልሚያ የሚገጥም ሰው ፈፅሞ አይገኝም። እኛ ግን ጥያቄ ያበዛብንን ሰው እንደጠረጠረ ምናልባትም ክብረ ነክ በሆነ መንገድ እንደሰደበን እናስባለን። በሃይማኖቱም አካባቢ ጥያቄን ማብዛት አምላክን እንደመፈታተን የአእምሮ ሰው እንደመሆን ነው የሚታየው። በትምህርት ቤትም በቤተ ክህነትም ነገሮችን በግልቡ እንድንቀበል ይጠበቃል። ከምርምር ይልቅ ግባታዊነትና ስሜታዊነት ክፉኛ የተጫነው መንፈሳዊነት እኛ ዘንድ በብዛት አለ። አእምሮን የሰጠን አምላክ አእምሮን አሽገን እንድናስቀምጠው እንደት ይፈልጋል? ዐዋቄ/አማሬ ኵሉ የሆነ ልዑል አምላክ ከትንሿ አእምሯችን የምትመነጨውን ትንኝ ጥያቄ የመመለስም ሆነ የማርካት ዐቅም ሊያጣ ወይም ለምን ተጠየቅሁ ብሎ ሊቁጣ እንደት ይችላል?

#ዶርክር_ተስፋዬ_ሮበሌ

መፀሀፍ (ሥነ አመክንዮ) ገፅ 40-43

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
902 viewsAbu Ki, edited  17:36
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 20:34:31 የአልበርት ካሙ ወርቃማ አባባሎች

አልበርት ካሙ(ከ1913-1960) በሥነ-ጽሑፍ የኖቤል ሽልማት የተበረከተለት ትውልደ አልጀሪያዊ ፈረንሳዊ ደራሲና ፀሐፌ ተውኔት ነው። እንደ የልቦለድ ደራሲ፥ ወግ ፀሐፊ፥ ጋዜጠኛና ፀሐፌ-ተዉኔት ስሙ የገነነ ነዉ። አልበርት ካሙ በሥራዎቹ የሕይወትን ወለፈንድ(the absurdity of life) በስፋት ዳሷል።

ምድር ላይ ብዙም ያልሰነበተው ካሙ ከሆነ ስፍራ በባቡር ለመሳፈር ሲጣደፍ ጓደኛዉ በመኪና ካላደረስኩህ ብሎት እያሽከረከር ሲጓዝ በሌላ መኪና ይገጫሉ። ጓደኛዉ ሲተርፍ፥ ካሙ ግን በአደጋው ይሞታል። ልክ እንደ ፅሁፎቹ አሟሟቱም ፍልስፍናዉን -የሕይወት ወለፈንድን- ያደምቃል ይላሉ ብዙዎች ከአባባሎቹ ለዛሬ እንቀንጭብ:-

1.በዚህ ሁሉ መኃል መረዳት የቻልኩት በተሸፈነ ድቅድቅ ክረምት ውስጥም የተሸሸገ በጋ በውስጤ ተዳፍኖ መኖሩንና ማግኘቴን ነው::

2.እስከ ዕንባህ የመጨረሻ ጠብታ ጥረስ ኑር፤

3. ደስተኛ ለመሆን ስለሌሎች ከልክ በላይ መጨነቅ የለብንም።

4.በሁሉም ውብ ልብ ውስጥ አንዳንዴ ኢ-ሰብአዊ የመሆን ነገር አለ።

5.ሰዎች ያለቅሳሉ ምክንያቱም ይች ዓለም ፍትሐዊ አይደለችምና

6.እኔ ያለሁት ስላመጽኩ ነው።

7.ነጻነት የተሻለ የመሆን ዕድል እንጂ ሌላ አይደለም።

8. ልቦ-ለድ በምስል የተገለጸ ፍልስፍና እንጂ ሌላ ዐይደለም

9. በዓለም ላይ ያለው ክፋት ሁል ጊዜ ከድንቁርና የሚመጣ ነው፣ መልካም ህሳቤም ከሌለው የመጥፎ ስሜት ያህል ይጎዳል።

10. የሕይወት ትርጉም ምን መሰለህ(ለሽ) 'ራስህን ከማጥፋት የሚከለክልህ የምታደርገው ማንኛውም ነገር እሱ የሕይወት ትርጉም ነው።

11. በየቀኑ የምትወስነው በጣም አስፈላጊው ውሳኔ 'ራስህን ላለመግደል መወሰን ነው።

12. ሕይወት የሁሉም ምርጫዎችዎ ድምር ውጤት ነው፣ ታዲያ ዛሬ ምን እያደረክ ነው?

13. ደስታና ወለፈን ሁለት የተለያዩ የአንድ ምድር ልጆች ናቸው፣ አይነጣጠሉም።

14. ራሴን ላጠፋ ወይንስ ቡና ልጠጣ? በመጨረሻ አንድ ሰው 'ራሱን ከማጥፋት ከሚያስፈልገው ድፍረት ይልቅ ለመኖር የበለጠ ድፍረት ያስፈልገዋል።

15. ተስፋ 'ኮ የለም እንፈጥረዋለን 'ጂ

16. የወለፈንድ(absurd) ጽንሰ-ሐሳብ አስፈላጊና የመጀመሪያው እውነት ነው።

17. እኔ የምወደው ሥዕሎችህን ሳይሆን ሥዕልህን ነው።


ሳሙኤል በለጠ ባማ ( በኔ የተመረጡ እና የተተረጎሙ )

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
879 viewsAbu Ki, 17:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 18:08:16 ለቃል አጠቃቀሜ ይቅርታና አንዳንድ "ምሁር" መላጣው ላይ ላብ ችፍ እስከሚል ስልጣን ላይ ላሉ ሰዎች ሲያሽቃብጥ ፀጉሩ ራሱ ተፀይፎት የሸሸው ነው የሚመስለኝ!

ማሽቃበጥ ስል ምን ትዝ አለኝ?ተማሪዎች ሆነን በረከት ስምዖን ወደከተማችን መጥቶ ነበር ! እና ንግግር እያደረገ በመሀል አንዴ አሳለ አንዴኮነው " ኡሁ " በቃ! ከዛ ወደንግግሩ ተመልሷል! አንድ ሽቁጥቁጥ የሚያደርገው የከተማችን ባለስልጣን እንዳለ የታሸገውን ሀይላንድ ውሃ ታቅፎ ወደመድረኩ በረረ ...ቦርጩ በምን ቀለለው! በረከት በእጁ ውሃ እንደማይፈልግ ምልክት ቢያሳየው ..."አመሠግናለሁ ደህና ነኝ" ቢል ሊሰማው ነው? መላጣው ላይ ላቡ እየተንጨፈጨፈ ተንበርክኮ ላስቲኩን በጥርሱ ሁሉ ቀዳዶ አንዱን ካወጣ በኋላ ግድ ካልጠጣህ ብሮ በሁለት እጁ ውሃውን ይዞ ጎንበስ ቀና ! የከተማው ህዝብኮ ስንት አመት ውሃ ሲለምን ስንዝር ተራምዶ አያውቅም!

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
1.3K viewsAbu Ki, 15:08
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-02 18:07:29 የአርሶ አደር ጎንጤ ነገር ሁኗል ኑሯችን!


አርሶ አደሮች በሚሸለሙበት ዘመን እንዲህ ሆነ!(እውነተኛ ገጠመኝ ነው) ከየወረዳው በካድሬዎች የተመረጡ አርሶ አደሮች አንድ አይነት ቲሸርት ለብሰው አዳራሹን ሞልተውታል! ሚንስትሮችና ሌሎች ባለስልጣናትም ነበሩ! አርሶ አደሮቹ ስማቸው እየተጠራ ያስመዘገቡት ካፒታል እየተጠቀሰ የምስክር ወረቀት ይሰጣሉ! መድረክ አስተዋዋቂው ቀጥሎ ስለሚሸለመው አርሶ አደር ተፅፎ የተሰጠውን ሞቅ አድርጎ ያነባል!

"ቀጥሎ የምጠራው ታታሪ .. በመስኖ ያመረተውን ቲማቲም እና ሽንኩርት በመሸጥ ሁለት አይሱዚ መኪና የገዛ ጀግና ነው ! ምንትስ ከተማ መጋዘን ገንብቷል፣ በባንክ ከሁለት ሚሊየን ብር በላይ ቆጥቧል! ከዚህ ባለፈ ለሚስቱ ሱቅ የከፈተ ጀግና አርሶ አደር ነው ....አርሶ አደር ጎን.....ጤ ቢሻው ወደመድረክ" ....ቿ ቿ ቿ ቿ ማንም አልተነሳም! አርሶ አደር ጎንጤ እባክህ ወደመድረክ ...አለ ደግሞ

ከጎንጤ መንደር የመጡ ሌሎች አርሶ አደሮች ጮክ ብለው
"ጎንጤ አልመጣም ! ወረቀቱን ተቀበሉሉኝ ብሎ እርዳታ ሊቀበል ወረዳ ጥህፈት ቤት ሄዷል!

አሌክስ አብርሃም

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
1.4K viewsAbu Ki, 15:07
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-10-01 19:16:13 በመብልና በመጠጥ፤ በፊትና በቁስ ደስታህን የሚተምን ሰው ያልበሰለ ሰው ነው!
(እ.ብ.ይ.)

ውስጡን የሚያውቅ፣ ልቦናውን የሚረዳ፣ የነፍሱን ጩኸት የሚሰማ፣ መንፈሱን የሚንከባከብ፣ ከህሊናው ጋር የሚስማማ ሰው ደስታው በመጠጥ እንደሚገኝ የስካር ደስታ ወዲያው ብን ብሎ አይጠፋም፡፡ ጤነኛ ደስታ ምንጩ ከልብ የሚፈልቅ ነው፡፡ ፈረንጆቹ ደስታን Pleasure እና Happiness ብለው ይከፍሉታል፡፡ ፈረንጆቹ ‹‹Pleasure is taking and happiness giving›› እንዲሉ በመውሰድ ወይም የሆነ ነገር በመጠቀም የምታገኘው ደስታ Pleasure ነው ይላሉ፡፡ Pleasure የሚባለው የደስታ ዓይነት ጊዜያዊ ነው፡፡ ምንጩ ውጫዊው ዓለም ነው፡፡ Happiness የሚሉት የደስታ ዓይነት ግን ከሰው ፊት ወይም ከቁሳቁስ አልያም የሆነ ነገር ተጠቅመህ የምታገኘው ደስታ አይደለም፡፡ ይሄ ደስታ ከራስህ ጋር በመደማመጥ፣ መንፈስህን በማንቃት፣ ለራስህ ከብር በመስጠት፤ ለሌሎችም ምላሽ የማይጠበቅበት ነፃ ፍቅርና ክብር በመስጠት፣ ቀና-ቀናውን በማድረግ የምትጎናፀፈው ደስታ ነው፡፡ የዚህ ዓይነቱ ደስታ ስሩ ልብህ ነው፡፡ ከመልካም መንፈስህ የሚቀዳ፣ ከነፍስህ የሚፈልቅ፣ ከበራው አዕምሮህ የሚጨለፍ፣ ከአናትህ ከህሊናህ ጓዳ ወደመላው ሰውነትህ የሚፈስ የህይወትህ ጅረት ነው፡፡ ብዙዎቻችን ይሄን ደስታ አግኝተን አላጣጣምነውም፡፡ አብዛኞቻችን በጊዜያዊ ደስታ (Pleasure) አቅላችንን ስተናል፡፡ ለራሳችን እንግዳ ነን፤ ለህሊናችን ባዳ ነን፡፡ ኸረ እንደውም ከእንግዳነትና ከባዳነት አልፈን ራሳችን ለራሳችን ጠላት ሆነንበታል፡፡ በገዛ ራሳችን ላይ የተነሳን የገዛ ራሳችን አሸባሪዎች አይደለንምን??

ደመወዝ ጎሽሜ በ‹‹ሦሥተኛው ኪዳን›› መፅሐፉ ስለጊዚያዊው የቀበሮ ደስታ የአባቶችን ሃሳብ አጣቅሶ ሲገልፅ፡-

‹‹ቀበሮ ካሉት ባህሪያት ሁሉ ሃሴት ይጎላበታል፡፡ ለምሣሌ ጠዋት ወይም ማታ ከጉድጓዱ እርቦት ይወጣል፡፡ ይፈልጋል፤ በምግብ አደን ብዙ ቦታ ያዳርስና ድንገት የፍልፈል ጉድጓድ ያያል፡፡ ጉድጓዱን እንዳየ የመጀመሪያ ስራው በደስታ መዝለል ነው፡፡ ይቦርቃል ይጨፍራል፡፡ በመጨረሻም ከጭፈራው በኋላ ጉድጓዱን ሲፈልገው ያጣዋል፡፡ በፈንጠዝያው ጉድጓዱን እርቆታል፡፡ እንደገና ፍለጋ ይጀምራል፡፡›› ይለንና

‹‹በመብልና በመጠጥ ብቻ ሕይወትን ለመበየን የሚሞክር ስታይ ቀበሮን አይተሃል ማለት ነው›› በማለት ቀበሮነትን በሰው ባህሪይ ወክሎ ምሳሌ ያቀርባል፡፡

እውነት ነው! አንዳንድ ሰዎችም የቀበሮ ዓይነት አስተሳሰብ ነው ያላቸው፡፡ ደስታቸው ሆዳቸው ላይ ነች፡፡ ሰውን የሚበይኑት ከመብልና ከመጠጥ የተነሳ ነው፡፡ ኑሮህን የሚለኩት፤ ህይወትህን የሚበይኑት የምታገኘውን ደመወዝ በማስላት ነው፡፡ ሆድ ነው ሚዛናቸው፡፡ ቁስ ነው መለኪያቸው፡፡ ከሆድ በላይ ያለውን ሕሊናህን አያስቡም፡፡ ከቁሳቁስ በስተጀርባ ስላለው መንፈስህ አያውቁም፡፡ ኪስህን አይተው እርካታህን ይለካሉ፡፡ አንተነትህን የሚቀምሩት ከፊትህ፣ ከአለባበስህ፣ ከምታገኘው ገቢ ተነስተው ነው፡፡ ሰውነትህን፣ አዕምሮህን፣ መንፈስህን፣ አስተሳሰብህን ለማወቅ አይጥሩም፡፡ ቁስህን እንጂ አመለካከትህን ማወቅ አይፈልጉም፤ ደመወዝህን እንጂ አንተነትህን አያሰሉም፡፡ አስተሳሰብህን ለመረዳት ሩቅ ናቸው፡፡ ፈተናህን፣ ጭንቀትህን፣ ውጣውረድህን፣ ውስጠዊ ህመምህን፣ ድካምህን አይገነዘቡም፡፡ የአንተነትህን ተመን የሚያወጡት፤ የኑሮህን ቀመር የሚያሰሉት ገቢህን አይተው ነው፡፡ ገቢህ ሕይወትህን እንደማይወስን፤ ኪስህ ማንነትህን እንደማይናገር፤ ፊትህ ሰውነትህን እንደማያረጋግጥ አልደረሱበትም፡፡ ባጠቃላይ ልክህን አያውቁም፡፡ የእነሱ ልክ ሆድና ቁስ ብቻ ነውና፡፡

ታላቁ ጥንታዊ ፈላስፋ አፒኩረስ፡- ‹‹የደስታን ስሜት ለማግኘት ብለህ የምታደርገው ነገር ሁሉ እውነተኛ ደስታ አይደለም፡፡ እሱ ጊዚያዊ ነው፡፡ ወይም Pleasure ነው›› ይለናል፡፡ አዎ እውነተኛ ደስታ ሌላኛው ጥንታዊ ፈላስፋ አርስጣጢሊስ እንደሚለው ውጤት እንጂ ግብዓት አይደለም፡፡ በበጎ ሕይወትህ፣ በአኗኗርህ፣ በምግባርህ፣ በቀና አስተሳሰብህ፣ በስኬትህ፣ በመልካም ስራህ የምታተርፈው እንጂ ቀድመህ የምታሰላው አይደለም፡፡

ፕሌቶም የደስታን ወለል ከፍ አድርጎ ነው የሰቀለው፡፡ ደስታ ይላል ፕሌቶ የሰው ልጅ የሞራል ከፍታና ግብረገብ ጣሪያ ነው በማለት ይበይናል፡፡ ሶቅራጦስም ደስታን ከስጋዊው ዓለም አርቆ ከነፍስ ጋር አጣብቆታል፡፡ ከስጋ ይልቅ ለነፍስ ትኩረት መስጠት የደስታ ቁልፍ ነው ሲል ደስታን ወደውስጣችን እንደንመለስ፣ ፊታችንን ወደመንፈሳችን እንድናዘነብል ይመክረናል፡፡

ወዳጄ ሆይ.... ደስታ በገንዘብ አይገዛም፡፡ ገንዘብ አልጋን እንጂ እንቅልፍን እንደማይገዛ ሁሉ መብልና መጠጥ፤ ዝና እና ቁሳቁስም እውነተኛ ደስታን አይሸምትም፡፡ ደስተኝነትህን የሚያረጋግጠው ያግበሰበስከው ቁስ ወይም ሌላ አካል ሳይሆን አንተነትህና አኗኗርህ ብቻ ነው፡፡ የሰው ፊት ስለቀጠቆረብህ ደስታህን አጣህ ማለት አይደለም፡፡ ሰው ስለሳቀልህም ደስታህን አታገኝም፡፡ ሰው ቢጠቁምብህም፤ ቢያጨበጭብልህም የአንተን ሕይወት አይቀይረውም፡፡ የሕይወትህ ቀያሪ ማርሹ ልቦናህ ብቻ ነው፡፡ የደስታህ ምንጭ ውስጥህ ነው፡፡ ቀና አመለካከትህና መልካም ስራህ ነው ሕይወትህን በሐሴት የሚያረሰርሰው፡፡ መንፈስህ ከፍ ሲል፤ ነፍስያህ ሲረካ ነው የደስታህ በር ወለል ብሎ የሚከፈተው፡፡ አርባአራት ሺ ነጥብ!

ቸር ደስታ!!!

ቸር ምሽት!!!

----------------------------------
እሸቱ ብሩ ይትባረክ (እ.ብ.ይ.)
ቅዳሜ መስከረም ፳፩ ቀን ፳፻፲፭ ዓ.ም.

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
2.4K viewsAbu Ki, 16:16
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 21:34:16 የስነ-ልቦና አቅሞን ማሳደግ ይፈልጋሉ?
እንግዲያውስ፦

እይታን የሚያሰፉ፤
ማንነትን የሚያንፁ፣
መልካምነትን የሚዘክሩ፣
ስብዕናን ከፍ የሚያደርጉ ውብ ምክረ ሀሳቦች በየእለቱ የሚነገርበት የምንጊዜም ግሩም ቻናል ተጋብዘዋል
697 viewsAbu Ki, 18:34
ክፈት / አስተያየት ይስጡ
2022-09-26 18:43:31 ይችን መብት ለሚስቴ ...


የአሜሪካ ፖሊሶች በሆነ ወንጀል ጠርጥረውህም ይሁን እጅ ከፍንጅ ሲይዙህ ( ያው አጉል ካልተሳፈጥክና ካልተፈራገጥክ በስተቀር እንዲሁም ሰኔና ሰኞ ካልገጠመብህ ማለቴ ነው ) በካቴና የሚቀፈድዱህ ሳይሆን የእጮኝነት ቀለበት የሚያጠልቁልህ ነው የሚመስሉት! ካቴናውን እያጠባበቁልህ ረጋ ባለ ድምፅ Anything you say can and will be used against you in a court of law. You have the right to an attorney...You have the right to remain silent....ምናምን ይሉሀል ...እና አንድ ሚስኪን አበሻ እያሳዩኝ ነው ...የአእምሮ ህመምተኛ ነው አሉኝ! ከሰባት አመት በፊት ሰይጣን አሳስቶት፣ የአሜሪካ ኑሮ ራሱን በጥብጦትና ተበሳጭቶ አውርታ የማታባራ ሚስቱን "አፍሽን ዝጊ አንች ሴትዮ" ይልና ፀጉሯን ጨምድዶ ቢላዋ አንስቶ ይዝትባታል ሬስቶራንት ውስጥኮ ነው ደግሞ!

እንደልብ የሚዛትባት አገር ዜጋ ነውና ...ዛቻውን ረስቷት አገር ሰላም ብሎ ወደቤቱ ሲመለስ የፖሊስ መኪና እያንባረቀ አስቆመዋ!የሆነ ሰው ደውሎ ጠቁሞ ነው... የሬስቶራንቱን ሴኪውሪቲ ካሜራ አይተውታል ! እና ከመኪናው ውረድ አሉና እጁን እያሰሩ ....You have the right to remain silent.... (ምንም ያለመናገር መብት አለህ) ...ሲሉት
"አይ ይችን መብት ለሚስቴ በሰጣችሁልኝ " ብሎ ዝም አለ ዝም አለ ! በቃ ዝም አለ ...ፍርድ ቤት ዝም ፣እስር ቤት ሲልኩት ዝም ፣እስሩን ጨርሶ ሲወጣ ዝም ፣ይሄው ሰባት አመቱ ዝም!!ፀበል ቢባል ህክምና ቢባል ዝም !! በሉ የምታውቁት ሰዎች ስም እንዳትጠቅሱ!

JOIN US
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
https://t.me/Yegna_Psychology
1.2K viewsAbu Ki, 15:43
ክፈት / አስተያየት ይስጡ